ይህንን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ ተቀብያለሁ የሚል ሁሉ የአንድ ወር ስንቅ በማዘጋጀት በየቤቱና በየቀበሌው ሆኖ ለምናቀርበው የፈጥነህ ድረስ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ሲል ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

ወራሪዉ የትግራይ አሸባሪ መንጋ ኃይል ወልቃይት ጠገዴንና አከባቢውን ከ16 ዓመት ታዳጊ ጀምሮ እስከ 70 ዓመት አዛውንት የሆነ ማንኛውንም ትግራዋይ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብን እንዲወር የክተት አዋጅ አውጇል።

ማንነታችን እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የአማራ ተወላጅ የሆነ ሁሉ በየሄደበት እንደ ዶሮ አፍኖ በመሰወር፣ በመግደል፣ አካልን በማጉደል፣ ከሰማይ በታች ከመሬት በላይ አለ የሚባል ግፍ ሁሉ ተፈፅሞብናል። በሺዎች የሚቆጠሩ ታሪክ አዋቂዎች፣ ስለ ህዝብ መብት ተከራካሪ የሆኑትን የሀይማኖት አባቶችን የት እንደደረሱ ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል።

ስለሆነም በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል፣ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እንዲሁም ሚሊሻና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጥምር ተጋድሎ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማህበረሰብ ነፃ ወጥቷል። ይህ የትናንት አኩሪ ገድላችን ነው።

መላው የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ሆይ!!

ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ኃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ህልውናህን ሊያጠፋ ቆርጦ ተነስቷል። በመሆኑም በጠላት ዝግጅት መጠን ልክ በተጠንቀቅ እንድትቆም የወቅቱ አስገዳጅ ሁኔታ ሆኗል።

የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ!!

በህብረት፣ በአንድነት፣ በፅናት ስለታገልክ የስርዐት ለውጥ አምጥተኃል። ነፃነትም አግኝተኃል። ይሁን እንጂ ድጋሚ ህልውናህን ሊያጠፋ ከመላ ትግራይ የከተተ ወራሪ ኃይል በይፋ ጦርነት አውጆብኃል።

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!!

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የትግራይ ተስፋፊ ኃይል ባወጀው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቷል። ከአሁን በፊት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃዩ ስቃዬ፣ በደሉ በደሌ ነው ብለህ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለኃል። ይህን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያደንቃል እውቅናም ይሰጣል። ኃብት ማፍራት ይሁን በህይወት መኖር መኖርም አገር ሲኖር ነውና፤ ይህንን አገር አጥፊ ወራሪ ቡድን ለመመከት በምናደርገው ተጋድሎ ከጎናችን እንድትቆም ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ይህንን የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጥሪ ተቀብያለሁ የሚል ሁሉ የአንድ ወር ስንቅ በማዘጋጀት በየቤቱና በየቀበሌው ሆኖ ለምናቀርበው የፈጥነህ ድረስ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ሲል ኮሚቴው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

”ከአማራነታችን ዝቅ የሚያደርገን ምድራዊ ኃይል የለም!!”

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ አየለ

Leave a Reply