የወያኔ ሚስጥራዊ ሃብት አዲስ ጦርነት አስነሳ “ እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ በረሃ ያሉትን ጠይቁ”

ራሱን ከጥንስሱ እስከ ሞቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር እያለ የሚጠራው ቡድን ስያሜው እያወዛገበ ነው። መንግስት “ ጁንታ” ብሎት ቢቆይም፣ አሁን ላይ “ ጁንታ ለመባል የሚያበቃ ቁመና የሌለው ተራ ሽፍታ” መሆኑን አስታውቋል።

በተቃራኒው አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የትህነግ ወዳጅ ሚዲያዎች “ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት” እያሉ የሚጠሩት ተዋጊ ሃይሉን እያሰባሰበ እንደሚገኝ፤ በቅርቡ ሙሉ ትግራይን እንደሚቆጣተር፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የመንግስት ተዋጊዎችን እንደገደለና ምርኮኞች ከመብዛታቸው የተነሳ መቀለብ እንዳልቻለ ደጋግመው ይናገራሉ።

Getachew K Reda (@reda_getachew) | Twitter
አቶ ጌታቸው ረዳ ” አብይን በሚገባው መንገድ መጠበንጃ እናናግረዋለ”

የተፈጠሩበት ቀን እንደሆነ የሚናገሩትን የካቲት 11 መቀለ እንደሚያከብሩ፣ በተለይም ዛሬ እግራቸው ነፍርቆ መራመድ እንደተሳናቸው የሚደመጠው አቶ ጌታቸው “ አብይን በሚገባው መልኩ በጠመንጃ እናናግረዋለን” በሚል በተደጋጋሚ መደመጡ በአፍቃሪዎቻቸው ዘንድ ታላቅ ተስፋ ሆኖ ከርሞ ነበር።

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የአገር መከላከያ ሰራዊት በቂ የማገገሚያ ጊዜ ወስዶ ራሱን ካደራጀ በሁዋላ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ትህነግ እንዳልሆነ እንዳደረገው መረጃ እየወጣ ነው። መንግስት ዝርዝሩን ባይናገርም በጥቅሉ ትህነግ የተዋጊነት ቅርጽ የሌለውና በየጥሻው ተበጣጥሶ እንደሚገኝ፣ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መመታቱና ማገገም እንደማይችል ይፋ አድርጓል።

በከባድ መሳሪያ፣ ድሮንን ጨምሮ በአየርና በምድር በስምንት አቅጣጫ የተከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ቁልፍ የትህነግ መሪዎችና አዋጊ ጀነራሎች ተገድለዋል። በሺህ የሚቆጠሩ ተገድለዋል። ወታደራዊ ታማኝ ምንጭ የጠቀሱ እንዳሉት ጉዳቱ ብቻ ሳይሆን ተህነግ የተመቱ አመራሮቹ እንዳይታወቁ ሲባል የፈጸመው ተግባር በዘግናንነቱ ተመዝግቧል።

የዶክተር ደብረጽዮን ጠባቂ ራሱን ስቶ መገኘቱና ከዛም በሰጠው ምስክርነት “ ሰዎቹ ግራ ገብቷቸዋል፤ ምን እንደሚያደርጉ አያውቁም” ማለቱ ዛሬ ለተሰማው ዜና መነሻ ግብዓት ይሆናል።

የኢትዮ 12 የአሜሪካ ተባባሪ እንዳለው በውጭ አገር ያለው የትህነግ አካል ተስፋ ወደ መቁረጡ አመዝኗል። የገንዘብ ድጋፍ በጠየቁና “እኛ ስለገንዘብ የምናውቀው ነገር የለም” ባሉት መካከል የተነሳው ልዩነት በቅርቡ ይፋ ይሆናል።


RELATED NEWS


ትህነግ ኢትዮጵያን ሲመራ ኤምባሲዎችን ለኔትወርኩ ማደራጃ ይጠቀም እንደነበር መረጃ ያሰባሰበው ተባባሪያችን እንዳለው፣ ኤንባሲ ውስጥ በቋሚ ደመወዝ ለዚሁ የኔትወርክ ስራ ሰዎች ይመደቡ ነበር። ለውጡ ከመጣ በተለይም ግጭቱ ከተጀመረ በሁዋላ ግን ይህ ኔት ዎርክ በአብዛኛው ራሱን ከኤምባሲ አላቋል።

ቀደም ሲል ትህነግ ያባረራቸውና የኔት ዎርኩ ቀጥተኛ አባል ያልነበሩና በውጭ አገር ያለውን ኔት ዎርክ በንቃት የሚመሩትን አብሮ የቀላቀላቸው “ ትግራዋይ” የሚለው አዲሱ እቅድ ሲሆን፣ መንግስት የህግ ማስከበሩን ሲጀምር የታሰበው እቅድ ሙሉ በሙሉ መክሸፉና ጉዳት መድረሱ ሁሉም በአንድነት ድምሳቸውን ለማሰማት እንዲሰባሰቡ ምክንያት እንደሆነ ተባባሪያችን ይገልጻል።

