Site icon ETHIO12.COM

የም.ዕዝ ጦር ማይፀብሪ ገብቷል፤ አላማጣና አካባቢው ላይ ያለ ሰራዊት ለቆ እንዲወጣ ተድርጓል

ሮይተርስን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አላማጣን እንደተቆጠጠር በትላንትናው ዕለት ዘገበዋል። ይህንኑ ዘገባ የተለያዩ የአገር ውስጥ ሚዲያ ሰራተኞች የራሳቸውን ምንጭ በመጠቀስ ሲገልጹ አምሽተው ነበር።

ዛሬ ባደረግነው ማጣራት የመንግስት ሃይል አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ መደረጉ ታውቋል። በሌላ ግንባር ያልተሳካ ማጥቃት ቢሰነዘርም ትህነግ እንዳሰበው አልቀናውም። ይልቁኑም የምዕራብ ዕዝ ማይጸብሪ መግባቱን አረጋግጠናል። ማይጸብሪ እጅግ ቁልፍ የስትራቴጂ ቦታ እንደሆነች ተመልክቷል።

አላማጣና አካባቢው የነበረ ሰራዊት አርባ የሚጠጉ የረሃብ ማስታገሻ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እንዲያልፉ በተከፈተበት ወቅት ብዙም ሳይቆይ መከላከያ ለቆ እንዲወጣ ሲደረግ የትህነግ ሃይል ከተማዋን በቀላሉ ተቆጣጥሯል። ጎበዜ ሲሳይ የሚባለው የኢሳት ሪፖርተር በፌስ ቡክ ገጹ እንዳለው ” ድንበራችን ነው ብለው ከሚያስቡት በዋጃ እና በቆቦ ማህል በምትገኝ አንስተኛ ወንዝ ላይ ቆመዋል” ሲል እማኞች ጠቅሶ ለጥፏል።

ሰራዊቱ ለምን አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ እንደተደረግ እስካሁን ምላሽ አልተሰጠም። መከላከያም በገሃድ ያለው ነገር የለም። አሜሪካ የሁሉም ጉዳይ መረጃ ባለቤትና አስቀድሞ ጠንሳሽ በመሆኗ ” በአጻፋ እርምጃ እንዳይወሰድ” መለቷ በጦርነቱ ውስጥ እጇ ስለመምኖሩ አመላክች እንደሆነ እየተጠቆመ ነው።

አሜሪካ ይህን ብትልም የኮረም ፤ የአላማጣ እና የዋጃ ሕዝብ የትህነግ ሃይል እንዳይጨፈጭፋቸው ሰግተዋል። የቻሉም ከተማዋን ለቀው መሸሻቸውን የሚያሳይ መረጃ በስፋት እየተሰራጨ ነው።

የአማራ ክልል የስንቅና የህይወት ድጋፍ እንዲደረግ በይፋ አውጇል። የክልሉ መሪ በይፋ ትህነግ አማራ ላይ ጦርነት እንዳወጀ አመልክተዋል። በአማራ ክልል በኩል የሚወጡ የክተት ጥሪዎች ወደ ተግባር እየተቀየሩ እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። ስንቅ የሚያዘጋጀው የደጀን ሃይሉም በዚሁ ተግባር መጠመዱን የሚያሳይ መረጃ በምስል እየታየ ነው።

አማራ ክልል ” የህልውና ” ሲል የጠራው ይህ ራስን የመከላከል ጦርነትና፣ ትህነግ ስልጣን ሲይዝ አካለለው የተባለው ቦታ ድረስ እስከሚደርስ ውጊያ እንደማያቆም ማስታወቁ በመነጋገር ሊፈታ የሚችል ጉዳይ ስለመሆኑ እስካሁን ፍንጭ የለም።

መንግስትም ሆነ አማራ ክልል ከትህነግ ሃይሎች ጋር ጉዳዩን በፖለቲካ አግባብ ለመፍታት እንደሚቻል የሰጡት ምልክት የለም። ትህነግም ወደ መቀለ ከተመለሰ በሁዋላ በአውሮፓዊያኑ፣ በአሜሪካና በዓለም አቀፍ ተቋማት ያለውን ድጋፍ ተጠቅሞ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ አይዘነጋም።

ሕዝብ ከጦር ሜዳ በሚወጡ እጅግ የፈጠኑ ተለዋዋጭ መረጃዎች መደናገሩ ታውቋል። የመከላከያ ሰራዊት አመራሮችም ሆነ መንግስት ይፋ አያድርጉት እንጂ አሜሪካ በከፍተኛ ደረጃ አንድ ሁለት ብላ ያስቀመተቻቸው ገደቦችና መመሪያዎች መንግስትን እጅና እግር አልባ እንዳደረገው መረጃዎች አሉ። በተለያም የዚህ ሁሉ ችግር ምክንያት የሆነው የህዳሴው ግድብ በመሆኑ፣ በግድቡ ዙሪያ አሜሪካ የቤት ስራ የሰጡዋት አገራት በሚፈልጉት ዓይነት መልኩ እየታዘዘ የሚመራ አዲስ መሪ “እስኪመደብ” ጫናውን በፍልሚያው ላይ የሚደረገው ድጋፍ እንደማይቆም ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቡይ በቅርቡ ስም ሳይጠቅሱ ” ውረዱ” ያሉ አገሮች መኖራቸውን ” ጉዳዩ የግለሰብ አይደለም” የሚል ምላሽ መስጥታቸው አይዘነጋም።

ጦርነቱ ከመጀመሩ ወራት በፊት የኢትዮጵያን ጦር የማፍረስ ዕቅድ እንዳለ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አሁንም ” የአብይ ጦር፣ የብልጽግና ጦር” በሚል የአገር መከላከያን በመጥራት የሚደረገው ቅስቀሳና የአሜሪካ አካሄድ ” ያልተገባ ጫና በማድረግ 115 ሚሊዮን ሕዝብን አደጋ ላይ መጣል አውሮፓን በስደት፣ አሜሪካን በደህንነት ጉዳይ ኪሳራ ይጥላታል” በሚል ዘመቻ የጀመረ ድርጅት አነጋገረን ማተማችን ይታወሳል።


Exit mobile version