Site icon ETHIO12.COM

ኢምፔሪያሊስት አሜሪካና አሽከሮቿ ምዕራብ አውሮፓ ኢትዮጵያን ለምን ጠሏት?


የኢትዮጵያን ታሪክ ለማያውቅ ግራ ሊጋባ ወይም አረመኔዋ፣ ሰው በላዋ አሜሪካ ሰው እንዳይሞት ብላ ሊመስለው ይችላል። ምክንያቱ ወዲህ ነው

  1. ኢትዮጵያ አንድ ሰልጥኛለሁ፣ መጥቄያለሁ የምትል የነጭ ፈረንጅ ሀገር ጣልያንን በ 1888 ዓም በእምዬ ምኒልክ ዘመን እና በ1933 ትብያ፣ ዱቄት አድርጋ አሸንፋለች። አሜሪካ ኢትዮጵያን ነጭ ህዝብን The white race ያዋረደች ብቸኛ የጥቁር ሕዝብ ሀገር ናት ብላ ትጠላታለች
  2. ኢትዮጵያ በ 1945 ዓም የተመድ መስራች አባል ሆና በተመድ ስብሰባዎች ላይ በቅኝ ግዛት ስር የሚማቅቁ አፍሪካውያን ነፃ እንዲወጡ በማሳሰብ ቅኝ ግዛትን ከሚቃወሙ የምስራቁ ጎራ ተሰልፋ ተግትጋቸዋለች። በዚህም አሜሪካ ቂም ይዛ ኢትዮጵያን ትጠላለች
  3. ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ስር የሚማቅቁ አገሮች ለነፃነት ለሚያደርጉት ትግል በገንዘብ በመሳርያ በወታደራዊ ስልጠና ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች። መንግስቱ ኃማ ዚምባብዌ ተንቀባሮ የሚኖረው ኢትዮጵያ ለዚምባብዌ ትግል በገንዘብ፣ በመሳርያ በወታደራዊ ስልጠና ባደረገችው እርዳታ ነው። ለጥቁር ነፃነት በመቆማችን ትጠላናለች
  4. ኢትዮጵያ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ስርዓት እንዲወድም አዲስ አበባ ፅቤት ከፍታላቸው ለማንዴላ ጭምር ወታደራዊ ስልጠና ሰጥታለች። ማንዴላ
    በኢትዮጵያ ፓስፖርት ኢትዮጵያዊ ተብሎ እንዲንቀሳቀስ ፈቅዳለች። ማንዴላ ለ27 ዓመት እስር የተዳረገው ከኢትዮጵያ ወታደራዊ ስልጠናውን ጨርሶ እንደተመለሰ ነው።ማንዴላ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስሄድ ጥቁር ፓይለት ሳይ ደነገጥኩ ኮራሁም ይላል። ማንዴላ ከኢትዮጵያ ስልጠና ጨርሶ ያሳሰሩት ኢትዮጵያ የነበሩ የሲአይኤ ሰላዮች ናቸው። በዚህም ምክንያት የጥቁር ሕዝብ ኩራት ሆነች ብለው ኢትዮጵያን አሜሪካኖች ይጠሏታል።
  5. ኢትዮጵያ የገለልተኛ አገሮች ንቅናቄ መስራች አባል ነበረች። የአሜሪካ ጭፍራ የሲአይኤ ቡችላ አልሆንም በማለቷ ይጠሏታል
  6. ኢትዮጵያ በ1955 ዓም ነፃ የወጡ አፍሪካ አገሮችን አዲስ አበባ ላይ ሰብስባ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አቋቁማ ፀረ ቅኝ ግዛት ንቅናቄ በማስተባበሯ ይጠሏታል።
  7. ግብፅ ምን ጊዜም ጠላት መሆኗ ቢታወቅም የፕሪንስፕል ጥያቄ ሆኖብን በ1965 ዓም ግብፅን ደግፈን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከእስራኤል ጋር በማቋረጣችን አሜሪካ ቂም ይዛ ጠልታናለች። በ 1984 ፕሮፍ እስራኤል ኢትዮጵያን ከድታለች፣ የእስራኤል አምላክ እያልን ተጎዳን ከአረቦች ጋር ብዙ የጋራ የሆኑ ነገሮች ስላሉን ከአረብ አገሮች ጋር ግንኙነት ማጠናከር አለብን ብለው ስለፃፉ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ኢትዮጵያ ናት የከዳችን እኤአ በ1973 ዴፕሎማቲክ ግንኘነታችንን አቋርጣችኋል ብሎ መልስ መስጠቱ ቂም እንደያዘብን ማስረጃ ነው።
  8. ኢትዮጵያ መሬት አንቀጥቅጥ የሶሻሊስት አብዮት አካሂዳ የአሜሪካንን ወታደራዊና ማንዴላን ያሳሰሩ የስለላ ተቋማት በሞላ USMAG, USNAMRU etc በማባረሯ ቂም ይዘው ይጠሏታል
  9. ደርግ ከወደቀ በኋላ ከቻይና ጋር የተጧጧፈ የንግድ ትስስር መስርተን ብዙ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ንግዳቸው ከቻይና ሀገር በመተሳሰሩ ፣ አፍሪካን እንዳለ ወደ ቻይና ወሰዱብን የቻይና መንግስት በኢትዮጵያ ከሚዘረጋው ኢንፍራስትራክቸር በተጨማሪ ለአፍሪካ ህብረት ሁሉ ትልቅ ግዙፍ ህንፃ በነፃ ሰርቶ ሰጠ በማለት አሜሪካ ጠልታናለች

መፍትሔ

ልምምጥ አይጠቅምም።

እልም ነው ጭልጥ ነው
ውሐ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም

ግጭትም ጉዳት አለው

የሚቻል ከሆነ ቶም ኤንድ ጀሪ መጫወት፣ ምንም ጊዜ ጀሪን መሆን ይበጃል።
ቶም ኤንድ ጀሪ ጌም ካልሰራ አማራጫችን በመስተዳድሩ ውሳኔ ሳይሆን ፓርላማ አቅርበን ሰፊ ውይይት ተደርጎ፣ ጥቅምና ጉዳት ተመዛዝኖ የግድ ሳንወድ የሚደርስብንን ሁሉ መከራ ችለን ዲፕሎማቲክ ግንኙነት እስከማቋረጥ መሄድ መቻል አለብን።
በምንም ተዐምር ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል እንጨፍለቅ፣ ቀጥ ብለን እንሙት እንጂ ማጎብደድ የለብንም

Guangul Teshager J

Exit mobile version