የዕርዳታ እህል ነው የጫንኩት ያለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከሱዳን በቀጥታ አሰልፎ ወደ ኢትዮጵያ ያስገባቸውን ዘጠኝ ከባድ መኪኖችን ” አላስፈትሽም” በማለቱ ፖሊስ አስቁሟል። ” መንግስት እርዳታ አስተጓጎለ” የሚል መግለጫ ይጠበቃል።
በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ተገቢ የጥንቃቄ እርምጃ ለመውሰድ ሲል መኪኖቹን አስቁሞ ፍተሻ ላድረግ ማለቱን ያስታወቁት በስፍራው ያሉ እማኞች ናቸው። የዕርዳታ ቁስ ጭነዋል የተባሉት ሎቤድ ተሳቢዎች ከሱዳን ተነስተው ወደ ትግራይ ለመሄድ፣ በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ፍላቂት ከተማ ከደረሱ በኋላ ፖሊስ የጸጥታና የጥንቃቄ ጥያቄ ያነሳው።
በአስቸኳይ ፍተሻ ተደርጎ እርዳታው ለህዝቡ እንዲደርስ የተጠየቁት ክፍሎች ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የፍላቂት ከተማ ፓሊስ ዘጠኙንም የ WFP ተሽከርካሪዎች ከሁለት ማርክ 2 አጃቢ መኪኖች ለጊዜው ባሉበት ሳይነቀሳቀሱ እንዲቆዩ አድርጓል።
WFP ከትሀነግ አመራሮች ጋር የድርጅቱ መርህ በማይፈቅድው ደረጃ በገሃድና በድብቅ እየፈጸመ ያለው ተግባር ለጥርጣሬው መነሻ መሆኑን ተመክቷል። በፈተሻ መሳሪያ ከተገኘ የዓለም ምግብ ድርጅት በአደባባይ በማስረጃ ስለሚወገዝ የአካባቢው አስተዳደር ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ መከናወን ያለበትን አከናውኖ ጉዳዩን እልባት እንዲያበጅለት ዜናውን ያሰራጩ ገልጸዋል።
ዜናው በማህበራዊ ገጾች የዓይን ምስክሮች ካሰራጩት ውጭ ከመንግስት ወገንም ሆነ ከዓለም ድርጅት በኩል እስካሁን በገሃድ የተባለ ነገር የለም። ትህነግ እርዳታን ሃይሉን ለማደስ እንደሚጠቀምበት ልምዶች ምስክር መሆናቸው በተደጋጋሚ የተባለ ጉዳይ ነው። ድርድርን አስመልክቶም ቅድሚያ ያስቀመጠው ነጻ በረራና የየብስ ኮሪዶር መሆኑ ይታወሳል።
- የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት… Read more: የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
- አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ“ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ… Read more: አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
- ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናውቤት የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ብላለች፦ “ደም ማነስ የያዘኝ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለሁ ነው። ቶሎ ይደክመኝ፣ አጥንቶቼን ይቆረጥመኝ፣ እንዲሁም ትኩረቴ በቀላሉ ይከፋፈል ነበር።… Read more: ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው
- የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?ሰሞኑን በራያ አላማጣ አቅጣጫ የትግራይ የታጠቁ ሃይሎች በግጭት መሰማራታቸውን ተከትሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ገለልተኛ ወገኖች አስታውቀዋል። ጎን ለጎን የትግራይ ከፍተኛ… Read more: የትግራይ አመራሮች ከፌደራል መንግስት ጋር ያደረጉት የተለየ ስምምነት አለ?
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት