Site icon ETHIO12.COM

ከድተው የቀሩት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ማንነታቸው ታወቀ

ከጁንታው ጋር ከድተው የቀሩት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ማንነታቸው ታወቀ

ጁንታው በሁለት ሳምንት ተደምስሶ በትግራይ ክልል በጊዚያዊነት ከተዋቀረው ከ15ት የክልሉ ቢሮ ኃላፊዎች እና የካቢኔ አባላት መካከል ግማሾቹ ጁንታውን ተቀላቅለው ቀርተዋል:: ሰሞኑን አዲስ አበባ ግቡ ሲባሉ በመቀሌ ከጁንታው ጋር የቀሩት የክልሉ ቢሮ ኃላፊዎች እና የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት:-

1ኛ) ዶክተር ካህሳይ ብርሃኑ – የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

2ኛ) ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ – የጤና ቢሮ ኃላፊ

3ኛ) አቶ ሰለሞን አበራ – የውኃ ኃብት ቢሮ ኃላፊ

4ኛ) አቶ ቴወድሮስ – የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ

5ኛ) አቶ ዬሴፍ ተስፋይ – ንግድና ኢንድስትሪ ቢሮ ኃላፊ

6ኛ) አቶ መንገሻ – የኮንስትራክሽን: መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

7ኛ) ወ/ሮ እቴነሽ ንጉሴ – የሴቶች ቢሮ ኃላፊ ናቸው!!!! ሌሎች ምክትል ቢሮ ኃላፊዎችን ሳይጨምር ነው!!!!

እንግዲህ ከእነዚህ ጋር ነበር መንግስታችን በእምነት እና በቅንነት ለ 8 ወራት ሲሰራና ሲደክም የነበረው::

እንግዲህ ከእነዚህ ጋር ነበር የሃገር መከላከያ ሰራዊታችን የክልሉን ሰላም እና የህዝቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ደሙን እያፈሰሰ እና ውድ ህይወቱን እየገበረ ለ8 ወራት ያህል ትግራይ ክልል የቆየው::

እንግዲህ ከእነዚህ ጋር ነበር የፌደራል ፖሊሳችን የትግራይ ህዝብ ደህንነትን ለማረጋገጥ : ሌብነትን እና ዘረፋን ለመከላከል : ወንጀለኞችን በህግ ስር ለማዋል : የህዝቡ ሰላማዊ ኑሮ እንዲመለስ … ወዘተ አያሌ መስዋዕትነት እየከፈለ በትግራይ ክልል የሰነበተው::

እንግዲህ እነዚህ ናቸው ከውጭ ሃገር የሚመጡ አምባሳደሮችን: የተለያዩ ልዑካንን: የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ነን ባዬችን : ዲፕሎማቶችን ወዘተ… ተቀብለው ሲያናግሩና የውሸት መረጃ ሲግቷቸው የነበሩት::

እንግዲህ እነዚህን ነው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በካቢኔነት ሰይሞ እያንዳንዷን ጉዳይ ሲያወያያቸው: በካቢኔ ሲያስወስናቸው : ውሳኔዎችን ሲያስተላልፍ እና እየተገበርኩ ነው ሲል የከረመው::

እንግዲህ በነዚህ የጁንታው ክፋዮች በኩል ነበር በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚወጡ እቅዶች: የሚደረጉ ወታደራዊ ዝግጅቶች : የደህንነት መረጃዎች: የሚደረጉ ሚስጥራዊ: ልዩና መደበኛ የካቢኔ ስብሰባዎች… ወዘተ አስቀድሞ አለያም በፍጥነት ለጁንታው እና በውጭ ለሚገኙ የጁንታው አፈቀላጤዎች መረጃ ሲወጣ የነበረው::

እንግዲህ የተለያዩ የሃገራችን የክልል መንግስታት: የሃይማኖት መሪወች : የሃገር ሽማግሌዎች: ታዋቂ ሰዎች : እርዳታ አሰባሳቢ በጎ ፈቃደኞች: ሚኒስቴር መ/ቤቶች : ኤጅንሲዎች እና ኮምሽኖች: የስልጠና ተቋማት… ወዘተ መቀሌ ድረስ እየሄዱ አይዟችሁ ሲሉና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ… ሲያስረክቧቸው የነበሩት ለነዚህ የጁንታው ነጭ ለባሾች ነበር::

እንግዲህ እነዚህ የጁንታው ክፋዬች በመታመናቸው ነበር የኢትዮጵያ መንግስት ሃገሪቱ ከሌላት ሃብት እየቀነሰ: ከኢትዮጵያ እናቶች አፍ እየቀማ : የፕሮጀክቶችን በጀት እያጠፈ … ስንትና ስንት ቀዳዳዎችን ሊሸፈን ሲችል… ሊታገዝ የሚገባው ህዝብ አለኝ ብሎ ከሁሉ በማስቀደምና ታማኝ ጊዜያዊ አስተዳደር አለ ብሎ በማመን #ከ 100 ቢሊየን በላይ ጥሬ ገንዘብ ወደ ትግራይ ክልል ሲልክ የሰነበተው::

ብቻ ስንቱ ክህደታቸው ተዘርዝሮ ያልቃል??? የክፋትና የአስመሳይነታቸው ልክስ በምን ይገለፃል??? በክህደት የፈፀሙት ግፍ እና ሰቆቃ እንዴትስ ተብሎ በምንስ ቃል ሊገለፅ ይችላል??? የባንዳነት ተግባራቸው: የባህሪ መመሳሰላቸው: የሴረኝነታቸውና የሻጥራቸው ልክ : የጭካኔያቸው ጥግ… በምን አንደበት ከቶ መግለፅ ይቻላል?? ሁሉም አንድ ናቸው ወይ ያስብላል? የኢትዮጵያ ህዝብ ግራ ገባው!!! እንዳይርቃቸው ፈጣሪን ይፈራል አብሮ በልቷል አብሮ ጠጥቷልና ይታገሳቸዋል:: እንዳይቀርባቸው እንዳያምናቸው የሚያደርጉትን ክህደት ክፋት እና እብሪት በተጨባጭ ያያል!!! የቸገረ ነገር ነው!!!

በአጠቃላይ ከጁንታው ጋር መቀሌ የቀሩት የክልሉ የቢሮ ኃላፊዎች እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ክህደታቸው ግልፅ ሆኗል!!!! መቅረታቸው በራሱ የሚናገረው ነገር ስላለ ብሄራዊ ክህደታቸው ሌላ አስረጅ አያሻውም!!!! ለፈፀሙት ሃገራዊ ክህደት (Treasonous Act) ግን በህግ የሚጠየቁበት ቀን ግን ሩቅ አይሆንም!!!! በክህደት ግፍ የፈሰሰው የሰራዊታችን ደም ስለ ፍትህ ይጮሃል!!! ስለዚህ የከሃዲዎችን ጉዳይ “ቀን” ወይም “ጊዜ” ለሚባለው ፈራጅ እንተወውና እንቋጨው!!!

ባይሆን ከእነሱ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን እና አሁንም ያላቸውን ሰዎችና ተቋማትን ግን መከታተል ይገባል!!!! በትግራይ ብልፅግና ስም አዲስ አበባ የገቡትም ብዙዎቹ የዚሁ ክህደት ተቀጥላ ናቸው!!!! ባንዳዎችን አሁንም በግልፅ ማጋለጣችንን እንቀጥላለን!!!! በቂ መረጃ አለ!!! መንግሥት እግር በእግር እየተከታተለ እርምጃ ይውሰድ!!!

ኢትዮጵያ የገጠማት ትግል እንዲህ ዓይነት ነው!!!! የገጠመን ችግር ለንግግር እንኳን አይመችም!!!!! እንደዛም ሆኖ ኢትዮጵያ ማሸነፏ የግድ ነው!!!!! ውዱ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራ ኦሮሞ አፋር ሲዳማ ሳትል…. በዚህ ወቅት አንድ ሁንና ባንዳዎችን እያሳፈርክና እየቀጣህ ሃገርህን አሻግር!!!! መንግስትም ጨክንና ቆሻሻውን አፅዳ!!!!! ኢትዮጵያ ማሸነፏ ባንዳዎችም መክሰማቸው አይቀሬ ነው!!!! ለማንኛውም ጀግናው መከላከያችን እንኳን ደጀን ወደሆነው ህዝብ መጣ!!!! ከነዚህ ጋር እንዴት ተደርጎ ለአንድ ዓላማ መቆም ይቻላል??! ባንዳ ያው ባንዳ ነው!!!! የታሪክ አተላ!!!!!

Ethiowekliks

Exit mobile version