Site icon ETHIO12.COM

“ዓለም በኢትዮጵያ ጉዳይ ደንቁሯል” የፊንላንድ ው.ጉ.ሚ “አስነዋሪ ውሸት ፈጽመወዋል”

ethio12 news – ኢትዮጵያ አንዱን ጉዳይ ስታልፍ ሌላ ጉዳይ ይነሳባታል። ትህነግ የኢትዮጵያን መከለከያ ሰራዊት ካረደና ከጨፈጭፈ፣ መሳሪያ የጣሉትን በምርኮ ይዞ ካሰቃየ በሁውላ የተወሰደውን “ ህግ የማስከበር ዘመቻ” ተከትሎ ከአውሮፓ ህብረት፣ ከአሜሪካ፣ ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር በመናበብ የሚነሱት ጉዳዮች መቆሚያቸው የት እንደሆነ መገመት አስቸጋሪ እንደሆነ በጉዳዩ የተሰላቹ እየገለጹ ነው። ” … ሕዝብ ጠራርጌ አጠፋለሁ የሚል መንግስት ዓለም ላይ የለም። ይህ የአደባባይ ክህደት ነው” ትብሏል።

“ የህግ ማስከበሩ” ዘመቻ በአጭር ጊዜ ትህነግን ወደ ጫካ ከገፋ በሁዋላ የአማራ ሃይልና የኤርትራ ሰራዊት ይውጡ” በሚል የተጀመረው ክስ፣ መጨረሻውን “ ኢትዮጵያ የኬሚካል መሳሪያ ተጠቅማለች” በሚል የሃሰት ምስል የተደገፈ ዜና እስከ ማሰራጨት ደርሶ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት ክፉኛ የሚወቀስበት የኤርትራ ሰራዊት ጉዳይ ዛሬ መልስ ባገኘበት ውቅትና ሰራዊቱ ኢትዮጵያን ለቆ መውጣቱ በይፋ እየተገለጸ ባለበት ሁኔታ አዲስ ዜና ተሰምቷል።

ዜናውም “ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትግራይን ለማጥፋትና አንድ መቶ ዓመት እንዳታንሰራራ እንደሚያደርጉ ነግረውኛል” “We are going to destroy” and “wipe out the Tigrayans for one hundred years”  በሚል ከሶስት ቀን በፊት የፊንላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሃቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ ተናገሩትና መንግስት “ ቅጥፈት” ሲል መልስ የሰጠበት ዜና ነው።

ፔካ አክለውም “For me “If you wipe out a national minority, it’s obvious that we have to react because it looks like ethnic cleansing ለኔ አንድን አነስተኛ ቁጥር ያለውን ማህበረሰብ እንዳያንሰራራ አድርጎ መምታት ዘር ማጽዳት እነደማለት ነው” ሲሉ መናገራቸው መንግስትን ክፉኛ አስቆጥቷል።


Statement by Finnish FM on Situation in Ethiopia Unsubstantiated: Ethiopian Ambassador

However, minister Haavisto “showed no interest to travel to the region, but instead resorted to visit the refugee camp in neighboring Sudan and extrapolate grossly inadequate information to provide unfounded claims that put unnecessary pressure on the government of Ethiopia,”Ambassador Hirut stated in the letter.

Ethiopian Ambassador in Brussels, Hirut Zemene

ፔካ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከመንግስት ጋር መነጋገራቸውን ያወሳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ከውይይታቸው ጭብጥ ውጪ የሰጡትን ምስክርነት “ኃላፊነት የጎደለው፣ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ አስነዋሪ ውሸቶች” ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮንኖታል።

ሰውየው በፌብሩዋሪ ማለትም ከአራት ወራ በፊት በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ባልስልጣናት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ቢነጋገሩም ይህን ያህል ጊዜ ቆይተው የኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች “ የትግራይን ህዝብ እንጨርሳለን” እንዳሉዋቸው እስካሁንጅ ለምን እንዳልተናገሩ አላስታወቁም። ወይም አዲስ ስታንዳርድ አልገለጸም።

አዲስ ስታንዳርድ ይህን ዘገባ በለጠፈበት የፌስ ቡክ ገጹ ስር ፔካ የሰጡት አስተያየት ቀደም ሲል ጀምሮ በተለያዩ አክቲቪስቶችና ወገኖች ሲነገር የቆየ መሆን የጠቀሱ “ በአውሮፓ ህብረት ሚዛናዊነት ተስፋ ቆረጥን” ያሉና ሰውየው የአደራዳሪነት ስራ ለመስራት አቅም እንደሌላቸው ያመለከቱ ታይተዋል።

