ETHIO12.COM

የጥንቃቄ ዜና “የትህነግ ጦር ሰላማዊ ነዋሪ መስሎ መቀለ ገብቷል ብለው…”

May be an image of child, standing and outdoors
አቶ ጌታቸው ህጻናት መካከል ሆነው ያሰራጩት ስዕል እጅግ መነጋገሪያ እየሆነና ትህነግ ህጻናትንና ሲቪል ሰዎችን መመሸጊያ እንደሚያደርግ የሚያረጋግጥ እንደሆነ ማሳያ ሆኗል። መቀለ ሰርገው ገብተዋል የተባሉት እውነት ከሆነ ያሉት እንደ አቶ ጊታቸው ህዝብ መካከል ነውና ጥንቃቄ የተባለው የከፋ ዜና እንዳይዘማ ከመስጋት ነው

“ሚስጢር ነው። ለሚመልከታቸው አድርሱልኝ” ሲል ነዋሪነቱ በአውሮፓ የሆነ የትግራይ ተወላጅ ለዝግፍት ክፍላችን እንዳስታወቀው እሱን ስጋት ላይ የጣለው መረጃ እየተሰራጨ ነው። መረጃው ” የትህነግ ሃይል መቀለ በድብቅ ገብቷል” የሚል ነው። ከመረጃው ጋር ይገናኝ አይገናኝ ባይታወቅም ” … ሰራዊታችን ከመቀሌ ብዙም የራቀ አይደለም እና ከፊት ለፊቱ የበለጠ አስገራሚ የድል ዜና ይጠብቁ!” ሲሉ ኪዳኔ ገ/ህይወት

እሱ ከሚሳተፍበት የውስጥ የግንኙነት መስመር ” ሚስጢር” በሚል “የትህነግ ሃይል ራሱን ቀይሮ፣ ከሕዝብ ጋር ተቀላቅሏል። መቀለን አሁን ነጻ እናወጣለን። መመሪያ ብቻ ነው የሚጠበቀው። መመሪያ ሲደርሰው ከየመንደሩ እየወጣ እርምጃ ይወስዳል። ከተማችን ነጻ ትወጣለች” ተብሏል። መረጃውን የሚያጋሩት ጉዳዩ በሚስጢር መያዝ እንዳለበት ገልጸው አክለው አንዳሉት ጦረነቱን ወደ አማራ ክልል ማስፋት የተፈለገውም ለዚሁ ዓላማ ተብሎ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአዲግራት እንደሆነው ዓይነት በድንገት መቀለን እንደሚቆጣጠሩ ከመሬት ( በስፋራው ካለው የትህነግ ዓመራር) ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደተነገራቸው፣ ይህንን በማሰብ ድጋፋቸውን በገንዘብ እንዲያጠናክሩ መመሪያ መውረዱን፣ የመለሶ ማቋቋሚያ ገንዘብ እንዲሰበሰብ ወዘተ ተናግረዋል።

በዋናናት ከላይ የተገለጸውን ሃሳብ የጠቆመው የትግራይ ልጅ ” ይህ መረጃ እጅግ የከፋ ነው” ብሏል። ባለው መረጃ መቀለ ዙሪያና ከተማዋ ውስጥ እጅግ በርካታ ሃይል መኖሩን፣ አንድ ነገር ከተፈጠረ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ የሆነና ሁሉም ዓይነት ትጥቅ ያለው ሰራዊት በመሆኑ ዕቅዱ ለሚዲያ ጦርነት ሕዝብ ለማስጨረስ እንጂ ሌላ ውጤት ስለማያመጣ የማስተማር ስራ መሰራት እንዳለበት ጠቁሟል።

እንደ አንድ የትግራይ ተወላጅ ሁሉንም ጉዳይ በግንኙነት መረቡ አማክይነትና በቀጥታ በስልክ ግንኙነት እንደሚከታተል ያስታወቀው መረጃ አቀባይ፣” በተለይ ምን መደረግ እንዳለበት የጠቆመው ነገር ባይኖርም፣ እቅዱ እንደታወቀ ይፋ ማድረግ አስፈላጊ መስሎ እንደሚታየው አመልክቷል።

በሌላም በኩል ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ ለፌስ ቡክ ተከታዮች በማሰራጨት በዩቲዩብና ፊስቡክ እንዲጮህበት ከተደረገ በሁዋላ ” ይሄ ውሸታም መንግስት” በሚል የመረጃ ማክሸፊያ ስራ በመስራት የመንግስትን ተዓማኒነት ማበላሸት በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ በሆኖ መገኘቱ እንደተነገራቸውና በዚሁ እንዲቀጥሉ መጠቆሙን ምንጩ ገልጿል።

ከበረሃ በተደጋጋሚ ቲዊት የሚያደርጉት ፕሮፌሰር ክንድያ ከላይ ከተባለው መረጃ ጋር ይገናኝ አይገናኝ ባይታወቅም ” …ሰራዊታችን ከመቀሌ ብዙም የራቀ አይደለም እና ከፊት ለፊቱ የበለጠ አስገራሚ የድል ዜና ይጠብቁ ” ሲሉ ለመረጃው ድጋፍ የሚሆን ዜና በቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል።

በተንቤን ግንባር አቢ አዲ ሰቆጣ መንገድ የትህነግ ሰራዊት ድል እየቀናው እንደሆነ በጠቆሙበት መልዕት ልዩ ዜና እንደሚሰማ ያመለከቱትን ተከትሎ እስካሁን ተጨማሪ መረጃ አለወጣም። ይልቁኑም በሰቆጣ በኩል በይፋ መንግስት ባያስታውቅም የአማራ ልዩ ሃይል ድል እንደቀናውና ” ከሃጂ ” የተባሉ የጦር መሪን ጨምሮ ትህነግ ላይ ጉዳት እንደደረሰና ያሰቡት ለጊዜው እንዳልተሳካ እየተጠቆመው ነው። ይሁን እንጂ መንግስት ማረጋገጫ አልሰጠም። ነገር ግን በቆላ ተንቤን የመሸገው ሃይል ላይ ጥቃት እየተካሄደ እንደሚገኝና ጥቃቱም እንደሚቀጥል መከላከያ ይፋ አድርጓል።

በሰሞኑ የውጊያ አውድ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ድል እንደቀናውና በርካታ አዳዲስ ምልምሎች እንደማረከ ሲናገር፣ መከላከያ በበኩሉ ከምርጫው ጋር በተያያዘ በተደረገ ሰራዊት የማቀሳቀስ እርምጃ የተፈጠረ ክፍተት በመሆኑ እርምት ተወስዶ የማጥቃት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንን አመልክቷል። ይህን ካለ በሁዋላ ግን ያስታወቀው ነገር የለም።

ጦርነቱን ወደ አማራ ክልል በማስፋት የሱዳን መግቢያና መውጪያ በር ለማመቻቸት የሚደረግ የመጀመሪያ ሙከራ እንደሆነ ስለ ጦርነቱ መረጃ እንዳላቸው የሚጠቁሙ አሉ።

Exit mobile version