Site icon ETHIO12.COM

ሶስት አባላቱ በትህነግ ይተገደሉበት ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ስራ ማቆሙን ይፋ አደረገ

ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በዓብይ ዓዲ፣ አዲግራትና አክሱም የሚያከናውናቸውን ስራዎች ማቆሙን አስታወቀ ቡዱኑ በሰራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ግድያ ላይ ምርመራ እንዲካሄድና ኃላፊነት የሚወስዱ አካላት እንዲኖሩ ጠይቋል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከዚህ ቀደም በሰጠው ምገለጫ “የህወሃት ታጣቂ ቡድን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰራተኞችን ገድሏል ብሏል

ከሁለት ሳምንት በፊት በ3 ሰራተኞቹ ላይ ግድያ የተፈጸመበት የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን፤ ግድያውን የተመለከተ ምርመራ እንዲካሄድና የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ደህንነታቸው ተጠብቆ የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲኖርም ጥሪ አቅርቧል።

ቡዱኑ በማእከላዊ እና ምስራቅ ትግራይ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለጊዜው ገታ ማድረጉን በመግለጽ፤ በዚህም የተወሰነ ክፍትት ሊፈጠር እንደሚችል ገልጿል። በሌሎች የክልሉ ቦታዎች እገዛ ለሚሹ ዜጎች የሚያደርገው እርዳታ ግን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባወጣው መግለጫ ስታቀውቋል፡፡

የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ተሬሳ ሳንክሪስቶቫል “ሰራተኞቻችን ከተገደሉ ሁለት ሳምንታት ቢቆጠሩም እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም፤ የአማሟታቸው ሁኔታም እንዲሁ ግልጽ አይደለም” ብለዋል።

ቡድኑ በሰራተኞቹ ላይ በተፈጸመው ግድያ ከባድ ጊዜያት እያሳለፈ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ፤ በግድያው ላይ ምርመራ እንዲካሄድ እንዲሁም ኃላፊነት የሚወስዱ አካለት እንዲኖሩ ጠይቋል።

“የተፈጸመው ግድያ ባልተጣራበት ሁኔታ፤ አሁን በተወሰኑ የትግራይ አከባቢዎች ኤም.ኤስ.ኤፍ የሚሰጠው አግልግሎት ማቆሙ ተገቢ ውሳኔ እንደሆነም” ገልጸዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት የኤስ.ኤም.ኤፍ የእርዳታ አስተባባሪ ማርያ ሄርናንዴዝ፣ ረዳት አስተባባሪ ዮሀንስ ሓለፎም ረዳ እንዲሁም ቴድሮስ ገ/ማርያም የተባለ ሾፌር በመጓዝ ላይ ሳሉ ተገድለው አስክሬናቸውም ከመንገድ የተወሰነ ሜትር ርቀት ላይ መገኘቱ የሚታወስ ነው። የስራ ባለደርቦቻችን ማርያ፣ ቴድሮስ እና ዮሃንስ ግድያ በዚህ ጦርነት የሰው ህይወት ምን ያክል እንደማይከበር ያሰየ ነው” ሲሉም ዳይሬክተሯ አክለዋል።

በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የህክምና እና የእርዳታ ድርጅተች ሰራተኞች ዒላማ መደረጋቸውን፣ አምቡላንስን ጨምሮ የህክምና ቁሳቁሶች መዘረፋቸውና መውደማቸውም እንዲሁም የኤም.ኤስ.ኤፍ ሰራተኞች የተለያያ ዛቻና ማስፈራራት ሲደርስባቸው መቆየቱንም ነው ዳይሬክተርሯ የተናገሩት።

የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (MSF- Médecins Sans Frontières) በትግራይም ሆነ በተቀሩት የኢትዮጵያ አከባቢዎች በቀጣይ የሚሰራ ከሆነ ሁሉም የግጭቱ ተዋናዮች ዋስትና ሊሰጡት ይገባልም ብሏል ሳንክሪስቶቫል፡፡

ሳንክሪስቶቫል “በባለደረቦቻችን የተፈጸመው ግድያ ዳግም እንዳይፈጸም ለማረጋገጥ፤ ሁሉም አካላት ኃላፊነት ወስደው ሊሰሩ ይገባል” ሲሉም ጠይቀዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግንቦት 25 ቀን 2013 በሰጠውመግለጫ በትግራይ ክልል አብይአዲ አካባቢ የ3 ደንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ሰራተኞች በተፈጸመባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን አስታውቆ ነበር።

መከላከያ በወቅቱ በሰጠው መግለጫው “የህወሃት ታጣቂ ቡድን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF- Médecins Sans Frontières) የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሰራተኞችን ከመኪና አስወርዶ እንደገደላቸው ቅድመ መረጃ ደርኛል” ማለቱም ይታወሳል።

ኤም.ኤስ.ኤፍ በስድስት ወራት የትግራይ ቆይታው ለ15 ሺህ 500 ገደማ ሰዎች የህክምና አገልግሎት መስጠቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

አልዐይ

Exit mobile version