Site icon ETHIO12.COM

የህወሓት አክቲቪስት ማርቲን ፕላውት “ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ያለፍተሻና እጀባ እርዳታ ይስጡ”

“ህወሓቶች በትጥቅ ትግሉ ወቅት የእርዳታ ገንዘብን ለመሳሪያ ግዥ አውለዋል” በሚል ያጋለጠው በወቅቱ የቢቢሲ የአፍሪካ ዴስከ ኤዲተር የነበረው ማርቲን ፕላውት ዛሬ ደግሞ የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ድርጅት መሳሪያ ግዥ ሊውል የሚችልበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በሚል ዘመቻ ተጠምዷል


ህወሓቶች በትጥቅ ትግሉ ወቅት የእርዳታ ገንዘብን ለመሳሪያ ግዥ አውለዋል በሚል ያጋለጠው በወቅቱ የቢቢሲ የአፍሪካ ዴስከ ኤዲተር የነበረው ማርቲን ፕላውት ማርቲን ዛሬ ደግሞ የእርዳታ ገንዘብ ለዚሁ ድርጅት መሳሪያ ግዥ ሊውል የሚችልበት ሁኔታ ካልተፈጠረ በሚል ዘመቻ ላይ መጠመዱን የሚለቃቸው መረጃዎች ያሳያሉ።

እ ኤ አ 1984 እስከ 85 በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች ከምዕራባዊያን የተሰበሰበውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለተጎጂዎች ከማድረስ ይልቅ በወቅቱ የነበሩት የህወሓት አመራሮች ለጦር መሳሪያ ግዥ ማዋላቸውን ማርቲን ፕላውት በወቅቱ በሰራው ዘገባ አጋልጧል።

የህውሓት አመራር የነበሩ ግለሰብ ለማርቲን ፕላውት፤ “ገንዘቡን የምናገኘው ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመደራደርና እንደነጋዴ በመቅረብ ነበር” ብለው እንደነገሩት በዘገባው ላይ ገልጿል።

ገንዘቡንም በጊዜው የነበረውን መንግስት ለመጣል ተጠቅምንበታል ማለታቸውን የጠቀሰው ማርቲን ፕላውት፤ ከምራባዊያንና ከእርዳታ ድርጅቶች የተሰበሰበውን 95 ሚሊየን ዶላር በቀጥታ ለመሳሪያ ግዥ እንዳዋሉት በዘገባው አጋልጧል።

በጊዜው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ከፍተኛ ቢሆንም አብዛኛው እርዳታውን ለሚፈልገው ህዝብ በትክክል አለመድረሱንም ገልጿል፤

ዛሬ ደግሞ ይህ ግለሰብ ለዚሁ ድርጅት (ህወሓት) አክቲቪስት በመሆን የፈጠራ ወሬ በማሰራጨት ሳይገታ፤ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ያለፍተሻና እጀባ ርድታ ይስጡ በሚል ዘመቻ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።

ይህ አክቲቪስት በየእለቱ በትዊተር ገጹ ላይ የሚያወጣቸው መረጃዎች ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ከማሳሳቱም በላይ ከአመታት በፊት ይሄው ድርጅት የእርዳታ ገንዘብን ለመሳሪያ ግዥ እንዳዋለው እያወቀ፤ ዛሬ ደግሞ ከዚህ አቋሙ በተቃራኒ እርዳታው ለዚሁ ድርጅት መሳሪያ ግዥ ሊውል የሚችልበት ሁኔታ ካልተመቻቻ ሲል እየተሟገተ እንደሚገኝ የሚለቃቸው መረጃዎች ያሳያሉ። (ኢ ፕ ድ)

ማርቲን ፕላዉት ህወሓትን ያጋለጠበት ዘገባ ከስር ተያይዟል
http://news.bbc.co.uk/2/hi/8535189.stm

Exit mobile version