Site icon ETHIO12.COM

“አሳስቦኛል”ብላ አሜሪካ ወልቃይት ላይ ፈረደች፤ “አገር አቀፍ ክተት ባስቸኳይ ይጠራ”

የአሜሪካ መንግስት ወልቃይትን ትህነግ እስኪቆጣጠር ደርስ ውጊያውን ማቆም እንደማይቻል በግልጽ ያስታወቀበትን መግለጫ ልክ እንደ አንድ የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ፕሮፓጋንዲስት ነው ያነበበው። በሌላ በኩል ህዝብ መንግስት በገሃድ ክተተ መጠራት እንዳለበት እየተናገረ ነው።

በምጽራብ ትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንደሚያሳስባት ለውሳኔዋ ማሟሟቂያ የተጠቀመችው አሜሪካ፣ ውጊያው ከቀረ ለትግራይ ተጎጂዎች የእርዳታ እህል ለማስገባት የተጀመረውን ጥረት ያደናቅፋል ስትል ወልቃይት በትህነግ እጅ እስኪገባ” ያሳበኛል፣ ግን ትህነግ ይግፋ ወይም ልቀቁለት” ስትል አዙራ አስታውቃለች።

ወልቃይት በትህነግ እጅ እንደሚገባ ሰዓትና ቀኑንን ባትጠቅስም አሜሪካ ” በትግራይ ክልል አጻፋዊ ጥቃት እንዳይፈጸም አስጠነቀቃለሁ” ብላለች። ይህን የተከታተሉ በመላው አገሪቱ ክተት እንዲታወጅ እየጠየቁ ነው። መግለጫውን ያንብቡ።

ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የተሰጠ መግለጫ

አሜሪካ በምዕራብ ትግራይ እየተካሄደ ስላለው ጠብ እና ወታደራዊ ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱን እጅግ አሳስቦናል። ውጊያውን ማስቀረት በትግራይ ውስጥ በረሀብ ለተጎዱ ህዝቦች የሰብአዊ ዕርዳታን ለማድረስ ወሳኝ የተጀመሩ ጥረቶችን ያዳክማል፡፡

የትግራይ መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ክልል ኃይሎች እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት በክልሉ ውስጥ ላሉ ሰላማዊ ሰዎች ፍላጎት ወደ ድርድር የተኩስ አቁም እንዲንቀሳቀሱ እና የኢትዮጵያን መንግስት አንድነት እንዲጠብቁ በድጋሚ እንጠይቃለን፡፡ በተደራጁ ወታደራዊም ይሁን በደህንነት ኃይሎች ወይም በሌሎች አካላት በትግራይ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመ ወይም ሊሆን የሚችል ማንኛውንም የአፀፋዊ ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን። አሜሪካ የታጠቁ አካላት ሁሉ የዜጎችን ጥበቃን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጋዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ ጥሰቶች እና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑት ሁሉ በሕግ መጠየቅ አለባቸው፡፡

በተከታታይ እንደገለጽነው የኢትዮጵያን ውስጣዊ ድንበሮች በኃይል ለመለወጥ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ተቀባይነት የለውም። እንደ ድንበር ያሉ አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸው ማንኛውም ጉዳዮች የኢትዮጵያ በመግባባት ውይይት እንዲወስን መደረግ አለበት።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ ላይ ያስተላለፈው መልአክት

Statement from US Department of State on Ethiopia.

“United States is gravely concerned by reports of ongoing hostilities in western Tigray and evidence of escalating military conflict there. Escalating fighting will undermine critical ongoing efforts to deliver humanitarian relief to famine-affected populations in Tigray

We again call on the Tigrayan Defense Forces, the Amhara regional forces, and Ethiopian National Defense Forces to move towards a negotiated ceasefire in the interests of civilians in the region and to preserve the unity of the Ethiopian state. We strongly condemn any retaliatory attacks that have been or may be directed against civilians in the Tigray region, whether by organized military or security forces or by rogue elements. The United States further calls on all armed actors to comply with their international humanitarian legal obligations, including regarding the protection of civilians. All those who are responsible for violations of international humanitarian law and human rights abuses must be held accountable.

As we have consistently said, any effort to change the internal boundaries of Ethiopia by force is unacceptable. Any issue of such national importance, like borders, would be an issue for the Ethiopian people to decide through consensual dialogue, not by the barrel of a gun.”


Exit mobile version