Site icon ETHIO12.COM

አብይ ” ውረዱ ብለውናል” እንስማማና ትህነግ ይንገስ? ወይስ ክተት?

አስቀድሜ ራሳቸውን ” እኔ ሌባ ነኝ” ብለው ድፍን ሕዝብ እያየ በረኪና ላያቸው ላይ ሲደፉና ውርደትን ጭልጥ አድርገው ሲጠጡ ዓለም ያያቸውን ታምራት ላይኔን በአማራና ኢትዮጵያ ጉዳይ አደባባይ የሚያቀርቡ ሚዲያዎችን ታስቡዋቸው ዘንድ እለምናለሁ። በአደባባይ ላያቸው ላይ የደፉት በረኪና ለምጡ እያብለጨለጨ እሳቸውም ሳያፍሩ እዛው ህዝብ ፊት ብቅ ያላኡ። እንደ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ዓይነቱን ከረሃብተኛ ጉሮሮ ነጥቆ አገር የከዳና የኢትዮጵያን ምርጥ ጀነራሎች ሆን ብሎ እንዲከሽፍ ታስቦ በተዘጋጀ መፈንቅለ መንግስት ያስጨረሰን ሰው የሚከተሉትንና የሱ አንደበት ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ልብ በሉዋቸው። (ውድ የሆኑትን ጀነራሎቻችን የውሻ ሞት የሞቱበትን፣ አስከሬናቸው የተጎተተበትን መፈንቅለ መንግስት ሱዳን እየሄደ ይከታተልና ይመራ እንደነበር ራሱ አምኗል- ኢሳትን ይመልከቱ)

በሁለተኛ ደረጃ ዛሬ ውጊያውና ትግሉ ከትህነግ ጋር ሳይሆን አሜሪካ ከምትመራው የተቀናጀ ግዙፍ ሃይላት ጋር እንደሆነ እንመን። የዚህ ሁሉ መዘዝ የአባይ ወንዝ መገደቡ ስለመሆኑ በሙያው የተካኑ፣ ጂኦ ፖለቲካውን ጠንቀቀው የሚያውቁ በስፋት ማብራሪያ የሰጡበት ጉዳይ ነውና ዛሬ ይኸው አስቀድሞ የተባለው እይሆነ ነው። አይሁዳዊው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዘመቻው መሪ ሆኖ አይናችን ላይ ወስፌ እየከተተ ነው። “ድሆች ለምን ብረሃን ያያሉ፣ አሳ ያመርታሉ፣ ስንዴ ከመረዳት ውጭ እንዴት ያጭዳሉ” በሚል የፍርዖን ትዕቢት እስከወዲያኛው ሊያጠፉን ተነስተዋል።

የአውሮፓ አገራት፣ የአረብ አገራት፣ ሱዳን ባቅሟ መርዝ ተሸካሚ ሆና… በአሜሪካን ፊት አውራሪነት የዘመቱብን ሳያንስ ዓላማቸውና ፍላጎታቸው በውል የማይታወቅ ሚዲያዎች ሃያ አራት ሰዓት ስለምን እንድንበተን እንደሚሰሩ፣ ምን ቢከፈላቸው እንዲህ አቅላቸውን እንደሳቱ፣ የት ሲደርሱ እንደሚበቃቸውና ምን ዓይነት አገር ለማየት እንደሚመኙ ለመረዳት በተደጋጋሚ ባስብም ሊገባኝ እንዳልቻለ፣ ይልቁኑም የቅዠት ዓለም እየመስለኝ ተቸግሬያለሁ።

መሪዎችን፣ አገርንና ሕዝብን ነጥሎ የማየት ጉዳይ የዓለም ሚዲያዎች መርህ ነው። እኔ በምኖርበት ሎንዶን እስከማውቀው አንድም ሚዲያ አገሩ ላይ ጠጠር አይጥልም። ስለ አገራቸው ዘብ እንዲቆሙም አይነገራቸውም። እንደውም ቀድመው አገራቸውን ጠብ መንጃ ከያዘ ሃይል በላይ ይከላከላሉ። የአገራቸውን ጥቅምና ፍላጎት ለማሳካት ሲፈልጉ ልክ አሁን ኢትዮጵያ ላይ እንደ ጥንብ አንሳ እንደወረዱባት ይሟሟታሉ። ብር የተከፈላቸውን የትህነግ ነጭ አክቲቪስት ሚዲያዎች በሌላ መልኩ የሚታዩ ናቸው።

ትንሽም ቢሆን ፊደል ስለቆጠርኩ የአገራቸንን ሚዲያዎች ለመስማት ስሞክር፣ ( ትንተና መሆኑ ነው) በንግግራቸው ውስጥ አልፎ የሚቀረናኝ ሴራና ክፋታቸው እንጂ ሙያዊ አሳብ አይደለም። የክፋታቸው መጠን ልክ የሌለው መሆኑ ከሚያስገርመኝ በላይ ጭንቀት የሚለቅብኝና መፍትሄው ግራ የገባኝ እነዚህን ሃይሎች የሚደጉሙና የሚከተሏቸው ” ኢትዮጵያዊያን” ናቸው። ከገሪቱ ሕዝብ ቁጥር አንጻር እዚህ ግቡ የሚባሉ ባይሆኑም በዋዛ ፈዛዛ አገራቸው በገሃድ እየሰመጠች እያዩ እተቸከሉበት የክፋትና የሴራ መንደር ተቀርቅረው የቀሩት ወገኖቼ ያሳዝኑኛል።

