ETHIO12.COM

“ጃል ሮባን ጨምሮ 295 አሸባሪ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ደመሰስኩ፣ በርካታ ማረኩ” ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

በምዕራብ ኦሮሚያ ጃል ሮባ በማለት ራሱን የሚጠራ የሸኔ ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ 295 አሸባሪው ሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱንና በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ መማረካቸው ተገለጸ። ሸኔም ሆነ የኦነግ ሰራዊት በሚል ራሱን የሚጠራው ክፍል ያለው ነገር የለም። ኦሮሚያ ፖሊስ ያስፈረውን እንዳለ ከታች አቅርበናል። ድርጅቱ የሚያወጣው መግለጫ ወይም ማስተባበያ ካለ ሲደርሰን እናካትታለን።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጠላትን የማጽዳት ሥራ ከጀመረ ሰንብቷል፤ በተለይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ፖሊስ ከሁለት ወር ወዲህ ልዩ እቅድ በማውጣት ወቅቱ የሚጠይቁውን የሽምቅ የውጊያ ስልት በመጠቀም በጠላት ላይ የእሳት ረመጥ በመሆን መቆሚያ መቀመጫ አሳጥቶታል።

ጃል ሮባ

በአራት ቀን ውስጥ 95 የጠላት ታጣቂ ቡድን ደምስሰን ለህዝባችን የድል ብስራት ማብሰራችን ይታወሳል።

በተመሳሳይ መልኩ በምዕራብ ኦሮሚያ የተለየ ኦፕሬሽን እየተካሄደ በመሆኑ በጠላት መንደር ሽብር ሆኗል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የምዕራብ ኦሮሚያ ክላስተር ከምስራቅ እና ማዕከላዊ ክላስተር ጋር በመዋሃድ ህባችን የሚሰጠውን መረጃ እንደ ከፍተኛ ግብአት በመጠቀም ድጋፉን እንደ ምርኩዝ በመጠቀም ከመደበኛ ፖሊስ ጋር እንደ ግራና ቀኝ ዓይን በመሆን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በመጣመር የአከባቢ ሚኒሻን እንደ ብርሃን በመጠቀም አኩሪ ድል አስመዝግቧል።

በዚህ መሰረት በሁለት ወር ውስጥ 295 የህዝብ ጠላት የሆነው አሸባሪው ሸኔ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ እንዲ ደመሰሱ ተደርጓል ፤ በተጨማሪም ጠላት ሲጠቀምበት የነበረውን የተለያየ 126 የጦር መሳሪያ እና 1995 የተለያዩ አይነት ጥይቶች ገቢ ማድረግ ተችሏል።
በተጨማሪ በዚህ ኦፕሬችን በጅማ ዞን ሊሙ ኮሳ ወረዳ ራሱን ጃል ሮባ ብሎ የሚጠራ የሸኔ ከፍተኛ አመራር አብሮት ከነበሩ 22 የአሸባሪው ታጣቂዎች ጋር ተደምስሷል።

ብዛት ያለው የተማረከ እና እጅ የሰጠ ጠላት እንዳለ ሆኖ በሌላ በኩል በዚሁ ኦፕሬሽን ለዘመናት ህዝቡን ሲያምሱ የነበሩ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የተለያዩ ሽፍቶች ተደምስሶ ለህዝቡ እፎይታ ሆኗል። ብዛት ያላቸው የተለያዩ አይነት ሽጉጦችም በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።

በአጠቃላይ የድሉ ባለቤት ለሆነው ህዝባችን ከፍ ያለ ምስጋና አለን።

ዜና ምንጭ : ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

Exit mobile version