ማርቲን ፕላውት የጠ/ሚ አብይን የጦር ሜዳ ምስል ከ360 ጋር ተናቦ ለምን ጠየቀ “ዜጎች ፎቶ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ”

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ጦርሜዳ መዝመት የታሰበውን የሚዲያ ዘመቻ ማበላሸቱን ተከትሎ “ነጭ ወያኔ” የሚባለው እንግሊዛዊው ማርቲን ፕላውት በቲውተር ገጹ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ያያችሁ” ሲሉ ለስላሳ ነገር ግን በመርዝ የተለወሰ ጣያቄ አቀርቧል። ሃብታሙና ኤርሚያስ የሚተነትኑበት 360 ከማርቲን ፕላውት መርዛማ ጥያቄ ጋር የተናበበ የሚመልስ ጥያቄ ማቅረባቸው ዜጎችን አሳዝኗል።

የሚዲያ ሴራና የፈጠራ ሪፖርት እንዴት እንደሚከናወን ሲያስለጥን በይፋ በቪዲዮ የተጋለጠው ማርቲን ፕላውት ” ከጦር ሜዳ የተነሳ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፎቶ ያላችሁ” ካለ በሁዋላ አለሳልሶ ” እስካሁን ምንም ማየት አልቻልኩም” ሲል በቲውተር ገጹ አራብቷል።

ኢትዮጵያን የተመለከተ አፍራሽ መረጃ በማሰራጨት ከተጠመዱትና “ይከፈላቸዋል” ከሚባሉት የትህነግ ቅምጥ ነጭ ካድሬዎች መካከል አንዱና ዋናው ማርቲን ፕላውት መሆኑንን የሚገልጹ ወገኖች እንዳሉት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የጦር ሜዳ አድራሻ ለማወቅ ያቀረበውን ጥያቄ መርዛማ በመሆኑ የሚዲያ ሰዎች፣ ማናቸውም አካላት፣ የመንግስት ሰዎች ሳይቀሩ ፎቶ ከማሰራጨት ሊቆጠቡ ይገባል። ፎቶ ማንሳትና መረጃ ማሰራጨት ላይ ታላቅ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ መክረዋል።

በፎቶ በሚገኝ መረጃ በሚሰራ የአቅጣጫ ሂሳብ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ቴክኖሎጂው ያላቸው ጣልቃ ገቦች መርዛቸውን ሊረጩ እንደሚችሉ ያመለከቱት ወገኖች 360 በዛሬው የተለመደ የውግዘት ዝግጅቱ ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትኛው ግንባር ናቸው? ሊነገረንና ልናውቅ ይገባል” ሲሉ ተደምጠዋል።

360 ዎች ማርቲን ፕላውት ካነሳው ጥያቄ ጋር በሰዓት ልዩነት ያቀረቡት ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት ናቸው” ጥያቄ እልህና ቁጭት የገቡ ” የቤት ጉዳ አንኳን እንደዚህ አይተየቅም። ማርቲን ፕላውት መረጃ ፍለጋ ያቀረበው መርዛማ ጥያቄ ሲገርመን በተናበበ መልኩ 360 ላይ ሃብታሙና ኤርሚያስ እየተቀባበሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት ግንባር ናቸው ሲሊ መጠየቃቸው እየሄዱ ያለበትን የክህደት መተን የሚያሳይ ነው። ሕዝብ ይህን ሊረዳና ሊያከሽፍ ይገባል” ሲሉ አስተአየታቸውን ሰጥተዋል።

በግልጽ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሚደገፉና የመንግስትን ” አልላላክም” አቋም ሲቃወሙ የከረሙት የ360 አዝማቾች ሃብታሙና ኤርሚያስ ዛሬ አብይ አሕመድ ” የት ናቸው፤ ይነገረን” ማለታቸውን ሕዝብ ሁሉ ልብ እንዲልና እንዲመዘግበው ሲሉ እነዚሁ ክፍሎች አሳስበዋል።

See also  በአማራ ክልል ኮማንድ ፓስቶች የማጽዳት ስራ መጀመራቸው ይፋ ሆነ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ረብሻው እየተቀዛቀዘ ነው

ዘመቻውን አስመልክቶ ” ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ፡፡ የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ፡፡ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ” ሲሉ በደፈናው የስራ ክፍፍል መደረጉንና ሁሉም ነገር ታስቦበት የተደረገ መሆኑንን በግልጽ ተናግረው ሳለ ” አገር የሚመራው ማን ነው?” ሲሉ ለመሳለቅ የሞከሩት 360ዎች፣ ” ሁሉም ነገር ተዘጋግቷል። ተደፋፍኗል” ሲሉ አምርረው መናገራቸው የጤና እንዳልሆነ አስተያተ የሰጡ ወገኖች አመልክተዋል። ሕዝብም ሆነ አመራሩ ” ለምን” ሲል የማርቲን ፕላውትንም ሆነ የእነ ኤርሚያስና ሃብታሙን በመርዝ የተለወሰ ጥያቄ በጥንቃቄ እንዲመረመሩ በድጋሚ አሳስበዋል።

ማርቲን ፕላውትና 360ዎች አብይ አሕመድ የሚገኙበትን ግንባር ፎቶ ጠየቁ፤ ለምን? “ዜጎች ፎቶ ለማሰራጨት እንዲቆጠቡ” ሲሉም ደግመው ደጋግመው አስተንቅቀዋል። ማህበራዊ ሚዲያው የጎጥ አስተሳሰቡ በተጠናወታቸውና በሚከፈላቸው አስመሳዮች የታጨቀ በመሆኑ በርካታ ጉዳዮች እንዲበላሹ አስተዋጾ ማድረጉን በማስታወስ ሕዝብ ከጦር ሜዳ በሚወጡ መረጃዎች ዙሪያ ጥንቃቄ የማያደርጉትን እንዲከላከል፣ መንግስትም እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅረበዋል። ዛሬ ፉከራ ሳይሆን ተግባር የሚያስፈልገበት ወቅት በመሆኑ የአገር አለኝታ የሆኑትን የመከላከያ ሰራዊታና የልዩ ሃይላት እንዲሁም በየአደረጃጀቱ ላሉት ሁሉ በሚታወቅ አግባብ ድጋፍ ከመስጠት በዘለለ አላስፈላጊ ጉዳዮች ውስጥ ላለመግባት ከወዲሁ ሁሉም ዝግጅት እንዲያደርግ ተማጽነዋል። ማርቲን ፕላውትም ሆነ 360 መረጃ መዘጋጋቱ እንዳስጨነቃቸው መረዳት አስፈላጊ እንደሆነም አመልክተዋል።

See also  በ30 ቢሊዮን ብር ወጪ 3 የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው ለባለሃብቶች ክፍት ሆኑ

Leave a Reply