Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ አዲስ አበባና አስመራን እንደሚያጠቃ አስፈራራ፤ “ሲረጋጋ 100 ዓመት ወደሁዋላ መመለሱን ይረዳል”

መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ በድንገት ሃይሉን ካስወጣ በሁዋላ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) መቐለ ከተማን እንደተቆጣጠር አስታውቋል። የቀድሞ የኢንሳ ሃላፊ የነበሩት ሜ/ጄኔራል ተኽለብርሃን ቀደም ብለው ከገቡት ሃላፊዎች አንዱ መሆናቸውም ተሰምቷል። ይህ ከሆነ በሁዋላ አዲስ አበባ እና በአጎራባች የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ሊያጠቃ እንደሚችል ይፋ ሆኗል። ማስፈራሪያውን ትህንገ መቶ ዓመት ወደ ሁዋላ ተመልሷል ሲሉ ዜናውን የሰሙ መልስ ሰጥተዋል።

በኅዳር ወር በሶስት ሳምንት ኦፕሬሽን ፈራርሶ ወደ ዋሻ የገባው የትህነግ ሃይል የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ማፈግፈጉን ተለትሎ ወደ መቀለ ቢገባም፣ የኢትዮጵያን ሰራዊት እንዳሸነፈ አመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” አንድ ቦታ ላይ ህዝቡ መከላከያ ገብቶ ይጠብቀን ብሎ ጥሪ አቅርቦ መከላከያ በቦታው ከገባ በኋላ ሁኔታውን ለማስተካከል የተወሰኑ ወታደሮችን በቦታው አስቀምጦ ወደሌላ ስፍራ ለዘመቻ ሄደ። ነገር ግን ማታ ላይ በቦታው የቀረውን ወታደር ይጠብቀን ብሎ የጠራው ህዝብ መሳሪያም ገጀራም ይዞ ወጥቶ ጨፍጭፎታል” ሲሉ መከላከያን የሚወጋው ሕዝብ በመሆኑ እንዲለቅ የተደረገበትን አንድ ምክንያት ለሚዲያ ሰዎች ሲያስረዱ ገልጸዋል።

“የቀድሞው የትግራይ መንግስት” በሚል ራሱን የጠራው፣ መንግስት አሁን ድረስ ” አሸባሪ” የሚለው ትህነግ ከተማዋን መያዙን ባረጋገጠበት መግለጫ “ጠላቶቻችን ትግራይን ሙሉ በሙሉ ለቀው እስኪወጡ ድረስ ህዝባችንና የትግራይ ሰራዊት ትግላቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን” ብሏል። ይህንኑ ተከትሎ የአትላንቲክ ካውንስሏ የአፍሪካ አጥኚ ብራውኒ ብሩቶን አቶ ነዓምን ትህነግ ያወጀውን ጥሪ ተከትሎ ያሰራጩትን ስጋት እንደሚጋሩ ገልጸዋል።

ትህነግ ወደ ከተማ እንደገባ ለትግራይ የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመራና አስመራንም እንደሚያተቃ በይፋ አስታውቋል። ከአስመራ በኩል ለዚህ የተሰጠ ምላሽ ባይሰማም፣ ከኢትዮጵያ በኩል ግን ትህነግ ካሁን በሁዋላ ስጋት እንደማይሆን ነው እየተገለጸ ያለው። የአማራ ክልል ግን ” ጸቡ ከመላው የአማራ ጸብ ጋር ነው” ሲል አስጠንቅቆ ክልሉ አስፈላጊውን ዝግጅትና መከላከል ማድረጉን አመልክቷል። ሕዝቡም ልክ ለትግራይ ህዝብ እንደቀረበው ጥሪ ” ልብህን ጠብቅ” ትብሏል።

የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ለኤኤፍፒ እንደገለፁት የሰራዊቱ ሃይል የክልሉን ደህንነት ለመጠበቅ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን፣ አዲስ አበባን እና አስመራን መቆጣጠር ለመቆጣጠር የሚቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። አቶ ጌታቸው ይህን ሲሉ ጠያቂው ” አቅማችሁ ምን ያህል ነው? ኤርትራም ሆን የኢትዮጵያ መንግስት ዝም ይላል ወይ” በሚል የማጠናከሪያ ጥያቄ አላነሳባቸውም።

“የትግራይን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚወስደውን ሁሉ እናደርጋለን” ያሉት ቃል አቀባዩ፣ “ወደ አስመራ መሄድ ትግራይን ለማረጋጋት የሚጠቅም ከሆነ እናደርገዋለን” ብለዋል። አዲስ አበባ መጓዝና ማጥቃትም በተመሳሳይ ትግራይን ለማረጋጋት ለትግራይ ጥቅም ሲባል የሚወሰድ እርምጃ ነው። የመንግስት የተናጠል የተኩስ አቁም አዋጁን እንደ ቀልድ ቆጥረውታል።