በጠነከረ ቃላት ወርፎ መግለጫ ያሰራጨው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሰውየውን “ ቅጥፈት” ሲል የጠራውን ምስክርነት፣ “በራስ-አዕምሮ ውስጥ ተደብቆ የሚቆይ የቅኝ-ግዛት አስተሳሰብ ነው” ነው ሲል ረግሞታል። መረጃው ይግንዛቤ እጥረትና ሽፍጥ እንደሆነም ግልጿል።

የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀቪስቶ እ.ኤ.አ. ሰኔ 15 ቀን 2021 ለአውሮፓ ፓርላማ የሰጡትን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ እንደሚያደርገው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።

ሚስተር ሀቪስቶ ለአውሮፓ ፓርላማ ባቀረቡት ገለፃ የቀረቡት ክሶች የኢትዮጵያን መንግስት ለማዳከም የታቀደ፣ በሃሰተኛ መረጃና  በአስነዋሪ ውሸቶች የተሞሉ ሲሆን፣ ዓላማው ተገቢ ያልሆነ ጣልቃ ገብነትን ለማመቻቸት ያላቸውን  መሰረታዊ ፍላጎት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑንን ጠቅሶ ሚኒስቴሩ በይፋ ኮንኖ አስታውቋል።

ከትግራይ ተቃዋሚዎች ጋር ለመነጋገር በአሁኑ ወቅት ሴሉ በትግራይ ውስጥ እንደ ተቃዋሚ እንደምይቆጠር፣ በሕገ-መንግስታዊ ሂደት የአሰራር ደንብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት የተፈረጀ ቡድን መሆኑ፣

የተኩስ አቁም ትግበራ በተመለከተ፣ የሕግ ማስከበሩ ወይም የመንግስት ተግባር የእኩልነት ተሳትፎ ሳይሆን የአሸባሪ ቡድን መሳሪያዎቻቸውን እንዲያስቀምጡ እና በሀገሪቱ ውስጥ ጥፋትን እንዳያቆሙ ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሆኖ ሳለ፣ ሚስተር ሃቪስቶ የአሸባሪው ትህነግ ተዋጊዎች መሳሪያቸውን እንዲያስቀምጡና ምህረት እንዲጠይቁ መንግስት ያደረጋቸውን ተደጋጋሚ ጥሪዎች ችላ እንዳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውሷል።

ከዚህም በላይ ምርጫው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ. ሰኔ 21 ቀን 2021 ለምርጫ እንደሚወጡና ምርጫ እንደሚያካሂዱ ያስታወቀው የመንግስት መግለጫ፣ ይህን የኢትዮጵያውያንን ፍላጎትና ምኞት የሚያረጋግጥ ዲሞክራሲያዊ ሂደት አቅልሎ መመለከት ስህተት መሆኑንንም አስታውቋል።

የግብርና ዳግም ማስጀመር ሂደትን አካቶ ዝርዝር ውይይቱን ያመለከተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ  ፔካ ሃቪስቶ ከጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ፣ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን አመልክቷል። ቢሆንም ቅሉ በስም የተጠቀሱት የአውሮፓ መልዕክተኛ ባቀረቡት ሪፖርት የውይይቶቹን ሙሉ ሃሳባ አለማንጸባረቃቸውን ነቅፏል። ከላይ እንደተገለጸው ለማድረግ ለታሰበው ጉዳይ አመቺ ይሆን ዘንዳ “ኃላፊነት የጎደለው፣ዲፕሎማሲያዊ ያልሆነ አስነዋሪ ውሸቶች” የተሞላበት መረጃ በመስተታቸው ሪፖርቱን እንደማይቀበለው መግለጫው አስታውቋል።

የኢትዮ12 ተባባሪ ዲፕሎማት አስተያየት ጠይቀናቸው፣ “ የአንድ አገር መሪዎች፣ ለድርድር የመጣን አካል የራሳቸውን ሕዝብ እንደሚጨርሱ ይናገራሉ ብሎ ማሰብ በዲፕሎማሲ ዓለም ድንቁርና ነው። ዓለም በኢትዮጵያ ጉዳይ ደንቁሯል። ዓላማው የፈለጉትን ለማሳካትና በሁሉም መንገድ አልሳካ ሲል ወደ ለየለት ቅጥፈት የመሸጋገር ምልክት ነው። ሰውየው ቃል በቃል የደገሙት የትህነግ ሰዎችና የሚከፍሏቸው ሚዲያዎች የሚሉትን ነው” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ነገ ደግሞ ምን እንደሚሉ መጠበቅ ነው ብለዋል።-

ፔካ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ትግራይ ሄደው እንዲጎበኙ ተጠይቀው ፈቃደኛ ሳይሆኑ፣ ሱዳን ደርሰው የተሳሳተ ሪፖርት በማቅረብ ኢትዮያን ሲከሱ በብራስልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ በቂ ምላሽ እንደሰጧቸው ይታወሳል። ethio12 news

Exit mobile version