የኢቶጵያ መንግስት የኢምባሲዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ይህም የሚሆነው ኤምባሲዎቹ ወጪ ከማብዛታቸው በላይ የግለሰቦች ምሽግና መጠቀሚያ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ለተወሰኑና ለተመረጡ አምባሳደሮች በደብዳቤ ጥሪ መላኩን አዲስ ስታንዳርድ ” ሰበር” ሲል ዘግቦታል።
ደብዳቤው በገሃድ የተሰራጨና ባለፈው ዓመት የተጠናው ጥናት ውጤት መሆኑን መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ በዲፕሎማሲው ረገድ ፋይዳ የሌላቸው ዲፕሎማቶች አገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈሏት በተደጋጋሚ ሲተች ነበር። በዚሁ መነሻ “እንደቀድሞው በጅምላ በግዢ ዲግሪ የተመረቁ ” ሳይሆኑ አዳዲስ ዲፕሎማቶች ተመልምለው ሲሰለጥኑ እንደነበር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የዚህ አካል እንደሆነ የተነገረለት የማስፈጸም ጅማሮ ሲሰሩበት ለነበረው ሚሲዮን ንብረት አስረክበውወደ አገር ቤት በመመልስ ሪፖርት እንዲያደርጉ የታዘዘበትን ደብዳቤ ደብዳቤው ከተላከለት አንድ አካል በመውሰድ “ሰበር” ዜና በሚል አዲስ ስታንዳርድ አትሟል። በደብዳቤው እንደተጠቀሰው ፣ጥሪ የተደረገላቸው እስከ ነሃሴ 15 ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ተሾመ ቶጋ፣ ኩማ ድሪባ፣ አይነት ዲፕሎማቶች ያሏት አገር መሆኗ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ለዲፕሎማሲው ቅረበት ያላቸው በተደጋጋሚ ሲተቹ እንደነበር።
የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸው የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ” ሰበር ዜና መሆን ያለበት መንግስት ህዝብን ሰምቶ እርምጃ ወሰደ የሚለው በሆነ ነበር” ሲሉ ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር። ሐኪሜ… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ ባለስልጣናትና… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት