Site icon ETHIO12.COM

“ዳግም የሚዋረድ የወያኔ ቡድን እንጂ ሒሳብ የሚወራረድበት አንዳች የአማራ ህዝብ አይኖርም!”

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ም/አስተዳዳሪ

የትኛውም ምድራዊ ኃይል ቢመጣ ዳግም ወደነበርንበት የሰቆቃና የግፍ ዘመን ሊመልሰን አይችልም! የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ህዝብ በማንነቱ ምክኒያት ለ30 ዓመታት የግፍ ግፍ ሲፈጸምበት የቆየ ህዝብ ነው።

አማራነት ማንነቴ ይከበርልኝ ብሎ ጥያቄ በማንሳቱ ምክኒያ ያለማቋረጥ በጅምላ ታርዷል። ሐብትና ንብረቱን ጥሎ ከራሱ ግዛት በሰላም እንዳይኖር ተደርጎ ተፈናቅሏል። ሐብት ፣ ንብረቱን ገዳይና ዘራፊው ቡድን ባሰማራቸው ሐይሎች ተዘርፏል። የእርሻ ማሳውን ሳይቀር በእብሪተኞች ተነጥቆ የጎልበት ሰራተኛ እንዲሆን ሁኖ ፍዳም መከራም ሲከፍል የኖረ ህዝብ ነው።

አሁን በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ህዝብ ዘንድ ያ! የግፍና የመከራ ዘመን ላይመለስ ታሪክ ሁኗል። የትኛውም ምድራዊ ኃይል ቢመጣ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ህዝብን ዳግም ወደነበርንበት የሰቆቃና የግፍ ዘመን ሊመልስ አይችልም! የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብም ባይተዋር ሆኖ ከኖረበት ዘመን ተላቆ ነጻነቱን በማጣጣም ላይ ነው።

ያ! ጥቁር ዘመንና ታርክ የአማራ ህዝብ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ላይመለስ ታሪክ ሆኗል። ትናንት በህዝባችን መሐል በሰገሰጋቸው የራሱ ተላላኪዎች ጭምር ሲወጋን እና ሲያስወገናን የነበረውን የውያኔ ቡድን ለራሱ ነጥለን እርቃኑን አስቀርተነዋል። በአማራ ህዝብ መሐል የበቀሉ የውያኔ ተላላኪዎችም ከስመዋል። የአማራ ህዝብም ከከፋፋዩ የውያኔ ስርዓት ተላቆ ውስጣዊ አንድነቱን ማጠናከር ጀምሯል።

አሁን ሁሉም ነገር ቀላል ነው። በጦርነት ሜዳ ማሸነፍም ሆነ መሸነፍን ማን እንደሚችል ወያኔዎች በእብሪት ተወጥረው በፈጸሙት ትንኮሳ ልካቸውን አሳይተናቸዋል። ትናንት ዛሬ አይደለም። ትናንት ትግላችን ከሁለት ኃይሎች ጋር ነበር። በህዝባችን ወስጥ ከተሰገሰጉ ተላላኪዎች እና ከውያኔ ዘራፊና ገዳይ ቡድን ጋር ነበር።

ያም ሆኖ እውነት ላይ ቁመን ባደረግነው የጋራ ትግል እርቃናቸውን አስቀርተን ጫካና ዋሻ አስገብተናቸዋል። ከአሁን በሗላም ከገባበት ጫካና ዋሻ ተመልሶ ዳግም የሚዋረድ የውያኔ ቡድን እንጂ ሒሳብ የሚወራረድበት አንዳች የአማራ ህዝብ አይኖርም!

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ም/አስተዳዳሪ

Exit mobile version