Site icon ETHIO12.COM

ተከዜ – አዲሱ የትህነግ የድንጋይ ዘመን ዕቅድ – ኦቻ የአማራ ልዩ ሃይልን ወነጀለ

የትህነግን ቀጣይ ዕቅድ ለመረዳት ተከፋይ ቁንጮ የቲውተር ፊት አውራሪዎቹን ውትወታና እነሱኑ ተከትለው በመናበብ የሚሰራጩ ዜናዎችን መመርመር፤ ከዛም ጌቶቻቸው የሚያወጡትን በመርዝ የተለወሰ መግለጫ መገምገም በቂ ነው። ሲያልፍ ደግሞ በተለያዩ አውዶች የሚቀርቡትን ሽለላዎችና ማንቂያዎች ማየት የትህነግን አሳብ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

“ነጩ ወያኔ” የሚባለው ማርቲን ፕላውት “ህወሓቶች በትጥቅ ትግሉ ወቅት የእርዳታ ገንዘብን ለመሳሪያ ግዥ አውለዋል” በሚል ያጋለጠው የወቅቱ የቢቢሲ የአፍሪካ ዴስከ ኤዲተር ነበር። በጡረታ ዘመኑ ሙያዊ ሃላፊነቱንና እውነታን አሽቀንጥሮ የትህነግ የቅስቀሳና የሃሰት ዜና አደረጃጀት አሰልጣኝ፣ አምራችና አከፋፋይ የሆነው ፕላውት አይኑንን በጨው አጥቦ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ያለፍተሻና ቁጥጥር በነጻነት ወደ ትግራይ ይንሸራሸሩ በሚል ዘመቻ ላይ ተጠምዷል።

ከህግ ማስከበሩ ስራ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ላይ በሚገርም አንድነትና ጥምረት ዘመቻ የከፈቱት ታላላቅ የሚባሉት አገሮችም መንግት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም አድነቀው በነካ አፋቸውና ደብዳቤያቸው የሚያነሱት ነገር ቢኖር ” ውሳኔው እርዳታ ለማስገባት አመቺ ሁኔታ የሚፈጥር ከሆነ …” በሚል ድብቅ አጀንዳቸውን እያንቀረቀቡ ነው።

የቲውተር ፊት አውራሪው ነጩ ወያኔ ማርቲን ፕላውት ” የሃሰት ዜና መፍጠር ግድ ነው” በሚል እንዴት የሃሰት ዜና እንደሚመረት የሚያስተምርበት ቪዲዮ ይፋ እንዳሳበቀው በምን ያህል ክፍያ እንደሚሰራ ድብቅ ከመሆኑ በቀር ሰውየው የትህነግ አጀንዳ ተካይ ነው። ተከዜ ድልድዩ መውደሙ ሲሰማ የአገራቱ መግለጫዎች፣ የእሱ የቀደመ ” የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ያለፍተሻና ቁጥጥር በነጻነት ወደ ትግራይ ይንሸራሸሩ” ዘመቻ ገሃዱን አጉልቶ ያሳያል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ እንዳስታወቀው የሽብር ቡድኑ ድልድዩን ያፈረሰው ወደ ክልሉ የሚወስደውን የእርዳታ መስመር ለመገደብ መሆኑንን ይፋ ማድረጉ፣ እንደተቋም መንግስት ተናገረው ለማለት እንጂ ለሌላ አዲስ ዜና አይደለም። ምክንያቱም መንግስት ወደ ትግራይ የሚገባውን እርዳታ ለመቆጣጠርና በአንድ ቀጭን መስመር እየበረበረ ለማስገባት አመቺውን መንገድ መጠበቅ እንጂ ሌላ ተግባር ሊፈጽም አይችልምና።

