Site icon ETHIO12.COM

ጨፌ ኦሮሚያ በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን በ”ጀግና” ማዕረግ እንዲጠሩና ቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ ወሰነ

በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩ ጨፌው ወሰነ። ኢዜአ እንዳለው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከማዕረጋቸው በተጨማሪ “ጀግና” ተብለው እንዲጠሩና ማንኛውንም አገልግሎት ሲፈልጉ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) የወሰነው ዛሬ ነው።

ዛሬ በተጀመረው የጨፌው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው መክፈቻ ላይ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እውቅና መስጠት የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ አቅርበው ፀድቋል።

አፈ ጉባኤዋ በማብራሪያቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑን ገልጸዋል።በሰሜን ኢትዮጵያ አሸባሪው የህወሃት ቡድን የፈፀመውን የአገር ሉዓላዊነት የመድፈር ወንጀል ሰራዊቱ በከፍተኛ ጀግንነትና መስዋእትነት ጭምር መቀልበሱን ጠቅሰዋል። “በዚህም ለአገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል።

በውሳኔ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላ ከላቸው ማንኛውም ማዕርግ በተጨማሪ ” ጅግና” የሚል የክብርና ተጋድሏቸውን የሚያደነቅ የክብር ስያሜ ይኖራቸዋል። ምክር ቤቱ ይህን ውሳኔ መወሰኑ ለሁሉም ምሳሌ እንደሚያደርገው ይገመታል።

ኦሮሚያ ክልል አሸባሪውን ሃይል “ለህልውናችን ያሰጋናል” ሲል ወደ ግዳጅ ቀጠናው ሰራዊት ማሰማራቱ ይታወሳል።

Exit mobile version