Site icon ETHIO12.COM

ውጊያው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው – ያለ አንዳች መደባበቅ የሆነው ይህ ነው

1981 እ.አ.አ የሁለተኛው አብዮታዊ ጦር ሽሬ ላይ ሲመታ ቃል በቃል የተነገረው ” የሽሬን ሕዝብ የሚያምነውን ሰራዊት ተጠራርተው ተረባረቡበት። ወታደሮቹ በጠመንጃ፣ ህዝቡ በገጀራ … ” ከዛ የሆነውን ማስታወሱ አይከብድም። ካሃጂ ጀነራሎችና ቀደመው ውጭ የወጡ ባንዳዎች ከኢትዮጵያ ገዳዮች ጋር ተባብረው የክህደት ግዳጃቸውን ፈጸሙ። ከጦርነቱ በሁዋላ የተጻፉ የምስክርነት መጽሃፎች በግልጽ ብለውታል። አልመለስበትም።

ዛሬም ታሪክ ራሱን ነው የደገመው። ዘመቻ አሉላ አባነጋ ብለው የትህነግ ሃይሎች ሲያውጁ፣ በነበረው ቁማርተኛ ጊዜያዊ የትግራይ አስተዳደር፣ ከዳር እስከዳር ነቅሎ የገባው የነጮች እርድታ ሰጪ በመደጋገፍ በረሃ ላለው ሃይል ስንቅ፣ ትጥቅ፣ መድሃኒትና ከሁሉም በላይ የመገናኛ መሳሪያ ያመቻቹ ነበር። ወጣቶች ወደ በረሃ እንዲወርዱ ቀስቅቃሽ ድራማዎች እየተሰሩ ያለ ፍተሻ በርዳታ ስም በነጻነት ያግዙዋቸው ነበር። በቅስቀሳ ጫካ የወረዱ ሕጻናት ሰልጥነው ወደ ከተማ እየተመለሱ ቤተሰቦቻቸው ጋር ሲገቡ እናውቅ ነበር። ለመቆጣጠር ስንፈልግ ዓለም ሲቪል ተነካ እያለ መንግስትን ያዋክባል። ዝም ስንል በየቀኑ ይገሉናል። ውሃ ውስጥ መርዝ ጨምርው ጨርሰውናል። ጋቢና ነጠላ እያወለቁ ለሰላም እየለመኑ አሳርደውናል።

የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጫካ ካለው ሃይል ጋር ይሰሩ ነበር። በዚህ አካሄድ ቅስቀሳው፣ የውጭ ተከፋይ ሚዲያዎች ዘመቻ፣ ጠርቶ ያለወጣው የባንዳዎች ትብብር፣ የሃያላኖቹ ማስጠንቀቂያና ቅጥ ያጣ ጫና ተዳምረው ትህነግ እንዳሸነፈ እየተነገረን ነው። ባንዳ ተንተኞችም መንግስትን ያሳጡ እየመሰላቸው ትህነግን ለማንገስ መከላከያ ሰራዊት ላይ ዳግም ክህደት እየፈጸሙ ነው። ኢትዮጵያ እንዳትነድ ከወዲያ ወዲህ እየተወረወረ ያቆየ ሰራዊት ላይ ከጠላት ባልተናነሰ ቁስሉን እየወጉት ነው። በሌለ መረጃ ጫፍ ይዘው እየዘላበዱ ሰድበው ለተሳዳቢ እየሰጡን ነው። እንዲህ የሚያደርጉት ሁሉ ታሪክ የማይረሳው ሃፍረት እየፈጸሙ እንደሆነ ሊያውቁት ይገባል።

ምንድን ሆነ

በትክክል የሆነውን ለመዘርዘር አቅም የለኝም። ግን ባጭሩ የሆነው የጉንዳን ታሪክ ነው። ጉንዳን የወረረው ሰው መላ ሰውነቱን ሲነከስ አንድ በአንድ ለቀማ አይጀምርም። በጁ የያዘውን ሁሉ ጥሎ ልብሱን አወላልቆ እርቃኑንን ይሆናል። ከቻለ ልብሱን አራግፎ መልሶ ይለብሳል። ትግራይ በመቀለ መቶ ኪሎ ሜትር ራዲየስ የሆነው ይህ ነው። በተመሳሳይ ሰዓት ህዝብ ወረረን። ተረባረቡብን። ሲቪል መስለው ቁጭ ያሉ እንደ አስከሬን የቀበሩትን መሳሪያ፣ ስለትም ያለው ስለት ይዞ ወጣ። በቃ አንዳች ሊታመን ያማይችል የጦርነት ህግና ሳይንስ ሊያስተናግደው የማይችል የድንጋይ ዘመን ጉዳይ ሆነ።

