Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ በምርጫ ቀን ድል ያስመዘግባል የሚል ተስፋ ተሰጠ

መንግስት ውጊያ ሳይሆን አሰሳ ላይ እንደሚገኝና ከዚህ በፊት ገብተውበት በማያዉቁበት አቅጣጫ በመከታተል እርምጃ እየወስደ እንዳለ በሚገልጽበት ወቅት ጫካ ያለው የትህነግ ሃይል በምርጫው ዕለት ” ታላቅ” የተባለ ድል እንደሚያስመዘግብ በተስፋ ለሚጠብቁት መገለጹ ተሰማ። በሌላ በኩል ደግሞ ትህነግ ሲመታ አቅጣጫ ለማስቀየር አስቀድሞ መረጃ በመስጠት አጀንዳ የፕሮፓጋንዳው መሪ ለመሆን የሚያራግበው ጉዳይ መሆኑም እየተመለከተ ነው።

የአሜሪካ ተባባሪያችን በውጭ አገር ገንዘብ በማሰባሰብና ሰልፍ በመውጣት ድጋፍ ለሚያደርጉት የትህነግ ደጋፊዎች ተሰራጭቷል ሲል እንደተናገርው ሰኞ ታላቅ የተባለው ድል በሁሉም ወገን ይጠበቃል።

አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያዊው ጀግናው አሉላ አባ ነጋ ስም የተሰየመ የማጥቃት ዘመቻ በቀናት ውስጥ እንደሚጀመር በኖርዌይ ላሉት ፕሮፌሰር ሼትል ስልክ ደውለው እንደገለጹ ተጠቁሞ ዜና ተሰራጭቶ ነበር። በዚሁ ከቀናት በፊት በወጣው ዜና ፕሮፌሰሩ ” እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ በቀናት ውስጥ ዘመቻው እንደሚጀመር ጠቁመውም ነበር።

ይህን መረጃ የጠቀሰው ተባባሪያችን በተመሳሳይ በትህነግ ደጋፊዎች ዘነድ ይህ ዜና እየተራባና ውጤቱ በጉጉት እየተጠበቀ ነው። የተባለው የማጥቃት ኦፕሬሽን በሁለት ብርጌዶች የሚደገፍና በሶስት አቅጣጫ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ዱላ እንዲያሳርፍ የታቀደ ስለመሆኑ በፍራው አዋጊ የሆኑ ዓላማቸውን በሚደግፉ መገናናዎች በገሃድ ሲናገሩም ተሰምቷል።

የትግራይ ተወላጅ የሆነው ናትናኤል በቅርቡ ትግራይ ደርሶ ከተመለሰ በሁዋላ አሰባሰብኩት ባለው መረጃ ትህነግ ካሁን በሁዋላ ውጊያ ከፍቶ የበላይነት የሚይዝበትቭ አምክኖ እንደሌለ ማስታወቁ አይዘነጋም። እንደውም በግዳጅ እናቶች ልጆቻቸውን እንዲያስረክቡ፣ አለበለዚያ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጣልባቸው፣ በየጊዜው የተሳሳተ መረጃ የሚያወጡት ” ነገ እንመጣለን” የሚሉት ህዝቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር ለማድረግ እንደሆነ መግለጹ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያን የሚወዱ ምርጫውን አጠናቀው ወደ መደበኛ ጉዳዮች ለመመለስ ሲናፍቁ በተመሳሳይ ትህነግ በምርጫው ዕለት ድል ለማስመዝገብ ቃል ገብቶ ደጋፊዎቹ በጉጉት እየጠበቁት ነው። መንግስት እያካሄደ ባለው አሰሳ በርካታ ህጻናት እጅ መስተታቸን፣ የትህነግ ሃይል እየተመታ እንደሆነ፣ በህዝብ ጥቆማ የተደበቁ እየተለቀሙና የተቀሩትም እጃቸውን እየሰጡ መሆኑንን እየገለጸ ነው።

ከሁሉም ወገን ያልሆኑ ግን በትግራይ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ እንዲቆም ምን መደረግ አለበት የሚለው ያሳስባቸዋል።

Exit mobile version