የትህነግ ደጋፊ ከሆኑት አንዱ የተጋሩ የፓልቶክ አውድ ላይ ሙዚቃ በመክፈትና ደስታቸውን በመግለጽ በየመካከሉ በሚሰጡት አስተያየት ቀጣዩ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ መሆኑንን ደጋግመው ሲናገሩ ተሰምቷል። ኤርትራን መውረርና አሰብን መቆጣጠርም የጥቃቱ አካል እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር።

ይህ በሚሆንበት ወቅት ኢትዮጵያ በመከላከያ ሃይሏ ውስጥ ያለባትን የሜካናይዝድ ተዋጊዎች ችግር የሚቀርፉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለሙያዎች ያስመረቀች ሲሆን፣ በብር ሸለቆ ደግሞ የሽምቅ ተዋጊነት ልዩ ክህሎት የተካኑ መሆናቸው የተነገረላቸው በርካታ ሺህ ሃይል አስመርቃለች።

አሉላ የሚባለው የትህነግ ደጋፊና የሚዲያ ባልደረባ “የተኩስ አቁሙ ውሸት ነው። ኢትዮጵያ በድሬደዋ ከፍተኛ የውጊያ ልምምድ እያደረገች ነው” ሲል ከድሬደዋ የተላከለትን መረጃ በቲውተር ገጹ አስፍሯል።

አዲስ አበባንና አስመራን ለመያዝ ምንም የሚይዘው ሃይል እንደሌለ ያስታወቀው ትህነግ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት በተመሳሳይ “በኤርትራና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ታላቋን ትግራይ እንገነባለን” ሲል ይናገር እንደነበርና በመጨረሻም ምን እደሆነ የሚያስታውስ ሆኗል። ትህነግ መቶ ዓመት ወደ ሁዋላ መመለሱን ውሎ አድሮ ሲረዳ ወደ ልቡናው እንደሚመለስ ያነጋገርናቸው ገልጸዋል።

የመከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ ከመውጣቱ በፊት በቆላ ተንቤን መሳሪያ ተደብቆበት የነበረውን ምሽግ ማውደሙ፣ ከዛም በትግራይ ተከማችቶ የነበረውን ከባድ መሳሪያ ለቅሞ አስቀድሞ ማውጣቱና ዛሬ ላይ በትግራይ ከጎሬላ ተዋጊነት በመውጣት ለአገር አቋራጭ ውጊያ የሚሆን አቅም እንደሌለ መንግስት ” ምንም ስጋት የለም፤ ጸድቷል” ሲል አመልክቷል።

በተመሳሳይ የአማራ ክልል በክፍተኛ ደረጃ ራሱን ያስታጠቀና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተናቦ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ስጋት እንደሌለ ለዝግጅቱ ቅርብ የሆኑ እየጻፉ ነው። ትህነግ እንደ ከዚህ ቀደሙ በጦርነት ኢትዮጵያን ለማትቃት ወርቃማ እድል እንደሌለው የሚያስታውቁ እንዳሉት አዲስ አበባና አስመራን ስለመያዝ የሚነገረው የዓለምን ትኩረት ለመሳብና የመደራደሪያ ጫና ለመፍጠር ነው።

በተመሳሳይ ዜና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለተኩስ አቁሙ እርምጃ ድጋፍ እየሰጡ ሲሆን አሜሪካ ውሳኔውን አወድሳ ያቀረበችው ስፍር ቁጥር የሌለው ጥያቄና ማሳሰቢያ ሌላ ህልም እንዳላት የሚያሳይ መሆኑ ተመልከተ። መከለከያ መቀለን ለቆ እስኪወጣ ስልክ ይሰራ እንደነበር እየታወቀና ራሳቸው ስልኩን እንደቆረጡት ነዋሪዎችን ጠቅሰው የዘገቡ እያሉ አሜሪካ አሁን መንግስት ላይ ሁሉንም እየደፈደፈች መሆኑ የተለመደ ህገወጥነት መሆኑም ተመልክቷል። ኢትዮጵያዊያን ከዳር እስከዳር እየሆነውን ማስተዋል ካልቻሉ አሜሪካ እየደገሰች ያለው ድግስ በቀላሉ የሚታለፍ አይሆንም።

በሌላ የትግራይ ዜና ” የከዳችሁን እናንት ናችሁ” በሚል አካባቢ እየተለየ ቅታት መጀመሩ፣ በዚህም ቁጥራቸው በውል የማይታውቅ ሰዎች መገደላቸው በአካባቢው ሰዎች እየተነገረ ነው። አምነስቲ ስጋቱን ገልጿል። ከተማዋ ሌብነት አስቸጋሪ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

Exit mobile version