Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ “በቆላ ተንቤን የድል ዜና አለኝ” አለ፤ ባለከዘራው መኮንን የታፈኑት በምኞት ነው

በጉጉት ሲጠበቀ የነበረውን የምርጫ ዜና በከፍተኛ ወታደራዊ ድል ለመቀልበስ በሶስት አቅጣጫ ትህነግ የከፈተው የማጥቃት ዘመቻ እስካሁን የተባለለት ነገር የለም። ይልቁኑ የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ አርፋፋዱ ላይ ” የድል ዜና አለኝ” ሲል እስካሁን የተገኘውንና ተጨማሪ ድሎችን የሚያሳይ መረጃ እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ “ቆላ ተንቤን ሰሞኑንን ሲሹለከለክ የነበረው የአሸባሪው ጁንታ ሃይል እርምጃ ተውሰዶበታል” ብለዋል።

” የአሸባሪው ህወሀት ርዝራዥ፣ መሰሎቹና ተባባሪዎቹ ከሆኑ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በመሆን ሃገራዊ ምርጫውን፣ የህዳሴ ግድቡን ሁለተኛ ዙር ሙሌት ለማደናቀፍ ሲሞክር ሰሞኑን በሚሹለከለክበት ቆላ ተንቤን በሀገር መከላከያ ሰራዊት እርምጃ ትተወስዶበታል” ያሉት ኮሎኔሉ፣ የአሸባሪውን ሃይል አመራሮች ለመያዝ የሚደረገው አሰሳ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።

አመራሩ ጦርነቱን በቅርብ ሆኖ እንደማይመራው ያስታወቁት ኮሎኔል ጌትነት ” ይህ ከሩቅ ሆኖ ንጹሃንን መማገድ ላማዱ ነው” ብለዋል። ” የጁንታው መሪዎች እየተሹለከለከና እንደልማዳቸው በርቀት ተደብቀው እንጂ በቅርበት የማይመሩት ውጊያ ሚሊሻዎችን እንዲሁም ምንም ወታደራዊም ሆነ የአስተሳሰብ ብስለት የሌላቸውን ወጣቶችን እየማገደ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

“የአሸባሪው ጁንታ መሪዎችን አድኖ የመያዝ ኦፕሬሽን ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት በስፋት እያከናወነ ይገኛል” ያሉት ኮሎኔል ጌትነት፤ “እስካሁን የተገኘውን ውጤትን በቅርብ ከሚመዘገቡ ተጨማሪ ድሎች ጋር ደምረን ይፋ እናደርጋለን” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

“ምርጫ ለማደናቀፍ ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊ መርጣለች። አባይ እንዳይሞላ ቢሰሩም በቅርቡ ሞልተን እናሳያቸዋለን” በማለት የሰራዊቱን ዝግጁነት ገልጸዋል። አሸባሪው አሸባሪው ጁንታ በቅርቡ “ጀ/ል ብርሃኑ ጥላሁንን አፍነናል፣ኮ/ል ሻምበል በየነን /ባለ ከዘራውን/ ገለናል” የሚል የሀሰት መረጃ ማሰራጨቱን ያስታወሱት ኮሎኔሉ ይህ ምኞት ጁንታው የኖረበት የሃሰት ባህሉ ውጤትና የሚያደናግራቸውን ክፍሎች መግዣ እንደሆነ አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው ካሉበት ሆነ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሶስት አቅጣጫ የኢትዮጵያ መከላከያ እየተደበደበ መሆኑንን አመልክተው ” የዓለም ዓቀፉ ሃይል ከማውገዝ ወጥቶ እርምጃ መውሰድ አለበት” ማለታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። በዚሁ ዘገባ ” የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የመከላከያችን የመጀመሪያው መስመር ነእ” ማለታቸውንም ገልጸናል።

ይህ እስከታተመ ድረስ አቶ ጌታቸውም ሆኑ ሌሎች ትሀንግ ድል እንዳስመዘገበ አልገለጹም። መንግስት ግን ከምርጫው በሁዋላ ምርኮኞችንና በትህነግ ላይ የደረሰውን ጥቃት በፊልም ለማሳየት መዘጋጀቱ ተሰምቷል።

Exit mobile version