Site icon ETHIO12.COM

ብልጽግና ከሸነፈ – ቀጣይዋ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሌሊሴ ነሜ

ብልጽግና ከቀጣዩ ምርጫ በሁዋላ ከፍተኛ የሚባል የሹም ሽር እንደሚያደርግ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይ በአዲስ አበባ ፓርቲው ካሸነፈ ለሊሴ ኔሜን ከንቲባ አድርጎ እንደሚሾም የኢትዮ12 የመረጃ አጋሪዎች ገልጸዋል። አዳነች አቤቤ ወዴት እንደሚዛወሩ ግን አልገለጹም።

ቀደም ሲል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽንን ሲመሩ የነበሩት ሌሊሴ ኔሜ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ይፋ ባደረጉት ሹመቱ ከነገ ሰኔ 16 2012 ጀምሮ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር መሆናቸው ይታወሳል።

ሌሊሴ ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም. ጀምሮ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የሰሩ፣ ከዚያ ቀደም ብሎ በኦሮሚያ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም የኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉና በሂደት ወደ ፌደራል እየተንደረደሩ የመጡ ባለስልጣን ናቸው።

ሌሊሴ ወደ መንግስት ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት በጂማ ዩኒቨርስቲ በቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩትና በአካባቢ ምህንድስና ዘርፍ መምህር ሆነው አገልግለዋል። ከሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚ ልማት ፕሮግራም ፖስት ግራጁዌት፣ በሊድ ስታር ዩኒቨርስቲ በቢዝነስ አስተዳደር የማስትሬት፣ በጅማ ዩኒቨርስቲ ምህንድስና ትምህርት መከታተላቸውን ስለ እሳቸው ሊንክዳል ላይ የሰፈረው መረጃ ያስረዳል።

ኢትዮ 12 ባላው መረጃ ብልጽግና አዲስ አበባን ለማስተዳደር ካሸነፈ ስር ነቀል ለውጥ ለመካሄድ እቅድ አለ። በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ካቢኒዎች በካድሬነት ሳይሆን በሜሪት ይሆናል። በዚህ እሳቤ እንደ ፍትህ ሚኒስትሩ አይነት ሰዎች ወደ ፊት ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ምርጫውን ፓርቲው አዲስ አበባና በትቅል በአገሪቱ ሲያሸንፍ ነወ።

Exit mobile version