Site icon ETHIO12.COM

በእርግዝና ወቅት የማይመከሩ ምግቦች

1. ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል

እርጉዝ ሴቶች በፍጽም ጥሬ ወይም በከፊል የበሰለ እንቁላል መመገብ የለባቸውም። ጥሬ እንቁላል ለሳልሞኔላ ኢንፌክሽን አይነተኛ መነሻ ሲሆን፤ ኢንፌክሽኑ ማስመለስና ተቅማጥ ያስከትላል። ይህም የልጅዎን ጤንነት ይጐዳል።

እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚንና ሚኔራሎች ጥሩ መገኛ ነው። ስለዚህ እንቁላል ሲመገቡ በሚገባ መብሰሉን ያረጋግጡ።

2. አልኮል መጠጦች

እርጉዝ ሴቶች በሚያስከትለው አሉታዊ ውጤት ምክንያት አልኮል ከመጠጣት መታቀብ አለባቸው። አልኮል መጠጣት የሚከተሉት የጤና እክሎች የመከሰት ዕድላቸው እንዲጨምር ያደርጋል፤ የህፃኑ የጤና ሁኔታ ለማስጨንገፍ (ማስወረድ)ና ፌታል አልኮሊክ ሲንድረም እና ለመሳሰሉት ችግሮች ይዳረጋል።

3. ቡና መጠጣት

በእርግዝና ወቅት ነፍሰ ጡር ስቶች (እናቶች) የሚጠጡትን የቡና ብዛት መመጠን አለባቸው። ከፍተኛ የካፌይን መጠን ሲወሰድ አነቃቂ ነው ይህም የህፃኑን የልብ ምት መጠን ያስተጓጉላል።

በተጨማሪም ካፌይን ዝቅተኛ ክብደት ያለው ህፃን የመውለድና የማስጨንገፍ ዕድልን ይጨምራል። በብዛት ከተጠቀሙ ደግሞ ድርቀትን ያስከትላል።

4. ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን ያለው አሳ

አሳ ጤናማ የኦሜጋ – የፋቲ አሲድ መገኛ ነው። ነገር ግን በእርግዝና ወቅት የሜርኩሪ ይዘታቸው ከፍ ያሉ አሳዎችን ከመመገብ መቆጠብ አለባቸው። ከፍተኛ የሜርኩሪ መጠን የህፃኑን የአእምሮ ዕድገትና የነርቭ ሥርዓትን ስለሚያስተጓጉል ከፍተኛ ጥንቃቄን ይሻል።

5. ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ስጋ

በፍጽም ጥሬ ሥጋ አይመገቡ በተለይ ነፍሰ ጡር ከሆኑ። ጥሬ ወይም በሚገባ ያልበሰለ ሥጋ መመገብ በፓራሳይት አማካይነት የሚከሰተው የቶክሶፕላስሞሲስ ኢንፌክሽን የመያዝ አደጋን ይጨምራል ይህም ገና ያልተወለደ ህፃንን ጤና ይጐዳል።

6. ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ

እርጉዝ ከሆኑ ወይም ለማርገዝ ሙከራ እያደረጉ ከሆነ ያልበሰለ ፓፓያ በፍጽም አይመገቡ። ጥሬ ወይም በደንብ ያልበሰለ ፓፓያ በብዛት መመገብ ልክ እንደ ማስጨንገፊያ መድሃኒቶች በመሆን ይሠራል። ስለዚህ ያልበሰለ ፓፓያ በብዛት መመገብ ማስጨንገፍ (ማስወረድ)ን ያስከትላል።

7. ለስላሳ አይብ

በእርግዝና ወቅት ለስላሳ አይብ መመገብዎን ያቁሙ። በአብዛኛው እነዚህ ለስላሳ አይቦች የሚዘጋጁት ፓስቸራይዝድ ካልሆነ ወተት ነው። እነዚህ ለስላሳ አይቦች በውስጣቸው ሊስቴሪያ የተባለ ባክቴሪያ ሊይዙ ይችላሉ። ይህ ባክቴሪያ ማስጨንገፍ፣ ያለጊዜው (ያለ ዕድሜ) ወሊድና በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ ህመም እንዲኖር ያደርጋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ -ጤና

Exit mobile version