Site icon ETHIO12.COM

በራያ አዘቦ ሕዝብ አደጋ ላይ ነው፤ መገደላቸውንና 30 ሺህ መፈናቀላቸውን ፓርቲው ይፋ አደረገ

የራያ አዘቦ ህዝብ በአሸባሪው ሕወሃት ዋጋ እየከፈለ መሆኑን የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።የአገር መከላከያ ሰራዊት ትግራይን ለቆ ከወጣ ጀምሮ የራያ አዘቦ ተወላጆች የሆኑ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንም ፓርቲው አስታውቋል።

በተጨማሪም ከ30 ሺህ በላይ ከአካባቢያቸው ተሰደዋል።የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የወጣቶች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጥጋቡ ጎበና እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የራያ አዘቦ መኾኒ ከንቲባ አቶ አለ በርዎ ከኢዜአ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።የራያ አዘቦ ህዝብ ባለፉት ሶስት ዓመታት አገራዊ ለውጡን ተቀብሎ የህዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

ህዝቡ በአሸባሪው ሕወሃት ከማንም በላይ ጭቆና ሲደረስበት እንደነበር አስታውሰው፤ ክልሉን መከላከያ ከያዘው ጀምሮ በተለይ አርሶ አደሩ ተረጋግቶ ወደ እርሻው መግባቱን ተናግረዋል።ሆኖም በአሁኑ ወቅት መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደውን የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ ህዝቡ በአሸባሪው ሕወሃት ዋጋ እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።

የትግራይ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውንና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ መንግስት ያደረገው መልካም ተግባር የራያ አዘቦ ህዝብ በአሸባሪው ሕወሃት ግድያና ሰቆቃ እየደረሰበት መሆኑን ጠቁመዋል።

ክልሉ በመከላከያ ቁጥጥር ስር እያለ የራያ አዘቦ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው፤ “አሁን ከአካባቢው መልቀቁን ተከትሎ ችግር ውስጥ በመግባቱ መፍትሄ ያስፈልገዋል” ብለዋል። የራያ አዞቦ ህዝብ ከዚህ የከፋ ጉዳት ከማስተናገዱ በፊት መንግስትና መከላከያ እንዲደርስለትም መጠየቁን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version