በኢትዮጵያ በመንግስት ደረጃም ሆነ በግለሰብ፣ በአጠቃላይ በፖሊሲ ደረጃም ሆነ በአፈጻጸም ሊሻሻሉ የሚገባቸው በርካታ ጉዳዮች እንዳሉ እሙን ነው። ለውጡ ከመጣ ጀምሮ በርካታ በጎ ስራዎች እንደተከናወኑም ይታመናል። በተመሳሳይ ለውጡ እውን ከሆነ ጀምሮ መንግስት ዕረፍት አልባ ሆኗል። አገሪቱ ላይ በየአቅጣጫው የተፈጸመው የሴራ ፖለቲካ ውጤቱን ለገመገመ ይህ መንግስት የመተንፈሻ ጊዜ እንኳን አልነበረውም። እልቂቱ፣ መፈናቀሉ፣ ግጭቱ፣ መረን አላባው የሚዲያ ጦርነት፣ ሁሉም በስፖንሰር የሚፈጸም ስለመሆኑ አንዳች ጥርጥር የለውም። ይህ ሁሉ እየታወቀ መሪዎቹን ሰብል እንደወረረ አንበጣ እምሽክ አድርጎ በየቀኑ መብላት ሙያ ተብሎ ዛሬ ማጥ ውስጥ እንደንገባ ሆነናል።

“የዘመናት ብሶት የወለደው ” ብሎ ” የዘመናት ችግር” የተከለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ስልጣኑንን ያሞቀው የአማራ መሪትን በመዝረፍና አማራን በጠላትነት በመፈረጅ ነበር። ምንም እንኳ አማራን የትግሉ መገልገያ ጠላት አድርጎ የሳለው ገና ድሮ ቢሆንም፣ ስልጣን ከያዘ በሁዋላ ግን በአማራ ላይ የፈጸመው ጉድ ለወሬም ለነጋሪም እልፍ ነው። ማምከንን ጨምሮ።

ትህነ ሌሎች ወንድማማች ሆነው አብረው የኖሩ እንዲጋጩ፣ እንዲባሉና እንዲጠፋፉ በመንግስት ሚድያ፣ በግብር ከፋዩ ህዝብ ሃብት ጸብን ሲረጭ ኖሯል። ለዓላማው ይጠቅመናል ያለውን መርዝ አሳትሞ የመማሪያ መጽሃፍ አድርጓል። በኪነት፣ በመጽሃፍ፣ በመድረኮች፣ ወዘተ እያሰራጨ አንድ ትውልድ አምክኗል። በተመሳሳይ በራሱ ክልል ለጥንቃቄ ሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብ፣ ምዕራብ እያለ ዞኖችን ሲከፋፍል፣ ሌሎችን በብሄር መትሮ የዘር አተላ ሲገት ኖሯል።

እንደ ሚዲያ በተፈጠረው አጋጣሚ ይህን ስጋት ለመቅረፍ፣ መርዙን በማምከን እንደመስራት፣ በኩርፊያ፣ በመገዛት፣ ባለማቀና አለማወቅን ባለመረዳት፣ በድፍረት ንግግር ይባስ ወደማንወጣው ችግር አምርተናል። ተራው ነዋሪ በገባው መጠን የማይረዱ ያገኙትን ሁሉ እየለቀሙ ሲረጩ የሚታያቸው ከሚረጩት የሚያገኙት ሃብት እንጂ ሌላ አይደለም።

ዛሬ ተወደደም ተጠላም ክፉ ጊዜ ላይ ነን። የአባይ መገደብ ዓለምን በሙሉ አነቃንቋል። የአባይ ጉዳይ አፈር ለቃመውና ተረት ለሆነው የትግራይ ነጻ አውጪ በረከት ሆኖ ዳግም ተነስቷል። የሉሲፈር አገልጋዮቹ እነ አሜሪካ ለግብጽና ስሟን ለማልጠራት አገር ሲሉ በአይሁድ አንደበትና ሴራ ተብትበውናል። ሴራው አገራችንን መሪ አልባ አድርገው ተህነግን በሌሎች ተላላኪዎች አጅቦ ወደ አመራር መመልስ ነው።

