Site icon ETHIO12.COM

የሃጫሉ ገዳዮች የተባሉት ” ጥፋተኛ” ተባሉ

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተከሰሱ ሶስት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ። የጥፋተኝነት ፍርዱን ያስተላለፈው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የጸረ ሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ነው፡፡

ጥፋተኛ የተባሉት ገዳዩ ጥላሁን ያሚ እንዲሁም ተባባሪዎቹ ከበደ ገመቹ እና አብዲ አለማየሁ ናቸው፡፡ችሎቱ የቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሀምሌ 8 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙን የዘገበው ፋና ነው።

ሃጫሉ ባለፈው ሳምንት የሙት ዓመቱ ሲከበርና በህይወት እያለ ያዘጋጀው አልበም ሲመርቅ አባቶ ለልጃቸው ነብስ ተጠያቂ የሆኑ ላይ ፍትህ እንዲበየን አጥብቀው ተይቀው ነበር። “ዋሴ” ብሎ ያዜመላት ባለቤቱ ደግሞ የባለቤቷን ስም ላልተገባ ተግባር እንዳትጠቀሙ ማለቷ አይዘነጋም።

Exit mobile version