በዚህ መነሻ ኔት ወርክ ውስጥ ያሉትና አሜሪካ ሆነው ድርጅቱን የሚመሩት፣ የድርጅቱን ሚስጢራዊ ሃብት የሚቆጣተሩና የሚያስተዳድሩት ክፍሎች ኔት ወርኩ ከገለላቸውና “ ትግራዋይ” ብሎ ከተነሳው አካል ጋር የመገናኘት በር ከፈተ።

እንደታሰበውና እንደተወራው ጦርነት የትግራይ ባህላዊ ጨዋታ ሳይሆን ቀረና የመከራው ጊዜ መጣ። ሃያ ሰባት ዓመት መንግስት የነበረው ትህነግ መቀለ ገባ። ከመቀለ በሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ወደ ጫካ ወረደ። ከጫካም ወደ ተከዜ ሰርጥ ዘለቀ። እንደተባለው “ ሽፍታ” ሆነ።

ጊዜው እየረዘመ ሲሄድ አንዳንድ ጥያቄዎች መነሳት ጀመሩ። የውጭ አገሩን ትግል በመምራት፣ በማስተባበር ከኔት ዎርኩ መሪዎች ይልቅ ኔት ዎርኩ ውስጥ የሌሉ ተቆጣጠሩት። የተለያዩ ስልት እየነደፉ ትግሉን እየመሩ በኔት ዎርክ ለቆዩትና የድርጅቱን ሃብት ያስተዳድራሉ ለሚባሉት አምባሳደር ብረሃነ ጨምሮ የገንዘብ ጥያቄ ማቀርባቸው ግድ ሆነ። ተባባሪያችን እንዳለው አሁን ላይ “ ለመሆኑ ሃብታችን የት ነው” የሚለው ጥያቄ በስፋት ተነስቷል።

“ እኛ የምናወቀው ነገር የለም፤ በረሃ ያሉት ናቸው የሚያውቁት” የሚል ምላሽ እነ አምብሳደር በርሃነ ገብረ ክርስቶስና ፍስሃ አስገዶም ይፋዊ ባልሆነ መልኩ መልስ ሰጥተዋል። ኔት ወርኩ ተፍቷቸው ከነበሩት መካከል እንደ እነ ስዬ አብርሃ ያሉትና እንደሳቸው ዳር የነበሩት የተሰጠውን ምላሽ አልወደዱትም። በዚሁ ሳቢያ የቃላት ጦርነት ማድረጋቸውም ተሰምቷል።

አምባሳደር ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ” የምናውቀ ነገር የለም”

በዚሁ የከረረ ንትርክ ሳቢያ በሃብት እጥረት ከአየር ወርዶ ለነበረው የትግራይ ሚዲያ ሃውስ መጠነኛ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉ ታውቋል። ምን ያህል አየር ላይ እንደሚኖር ባይታወቅም ይህ እስከተዘገብ ድረስ አየር ላይ ነው።

እንደ ተባባሪያችን መረጃ ከሆነ ተከዜ በረሃ ተበጣጥሶ ያለው ሃይል መመናመኑ በአሜሪካ ባሉ ቁንጮ ደጋፊዎች ዘንድ አንዱ በሌላው ላይ ጣት እንዲቀስሩ አድርጓቸዋል። በህመም ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው የአቶ ጌታቸው አሰፋ እውቀት ማነስና ግትርነት፣ ዶክተር ደብረጽዮን መለስ ዜናዊ ያባረራቸውን ጦርኞች ማሰባሰባቸው ለዚህ እንደዳረጋቸው በማንሳት እየተካሰሱ ነው።

በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልጣን፣ ሃብት፣ ዘመናዊ ኑሮ የከዳው የትህነግ አመራር ምንም ይሁን ምን ወደማይመለስበት ደረጃ መድረሱን የተረዱ የድርጅቱ ሃብት የህዝብ ስለሆነ መረጃ እየጠየቁ ነው። ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ እንዳሉት አንድ ክላሽ ለአምስት የሚሰጠው ትህነግ ችግሩ ሰፊ ነው። ከሁሉም በላይ ሰብአዊ ቀውሱ እርብርብ ስለሚጠይቅ እዛው ላይ ማተኮር ይሻላል የሚል አቋም ያላቸው እየተነሱ ነው። ተባባሪያችን እንዳለው የአሜሪካ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደካማ ነው። አደረጃጀቱ ሊቀየር ይገባል። እጅግ ስልጡንና ብቃት ያላቸው ሰራተኞች ሊመደቡለት ይገባል። ዛሬ የተለየ ሃሳብ ማራመድ የሚፈለጉ የትግራይ ልጆች አሉና ኤንባሲው ቢያሰባስባቸው መልካም እንደሚሆን አመልክቷል።


    Leave a Reply