በንድ ግዳይ ላይ እንደሚረባረብ አውሬ በየስፍራው ተረባረቡብን። ይህ የወታደር ሳይንስ እውቀት አይደለም። ሲነዛ የነበረውና የጊዜያዊ አሰተዳደሩ ሳይቀር ሲደግፈው የነበረው ፕሮፓጋንዳ፣ እንዲሁም በውል የማይታወቀው ኢትዮጵያን ጥላቻ ነው። እናም ምን እንሁን? 10 ሺህ ሰራዊት በሚሊዮን የሚቆጠር፣ ” እራበን እያለ” ዓለምን ከሚያስት ህዝብ መካከል ምን ሊያደርግ ይችላል? ወገን መረዳት ያለበት ይህን ነው።

በየትኛውም የፊት ለፊት ውጊያ አልተረታንም። ልዩ ኦፕሬሽን እንዳደረጉና ምጡቅ አዕምሮ እንዳላቸው ተደርጎ የሚወራው ለምን ዓላማ እንደሆነ ማገናዘብ ያስፈልጋል። በነበረው ውጊያ ታክቲክ ብሎ ነገር የለም። ክፉ ፕሮፓጋንዳ ሲጋት የኖረ ሕዝብ ያለውን ይዞ እንዲቦጫጭቀን አሴሩ። ኢትዮጵያ ሂሊኮፕተርና ጀት አላት። ሚሳይላና ሰፊ ቦታ የሚሸፍን መሳሪያ አላት ግን አልተጠቀመችም።

ያለ አንዳች መዋሸት የምናገረው ነገር ቢኖር ከየመንደሩ፣ ከየስርቻው፣ ከየቤተክርስቲያኑ እየወጡ ሲረባረቡብን አብዛኛው ጦር ማመን አልቻለም። ይህን ከማይ ብሎ ራሱን ያጠፋ ብዙ ነው። ቢጽፉትና ቢናገሩት አያልቅም። እስከሚገባኝ እዛና እዚህ ያለው ጉዳይ አብቅቷል። የሶማሌ ክልል መሪ ሙስጣፌ ” እየጠሉን የገዙን” ሲል የነገረን ትክክል ነው።

መልዕክቴ

ካሁን በሁዋላ ሰራዊታችን ደጀን አለው። ጨዋታው የተገላቢጦሽ ነው። ይህ አራጅ ቡድን ከነጭፍራው ከክልሉ ቢወጣ እኛ ላይ እንደሆነው ደጀናችን ይመክተዋል። እንደ ድሮ በጎንደር በጎጃምና በደሴ መጋለብ አይቻልም። ከክልላቸው ወጥተው ጥቃት ካሰቡ ሲቪል ለብሰው አይዋጉም። ጋቢ አንጥፈው አያታልሉም። ጸሎት ቤቶችን ምሽግ አያደርጉም። በየመንደሩ አይወተፉም። እናም ኢትዮጵያ በጀት፣ በሄሊኮፕተር፣ በላት ከባድ መሳሪያ ሁኔታውን እያየች ትጠቀማለች። ስለዚ ደጀን መስለው እንደተረባረቡብን አይነት ውጊያ አይታሰብምና ወገን አትስጋ።

በግል ካሁን በሁዋላ እንኳን በውትድርና በማናቸውም ዓይነት አገልግሎት ወደ ትግራይ አላቀናም። አምላክ ክንፍ ቀጥሎልኝ ለሃዋሪያዊ አገልግሎት እንኳን ቢልከኝ አላደርገውም። እኔ ብቻ ሳልሆን ዘር ማንዘሬ ይህን እንዳያደርግ በገሃድ እናገራለሁ። ሕዝብ አልጠላም። ግን በግል በቅቶኛል። ሁለት አስርት ዓመት ስንጠብቃቸው ኖረን አረዱን። ጨፈጨፉን። በመኪና ሄዱብን። ሁሉን ችለን በየዋህነት ተመልሰን እስራቸው ገባን። ጅሎች ነበርንና ዳግም እንደ ጉንዳን ወረው ተረባረቡብን። ቀን ሲደርስ ዝርዝር እጽፋለሁ። ባለፈው ስርዓት በ1981 እ አ አ የሆነው ተደገመ። ነገሩ ያበቃው ያዛኔ መሆን ሲገባው በኔ እድሜ በገሃድ ሶስቴ ታረድን። ጠላት አድርገው በተኑንን። ኦሮሞ አማራ ጉራጌ ሳይመርጡ በሉን።