ይህ ብቻ አይደለም የተከዜ ድልድይ መውደሙ እንደተሰማ በቅጽበት ሮይተርስ የዓለም የምግብ ድርጅት ቃል አቀባይ ፒተር ስሜርደን ጠቅሶ የዕርዳታውን አቅርቦት ከበፊቱ በበለጠ እንደሚያደናቅፈው ዘግቧል። በዚሁ ዘገባ ፒተር ስሜርደን የድልድዩ መፍረስ በዕርዳታ አቅርቦቱ ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ እየተጠና እንደሆነና ከጎንደር ሽሬ ወደ ሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአስቸኳይ የሚፈለግ የምግብ አቅርቦት ለማድረስም አማራጭ መንገድ እንዳለም እያጠኑ መሆኑ ተመልክቷል።

ሮይተርስ የቃል አቀባያዋን ” ስጋት” ተንተርሶ 900 ሺህ የትግራይ ነዋሪዎች በከፍተኛ ረሃብ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን ደጋግሞ እያስታወሰ ዜናውን ሲዘጋ ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ነጻ መስመር የማይታሰብ መሆኑንን ደጋግማ ማስታወቋን ሮይተርስ ረስቶታል። ከዛም በላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” በዛን ዘመን አስተሳሰብ ላይ የተተከሉ” ሲሉ ትህነግ በረሃብ ስም በሱዳን በር ተከፍቶለት ነብስ መዝራቱን በማስታወስ ያንን ዛሬ እደግማለሁ ብሎ ማሰብ ቅዠት እንደሆነ ይፋ መናጋራቸውንም ሮይተርስ ለዘገባው አስፈላጊ ሆኖ አላገኘውም።

እንደ ዛሬ አይኑ ሳይንሸዋረር ለዕርዳታ የገባ ዕህል እየተቸበቸበ ለመሳሪያ ግዥ መዋሉን በጥሩ መረማሪ ጋዜጠኛ ክብር ያጋለጠው ማርቲን ፕላውት፣ ሕዝብን በማስራብ ምን እንደተሰራ ታሪኩን ሁሉ እያወቀ፣ ዛሬ ነጻ ኮሪዶር እንዲከፈትና ትህነግ በሱዳን መውጪ አግኝቶ ዳግም በመሳሪያና የጦር ሎጂስቲክ እንዲበለጽግ እየወተወተ ነው። ዘመቻው በመናበብ የሚካሄድ በመሆኑ የሚታወቁት አገራትም አብረው በዚሁ ዘመቻ ኢትዮጵያ ላይ እይሰገሩ ነው።


ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!

ለጠ/ሚ/ሩ መጥፎ ዜና የሚሆነው የሚያደርጓቸው ጥረቶች የሚያመጡት ውጤት አናሳ የመሆኑ ጉዳይ ነው። ምክንቱም ህወሓት 6ሚሊዮንና አናሳ የሆነውን የትግራይ ተወላጅ የሚወክል ድርጅት ቢሆንም ለ27 ዓመታት በሥልጣን ላይ በቆየባቸው አምባገነናዊ ዓመታት ከሌሎች ክልሎች ጋር የፈጠረውና ሥር የሰደደ ጥቅማዊ ወዳጅነት እንዲሁም ከ61 ጄኔራሎች መካከል 57ቱ የትግራይ ተወላጅ መሆናቸው የኢትዮጵያ ድንበር ጠባቂ ኦፊሰሮች ሁለት ሦስተኛው እንዲሁ ትግሬዎች ከመሆናቸው ጋር ተዳምሮ የዓቢይን ሥራ ቀላል እንዳይሆን ከሚያደርጉት ዋንኞቹ ናቸው።


ከላይ በተባለው መረጃ መሰረት ቀጣዩ ፈተና ” በሱዳን በኩል ነጻ መስመር ክፈቱና ትህነግ በመሳሪያ ይደራጅ፤ ረሃብን መሳሪያ አድርጎ የ1997 ታሪክን ይድገም” የሚለው ጫና ነው። ይህን መፍቀድ ለትህነግ በር እንዲከፈት ያላትን አቅምና ግንኙነት በሙሉ እየተጠቀመች ያለችው የፈርዖን መንፈሷ ግብጽ ደርድራ የምትጠብቀውን መሳሪያ ወደ ትግራይ አስገብቶ ሌላ የመከራ ዓመታትን ለማስተናገድ መስማማት እንደማለት ነው።

