Site icon ETHIO12.COM

አክቲቪስት – የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ

የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ትግራይን የተመለከቱ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው

ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለመላው የዓለም ህዝብ ወኪል ሆነው የአለም ጤና ድርጅትን በዋና ዳይሬክተርነት እያገለገሉ ቢሆንም ለአንድ በአሸባሪነት ለተፈረጀ የህወሓት ቡድን ሽፋን ለመስጠት እየተንቀሳቀሱ ያሉ ይመስላል።

ድርጊታቸው እንደ አንድ የዓለም ዓቀፍ ድርጅት መሪ ሳይሆን ወገንተኛነት የተጫነው የአንድ ቡድን አክቲቪስት መምሰል ከጀመሩም ውሎ አድሯል።

በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የህወሃት ቡድን የአገርን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በማድረስ ቀይ መስመር በማለፉ የህግ ማስከበር እንደተወሰደበት ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የቡድኑ ስራ አስፈጻሚ አባል ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ የዓለም ዓቀፍ ተቋም እየመሩ ቢገኙም ዛሬም የቡድኑን ጥፋት ለመሸፋፈንና ነፍስ ዘርቶ እንዲመጣ ለመደገፍ እይተፍጨረጨሩ ይገኛሉ።

ባለፈው አንድ ወር ብቻ የግለሰቡን ማህበራዊ ገጽ ብንመለከት ስለሌላው ዓለም አንድም ነገር ሳይተነፍሱ አሸባሪውን ቡድን በመደገፍና የኢትዮጵያን መንግስት ለመወንጀል በሚመስል መልኩ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

መልዕክት ብቻ ሳይሆን አሁን አሁን ፍላጎታቸው ግልጽ እየሆነ የመጡ መገናኛ ብዙሃንን የተሳሳቱ መልዕክቶች አጋርተው ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ሞክረዋል።

በተለይ መንግስት ወቅቱ የእርሻ በመሆኑ አርሶ አደሩ ይረስ፣ የትግራይ ህዝብም የጥሞና ጊዜ ይሰጠው በሚል የወገተኝነት ስሜት መቀሌን ለቆ በወጣበት ወቅት የህወሓት አሸባሪ ቡድን የደረሰበትን የስነ ልቦና ስብራት ማካካሻ እንዲሆነው አሸንፌ መቀሌን ተቆጣጠርኩ ማለቱ ይታወሳል፡፡

የህወሓት አሸባሪ ቡድን መቀሌ መግባቱን ተከትሎም በተለያዩ የአለም ሃገራት የሚገኙ የቡድኑ ደጋፊዎች “አሸነፍን” እያሉ በተለያዩ ማህበራዊ ገጻቸው ህዝብን ለማደናገር ሞክረዋል።

ለአብነትም ከነዚህ አደናጋሪ መልዕክቶች መካከል “እውነት ያሽንፋል” “ኮራሁ” የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች የወቅቱ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ናቸው፡፡

በማይናማር፣ ከሰሞኑ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ስለሆነው ነገር ግድ ያልሰጣቸው ዶክተር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን ለመወንጀል እየተካሄደ ያለውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ መታየታቸው ግለሰቡ የዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ተወካይ ሳይሆኑ፤ የአንድ አሸባሪ ቡድን አክትቪስት መሆናቸውን ያሳብቅባቸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version