ETHIO12.COM

ከሱዳን የተነሱ የጭነት መኪኖች ” አንፈተሽም” ብለው ተይዘዋል፤ ምን አስፈራቸው?

የዕርዳታ እህል ነው የጫንኩት ያለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከሱዳን በቀጥታ አሰልፎ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባቸውን ዘጠኝ ከባድ መኪኖችን ” አላስፈትሽም” በማለቱ ፖሊስ አስቁሟል። ” መንግስት እርዳታ አስተጓጎለ” የሚል መግለጫ ይጠበቃል።

በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ተገቢ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ሲል መኪኖቹን አስቁሞ ፍተሻ ላድረግ ማለቱን ያስታወቁት በስፍራው ያሉ እማኞች ናቸው። የዕርዳታ ቁስ ጭነዋል የተባሉት ሎቤድ ተሳቢዎች ከሱዳን ተነስተው ወደ ትግራይ ለመሄድ፣ በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት ከተማ ከደረሱ በኋላ ፖሊስ የጸጥታና የጥንቃቄ ጥያቄ ያነሳው።

በአስቸኳይ ፍተሻ ተደርጎ እርዳታው ለህዝቡ እንዲደርስ የተጠየቁት ክፍሎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የፍላቂት ከተማ ፓሊስ ዘጠኙንም የ WFP ተሽከርካሪዎች ከሁለት ማርክ 2 አጃቢ መኪኖች ለጊዜው ባሉበት ሳይነቀሳቀሱ እንዲቆዩ አድርጓል።

WFP ከትሀነግ አመራሮች ጋር የድርጅቱ መርህ በማይፈቅድው ደረጃ በገሃድና በድብቅ እየፈጸመ ያለው ተግባር ለጥርጣሬው መነሻ መሆኑን ተመክቷል። በፈተሻ መሳሪያ ከተገኘ የዓለም ምግብ ድርጅት በአደባባይ በማስረጃ ስለሚወገዝ የአካባቢው አስተዳደር ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ መከናወን ያለበትን አከናውኖ ጉዳዩን እልባት እንዲያበጅለት ዜናውን ያሰራጩ ገልጸዋል።

ዜናው በማህበራዊ ገጾች የዓይን ምስክሮች ካሰራጩት ውጭ ከመንግስት ወገንም ሆነ ከዓለም ድርጅት በኩል እስካሁን በገሃድ የተባለ ነገር የለም። ትህነግ እርዳታን ሃይሉን ለማደስ እንደሚጠቀምበት ልምዶች ምስክር መሆናቸው በተደጋጋሚ የተባለ ጉዳይ ነው። ድርድርን አስመልክቶም ቅድሚያ ያስቀመጠው ነጻ በረራና የየብስ ኮሪዶር መሆኑ ይታወሳል።


Exit mobile version