የትህነግ በመሳሪያ ማበጥና ዳግም መደራጀት ለኤርትራ ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ በዝምታ አታየውም። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአማራም ተለይቶ ካራ እየተሳለበት ባለው የአካባቢው ሕዝብ ላይ እልቂት ማወጅ ነው። እናም የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች አስቸኳይ መፍቴ ለመጠት ምን ይደረግ? አሁን አሁን የሚባለው ያለው አሰብ ወደብን መጠቀም ከዕርዳታው ጋር ሊገባ የሚችለውን መሳሪያም ሆነ ሌሎች ጉዳዮች ለመቆጣጠር አመቺ እንደሆነ የሚናገሩ አሉ። አለያም በጅቡቲ በአፋር በኩል!! ሌላው ሃሳብ በሙሉ የማይሆንና ተቀባይነት የሌለው ነው።

መንግስት በዚህ አቋሙ የሚደራደር አይሆንም። ጫና ፈጣሪዎቹ አውሮፕላን ለመጠቀም ማቀዳቸው እየተጠቆመ ነው። ይህ በቀጥታ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማወጅ በመሆኑ አይሆንም። አይሆንም ማለት ብቻ ሳይሆን የሚሆንም ከሆነ በጥብቅ ፍተሻ እንጂ ባለፉት ጊዚያት እንደታየው ” አትፈትሹን፣ አያጅቡን፣ ሪፖርት አትጠይቁን” በሚለው የርዳታ አሰጣጥ አካሄድ ሊሆን እንደማይገባ መንግስት አማራጭ አሳቦችን ማዘጋጀቱ ተሰምቷል።

ቢቢሲ ይህ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (ኦቻ) ጠቅሶ ጎንደርና ሽሬን የሚያገኛው የተከዜ ድልድይ ሰኔ 25/2013 በአማራ ልዩ ኃይል ከጥቅም ውጭ እንዲሆን እንደተደረገ የሚጠቁም መረጃ ደርሶኛል ማለቱን አስነብቧል።

በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢንተርኔትና ቴሌኮሚዩኔኬሽን አቅርቦት መስተጓጎሉ ላይ ከድልድዩ መፍረስ ጋር ተዳምሮ የእርዳታ አቅርቦቱን አስቸጋሪ እንደሚያደርገው ተመልክቷል።

” ከወራት በፊት ጌታቸው ረዳ የአማራ ሕዝብ መሰረተ ልማቶችን እንደሚያጠቁ ተናግሮ ነበር። እናጠቃለን ካሏቸው መሰረተ ልማቶች መካከል በተደጋጋሚ የጠቀሰው ታላላቅ ድልድዮችን ነው። ከባሕርዳርና ጎንደር ከተማ ውጭ ያሉ የአማራ ሕዝብ መሰረተ ልማቶችን እናጠቃለን ባሉት መሰረት እፎይታ ሲያገኙ በቅርብ ያገኙትን የተከዜ ድልድይ አጥቅተዋል” ሲል ዘሀበሻ ዛቻቸውን ያሰሙበትን የቪዲዮ ማስረጃ አያይዞ ይፋ አድርጓል።

አስቀድሞ የተሰጡና የተገለጹ መረጃዎች መኖራቸው ቢታወቅም በጉዳዩ የሚዘግቡ ሚዲያዎች ሲጠቀሙባቸው አይታየም። ከወራት በፊት ድልድይ እንደሚያፈርሱ፣ በቪዲዮው እንደሚሰማው የተመረጡ ቦታዎችን በመላው አገሪቱ እንደሚያጠቁ ያስታወቁት አቶ ጌታቸው ይህን ማለታቸውን ጠቅሶም የጠየቃቸው አንድም የመገናኛ አውታር ይህ እስከታተመ ድረስ የለም።

Exit mobile version