Site icon ETHIO12.COM

ክብር- ለኢትዮጵያ ጦር


(አሳዬ ደርቤ)

ጀግኒት እንዳለችው ‹‹ክልሉን ለማስከበር የአማራ ልዩ ሃይልና ሚኒሻ ከበቂ በላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን አንድነት ለማሳየት ግን የሁሉም ክልል ደጀንነትና ሕብረት ያስፈልጋል፡፡››

ትሕነግ በሽፍትነት ከኖረበት የደደቢት በረሃ ወጥቶ ቤተ-መንግሥት ውስጥ እስኪሸብት ድረስ አማራን በጠላትነትና በአሀዳዊነት ሲፈርጅ ብሎም ይሄን ሕዝብ ይታገሉ ዘንድ ብሔር ብሔረሰቦችን ሲያደራጅ የኖረ ድርጅት ነው፡፡

የብሔር ብሔረሰቦችን ማንነት ማስከበር ቀርቶ ቁጥራቸውን በውል ማወቅ ተስኖት ‹‹ከሰማንያ በላይ›› እያለ አማራ ጠልነት የፌደራሊስትነት መገለጫ ይሆን ይመስል እልም ያለ በዝባዥ አሃዳዊ መንግሥት መስርቶ ሲዘርፍና ሲያወናብድ የኖረ ፓርቲ ነው፡፡

በጌታቸው ረዳ አንደበት ‹‹እሳትና ጭድ›› ተብለው በተገለጹት ሕዝቦች ትግል ከፌደራል ከተባረረ በኋላም ሲነዛቸው የነበሩ ፕሮፖጋንዳዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማንነት ቀምተው በአማራነት የሚፈርጁ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብን ለእርስ በእርስ መጠፋፋት የሚያዘጋጁ፣ ከአማራዎች ይልቅ ሱዳኖች ወዳጁ መሆናቸውን የሚያውጁ ነበሩ፡፡

የመከፋፈል ፍልስፍናውን በማጠናከርም ከግብጽና ሱዳን የሚላክለትን ድርጎ ኢትዮጵያን መሰነጣጠቅ ለሚፈልጉ ድርጅቶችን ሲያካፍልና ሲያስታጥቅ ነበር፡፡
ኢሳያስን ወዳጅ ማድረግ እንደማይቻል ሲገባውም ኤርትራውያንን ‹‹ቆለኞቹ›› እና ‹‹ደገኞቹ›› እያለ ከመከፋፈል ባለፈ ፕሬዝዳንቱን ለማስገደልም ሲጣጣር ነበር፡፡ (ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ሥም የተደራጀውን የሰሜን እዝ ላይም ጥቃት ሲፈጽምም በማንነት ሸንሽኖ ነበር፡፡)

ታዲያ የትሕነግ አሸናፊነት በመከፋፈል መርሕ ላይ የተመሠረተ እንደመሆኑ ሽንፈቱና ሞቱ ደግሞ ከኢትዮጵያ አንድነት የሚቀዳ ነው፡፡ በመሆኑም ትሕነግ ከሰሞኑን ያጋጠመው መራር ሽንፈት መንታ ሆኖበታል፡፡ በዚህም መሠረት የሚፎክርበት ታጣቂው በሠዓታት ውስጥ በአማራ ሠራዊት ተለብልቦ ከመሸኙቱም በላይ ከየስፍራው በሚተምመው የኢትዮጵያ ሠራዊት ደግሞ በውሸት ጡብ የተገነባ ስነ ልቦናውን አንኮታኩቶ ‹‹ወደ ራያ የሄድኩበት እግሬ በተሰበረ ኖሮ›› ብሎ እንዲመኝ አድርጎታል፡፡

➜ትሕነግ ብልጥ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሞኛ ሞኝ ድርጅት በመሆኑ ሲዳማ ክልል ስትሆን ‹‹እልልልልል›› የሚል መግለጫ ስላወጣ ብቻ የሲዳማ ሕዝብ በእልልታ የሚምታታ ይመስል መላሹን ክዶ ከአፋኙ ጋር የሚሰለፍ ይመስለዋል፡፡

➜‹‹የትኛውም ሕዝብ ያስባል›› ብሎ ስለማያስብ አንድ የወላይታ መምሕር ጋብዞ ‹‹አጼ ምኒልክ በወላይታ ሕዝብ ላይ ግፍ የመፈጸም ሐሳብ ነበረው›› ማስባል ከቻለ ድፍን የወላይታ ሕዝብ ከእሱ ጋር የተሰለፈ ያህል ይሰማዋል፡፡

➜ልክ እንደሱ ቀየ ዳውድ ኢብሳና የኦሮሞ ሕዝብ አንድ ሆነው ይታዩታል፡፡ አብዲ ኢሌና ሶማሌ ይምታታበታል፡፡

የሰሞኑ ዘመቻ ታዲያ ወደ ሞት ቀጠና ከሚነዳው ሠራዊት ባለፈ ክልሉን እና እራሱን ሲደልልበት የኖረውን የውሸት ትርክት አፈር ድሜ ያስበላ ነው፡፡
በዚህም መሠረት፡-

አገኘሁ ተጣርቶ- ጌታቸው አቅራርቶ- ፎክሮ ሳይጨርስ
ከገብርዬ ጋራ- መቃብር ፈንቅሎ- ተነስቶ ቴዎድሮስ
በኮረም ማይጸብሪ- ባንዳ እና ከሃዲን- ሲጀምር መደምሰስ

የአብደሳ አጋ ወራሽ፥ የአቢቹ፣ የባልቻ
ጸረ አገርን መቅበር፥
ማነው የፈቀደው፥ ለአማራዎች ብቻ?
ከሚል ጥያቄ ጋር፥
አገሩን ሊታደግ፥ ድንገት ከተፍ ሲል፤
እንቆቆ እየጠጣ
አፋሩ፣ ሲዳማው፥
ሶማሌው ደቡቡ፥ ጋምቤላው ሲከተል፤

ያጋጠመው ሽንፈት፥ ያ የአንጀት ኮሶ ትል
ከአገሬው ሆድ ወጥቶ- ከኪሲ እንደመጣል፡፡💪

Share

Exit mobile version