አሁን መጽሓፉ ” ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው” እንዳለው ሰልፉ የሕዝብ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። የሆነብን ሁሉ እንዲሁ በቀላሉ የሚረሳ አይደለም። በየሚዲያው ይህን አስመልክታችሁ የምታወሩ ደጋግማችሁ አስቡ። መከላከያ የአገር ክብር ነው። መንግስትን ያጠለሹ እየመሰላቸው አፋቸውን በሰራዊቱ ላይ የሚጠርጉትን ሕዝብ ይዋጋ። በዚህ ጉዳይ ዝምታ አያዋጣም። ችግር ቢኖርም እንኳን ጥቆማው እጅግ አግባብነት ባለውና በጥንቃቄ ሊሆን ይገባል።

ኢትዮጵያ ከሁሉም በላይ ናት። ከሁሉም በላይ የምትሆነው ሁሉም ለበጎ ሲባል ዘብ ሲቆም ነው። ሁሉም ዘብ ያልቆመላት አገር አደጋዋ ብዙ ነው። መከላከያ ከፊት የሚመራ ቢሆንም ሁሉም ዜጋ ድርሻውን መወጣት አለበት። ሕዝብ ለመከላከያ ሰራዊት ያለው ክብርና ድጋፍ ለአፍታም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ባይሆንም፣ አንዳንድ አዋቂ ነን ባዮችን አደብ ማስገዛት እንደሚያስፍለግ ለመግለጽ እወዳለሁ።

በመጨረሻ

መከላከያ የራሱ የሕዝብ ግንኙነት እያለውና ማናቸውንም ጉዳይ በአግባቡ በበቂ ወታደራዊ እውቀት ለሕዝብ ማብራራት እየቻለ በየስርቻው ወሬ ሰማን፣ እገሌ ነገረን በሚል የሚነዛው አፍራሽ የወሬ ናዳ ባስቸኳይ እንዲቆም ይህንን የምታነቡ አለቆቼ መመሪያ እንድትሰጡ ጥሪ አቀርባለሁ። ማንኛውም ከፍተኛ መኮንን መረጃ ከመስጠትና ጥቆማ ከማቀበል በህግ እንዲታቀቡ እንዲደረግ እማጸናለሁ። ማንኛውም ሚዲያም ሆነ ግለሰብ የሚፈልገውን መረጃ ለዚሁ ተጋብር በተቋቋመ የህዝብ ግንኙነት መመሪያ በኩል እንዲያከናውን ሳይውል ሳያድር መመሪያ እንዲሰጥ እለምናለሁ።

ከዚህ ውጭ የመከለካያን ከፍተኛ መሪዎች ለማስታወቂያነት መጠቀም እጅግ አግባብነት የጎደለውና ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ ሁሉ ራሳቸውን በሃላፊነት እንዲያርቁ አደራ እላቸዋለሁ። ለአገራቸው ካላቸው ቀናኢነት እንደሚያደርጉት ቢያስቡም በጣናት ያልተደገፈ ፕሮፓጋንዳ ወደ ራስ ይዞራል፣ ለሌሎች ቅስቀሳም ያመቻቻልና እናስብ። ትግራይም አገር ልሁን ካለች በውል፣ በህግ እዛና እዚህ መርገጥ ሳይኖር የድንጋይ ችግር የለምና ግንብ እንዲገነቡ አድርገን እንለያይ!! ሁሉም ዜጋ በዚህ መልኩ ይርዳቸው። ተነጋግሮ ችግሩን የሚፈታ ስልጡን ትወልድ እስኪመጣ ድረስ!!

የመከላከያ መካከለና ደርጃ መኮንን ነኝ

ዝግጅት ክፍሉ

ይህን ማስታወሻ አዘጋጅተው የላኩልን የመከላከያ ደረጃ መኮንን የሆኑ የአገር መከላከያ አባል ናቸው። ሃሳብና ጥያቄ ካልቹህ እንዳረሳለን። ዋናው ዓላማቸው ይህን መረጃ የሚያዩ እርምት እንዲወስዱና ሌሎች ባደረጉት መልኩ ሳይሆን ቀና የአገራቸው መከላከያ ደጀን እንዲሆን ከስታወቁን በሁዋላ ነው። ሃሳቡ ዝግጅት ክፍሉን አይወክልም።

Exit mobile version