ይህ ከሆነ በሁዋላ ጦራችን ልክ እንደቀደመው ባይሆንም ይናዳል። ጦራችንን ያሳረዱና ያረዱ ከተደበቁበት ይወጣሉ ወይም ከታሰሩበት ይፈታሉ። እነ ስብሃት ነጋ ዳግም ይተፉብናል። በትግራይን መልሶ ማቋቋም ሰበብ ዳግም ሃብታችንን ስንዘረፍ እንኖራለን። የለውጡን አመራሮች ያጠፉዋቸዋል። ማረድና መጨፍጨፍ ለሚታዘዙ መብት ሆኖ ሰራዊታችንና አገራችንን ለመከላከል የተፋለሙ “የጦር ወነጀለኛ” እንዲሆኑ ድግሱ ጎን ለጎን ተጧጡፏል። በዛው ይዘጉባቸዋል። ይህ እንዲሆን ነው እየትሰራ ያለው። የሚመደበው ተላላኪ ለግብጽ የግርድና ውል ይፈርማል። ግብጽ ውሃ ጎደለ ባለች ቁጥር ከባንኩ እያወጣ ለምስጠት የሚምል ተላላኪ ኢትዮጵያ ላይ ይጫናል። ይህ ሃቅ ነው።

ይህ የማይቀረው የአሜሪካ ዕቅድ ትግራይ ተዘርፎ የተሰጣት የአማራ ክልል መሬት ባስቸኳይ በድጋሚ ከአማራ ክልል እንዲነጠቅ ያዛል። በነጋ ጠባ አማራ ከትግራይ እንዲወጣ የሚወተውተው የአይሁድ አፈ ቀላጤ ብሊንከን፣ አማራ ክልሉን መነጠቁን ከየትኛውም የአሜሪካ ባለስልጣን በላይ ያውቃል። አይሁዶቹ ታሪኩን ሁሉ በደንብ ቢረዱትም ከግብጽ ጋር በዶለቱት መሰረት ለግብጽ ሲራ ተስማሚው አስፈጻሚ የትግራይ አስገንታይ ቡድን በመሆኑ ያለውን ሁሉ ማስፈጸም ግድ በመሆኑ አማራ ላይ ተፈርዶበታል።

የማንነትና የመሬት ይመልስ ጥያቄ ውስጣችን ለተሰገሰጉ የአሜሪካ ጆሮ ጠቢዎች ገሃድ ነው። ባጭሩ ላፉት ሰላሳ ዓመታት በህግ ሊፈታ ያልቻለውና እንደ ታምራት ላይኔ ዓይነት ሞራል አልባ ከሃጂዎች ሲደግፉት የኖሩት የመሬት ወረራ ዓለም የሚያውቀው ሃቅ ነው።

ትህነግ በፌዴሪሽን ምክር ቤት የፍትህን ደጅ ሰረገላ ቁልፍ አስረክቦ በሾማቸው ታማኞቹ ያስቀረቀረበት የአማራ የመሬት ይመለስ ጥያቄ በመንግስት ምላሽ እንዳይሰጠው የሆነው ለምን ይሆን? ብሎ የሚጠይቅ የሚኖር አይመስለኝም። ወልቃይት ጠገዴ ፣ ሁመራና የራያ መሬት በሃይል ተወሮም ከችጋር ያልወጣው ትህነግ፣ በወረራ የዘረፈውን መሬት ካጣ በሁዋላ ዳግም ለማስመለስ ሚሊሻና ሃይል ማሰባሰቡን በማድነቅ የምዕራብ አገራት ሚዲያዎች እየጻፉ ነው።

ትህነግ ክተት ጠርቶ ሲያበቃ ይደነቃል። አማራ ራሱን ለመከላከል ዝግጁ መሆኑንን ሲናገር ” ውጣ” ይባላል። በዚህ ላይ የአገራችን ዜጎች መሆናቸውን ባንጠራጠርም ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ከፋፋይ ” ትንተና” እያሰሙ ነው። አንዳንዶችም ባደባባይ ሌላ እያወሩ በየኤምባሲው ጭራቸውን እየቆሉ ነው። ይህ ሁሉ ተዳምሮ ወዴት እንደሚያመራን ነገ ዛሬ ሳንል ማወቅ አለብን። አውቀንም የሚበጀውን ማድረግ ይገባናል።

በኦሮሚያ እየተሻሻለ የመጣውን ሰላም እንደ ቀላል በመቁጠር፣ ሌላ ጣጣ ለማምጣት የሚራወጡትን በዚህ አጋጣሚ ለመምከር እወዳለሁ። ኦሮሚያ ከተለኮሰ የሚቆም ነገር አይኖርም። የኦሮሚያን ስሪት በወጉ መረዳት እጅግ ዋና ጉዳይ ይመስለኛል። በቀጣይ እመለስበታለሁ። እስከዛው ግን አብይ ” ውረዱ ብለውናል” ብለው ጫናውን በግልጽ መናገራቸውን እናስብ። እንስማማና በትህነግን ለመገዛት እንማል? ወይስ ምን እናድረግ? ምሁራን በአስቸኳይ ኮንፍረንስ አድርገው ጥሪያቸውን ያሰሙንና ክተት ይታወጅ?

መኩ ዓለምሰገድ ሎንዶን

ጽሁፉ የጸሃፊውን እምነት ብቻ የሚያንጸባርቅ ነው


Exit mobile version