Site icon ETHIO12.COM

“አሸባሪው ትህነግ” በአፋር በኩል ከተሳካለት የጅቡቲ መስመር ለማወክ፣መሰረተ ልማት ለማውደም ተመኝቷል

የአሸባሪው ትህነግ ቃለ አቀባይ ጌታቸው ረዳ ሳምንቱን ሙሉ በአፋር በኩል ውጊያ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያመነበትን ሪፖርት ያቀረበው ሮይተርስ ” አፋር ቁልፍ ወታደራዊ ጠቀሜታ አላት” ሲል ያትታል። ጌታቸውን ሳይጠቅስ ይህንኑ ያለበትን ምክንያት ይዘረዝራል።

ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ ብቸኛ የባህር መገልገያዋ ጅቡቲ መሆኗን ሮይተርስ አስታውቆ፣ የባቡርና የተሽከርካሪ ጎዳና ከጅቡቲ ተነስቶ አፋርን በማቋረጥ ከአዲስ አበባ ጋር የሚገናኙበት እንደሆነ ያስረዳል።

Afar is strategically important because the road and railway linking the capital Addis Ababa to the sea port of Djibouti run through it. Djibouti is landlocked Ethiopia’s main access to the sea.

ቀደም ሲል ከአሸባሪው ቡድን ዘንዳ ሲወጡ የነበሩት መረጃዎች አሰብን የመያዝ ዕቅድ እንዳለ የሚያመላክት ቢሆንም አሁን በአፋር በኩል የውጊያ ቀጠናውን በማስፋት የመሃል አገሩን እንቅስቃሴ ለማወክ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ የአዲስ አበባን ጉሮሮ ለመዝጋት ያቀደ መሆኑ ታውቋል።

ዕቅዱ ምን ያህል ይሳካል ወይም አይሳካም የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ የጁንታው ሃይል በአፋር በኩል የጀመረው ትንኮሳ የአፋርን ድንበር የመውሰድ ወይም የመድፈር እንዳልሆነ ጊታቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል። በዘገባው የመንግስትን አቅም ማዳከም እንደ ዓላማ መያዙም ተጠቁሟል።

በሱዳን በኩል ወልቃይትን አስለቅቆ ከሱዳን ጋር የሚገናኝበትን ኮሪዶር በማስከፈት በማይካድራ ጭፍጨፋ ፈጽመው ያመለጡ 30 ሺህ የታጠቁ ወታደሮቹን ለማስገባት አቅዶ እንዳልተሳካለት ፋይናንሻል ታይም ሁለት ጊዜ በቀያየረው ሪፖርቱ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ጌታቸው ረዳና ጻድቃን “ገና ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለ” ማለታቸውን ተከትሎ ቁጣው የገነፈለው የአማራ ህዝብ በፈቃደኛነት ” ክተት” ካለ በሁዋላ ከድበሩ በማለፍ አፋር ክልል ላይ ጥቃት የሰነዘረው የአሸባሪው ሃይል አፋር ክልል ገብቶ ተኩስ መክፈቱንና ሳምንቱን ሙሉ ጦርነት መክፈቱን አልካደም።

ይህንኑ ተከትሎ በክልሉ ለተከሰተው ረሃብ የሚውል ቀለብ ወደትግራይ እንዳያመራ መስተጓጎሉን የትባበሩት መንግስታትን የምግብ ድርጅት ጠቅሶ ያስታወቀው ሮይተርስ መስተጓጎሉን ማን እንደፈጠረው አልገለጸም። የምግብ ድርጅቱም ቢሆን ገና የሚጣራ መሆኑንን ነው የተናገረው።

ጌታቸው ረዳ በአፋር ድንበር ጥሰው ጦርነት መክፈታቸውን አደባባይ ቢያስታወቅም የዓለም የምግብ ድርጅትም ሆነ ሌሎች ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በገሃድ አሸባራዊን ሲያወግዙ አልተሰማም። እንደሚሰማው ከሆነ ዓላማው በሰመራ ሳይሆን በሱዳን ኮሪደር እንዲከፈት ለማስገደድ የተደረገ መሆኑ ነው።

በአፋር በኩል ግጭት መኖሩን ክልሉን ጠቅሰው የሚዘግቡ የውጭ ሚዲያዎች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ ከአፋር ግጭት ጎን ለጎን እየገለጹ ያሉት በምዕራብ ትግራይ (በወልቃት ማለታቸው ነው) ኮሪዶር መከፈት እንደሚገባው ነው።

ይህ ሁሉ ሲሆን መንግስት ዛፍ እየተከለ፣ ወታደሮቹ ልማትና ዳግም አቋቋም በማስተካከልና በግልጽ ላልተነገረ ጥቃት መዘጋጀቱን ከማስታወቁ ውጭ ያለው ነገር የለም። ክልሎችም ” አሸባሪው ትህነግ ያሰጋናል” በሚል ሃይላቸውን ወደ ሚፈለግበት ግንባር እየላኩ ነው።

የአማራ ክልል የኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ” አሸባሪው በሱዳን 30 ሺ ሰራዊት አለኝ” የሚለው ሃሰት ነው” ሲሉ ማጣታላቸው ይታወሳል። እሳቸው እንዳሉት ይህ ሃይል ከሱዳን ሊያስገባቸው የሚፈልገው ሳምሪ የሚባሉትን ባማይካድራ የዘር ማጥፋት የፈጸሙትን ሃይሎችን ነው።

በተመሳሳይ ዜና ለአሸባሪው የቅርብ ደጋፊዎች ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት ቡድኑ መሰረተ ልማት የማውደም እቅድ እንዳለው ገልጸዋል። ይህም የሚሆነው ” ተያይዘን እንፍረስ” ከሚለው አስተሳሰቡ የመነጨ ነው። የትህነግ አሸባሪ ቡድን ከክልሉ በመውጣት አገሪቱን ለማተራመስ ሲሞክር በተቃራኒው ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማገናዘብ አለመቻሉ በርካቶችን እያሳዘነ ነው።

“ቡድኑ ከክልሉ ወጥቶ ሌሎችን ለምን ያውካል? ከክልሉ ወጥቶ ሌሎችን ለማወክና ለመግድለ ምክንያቱስ ምንድ ሊሆን ይችላል?” በሚል የዜና ምንጮቹ ላቀረቡት ጥያቄ የአሸባሪዎቹ ደጋፊዎቹ ” ለትግራዋይ የማትሆን ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች” ሲሉ መልስ እንደሰጧቸው በጽሁፍ በላኩት መልዕት አመልክተዋል።

ደብረጽዮን ለቪኦኤና ጀርመን ራዲዮ ” ለኢትዮጵያ ህዝብ” ሲሉ ድርጅታቸው በታሪኩ ማንንም በጠላትነት ፈርጆ እንደማያውቅ፣ ኢትዮጵያንም እንዳትፈርስ አቅፈውና ደግፈው መያዛቸውን መናገራቸው ይታወሳል። እሳቸው ይህን ቢሉም አሁን የሚታየው ድርጅታቸው አፋር ገብቶ ግድያ በመፈጸም ላይ ነው።

ክልሉ እንዳስታወቀው የትህነግን አሸባሪ ቡድን ለመመከት እየሰራና አጻፋ እየመለሰ ሲሆን ግልጽ ባይነገርም አገር መከላከያም በበቂ ደረጃ ዝግጅት ማድረጉ ተሰምቷል። አካባቢው በአየር ለማጥቃት ስለሚያመች በሔሊኮፕተር ተዋጊዎች በመጠቀም ጠንካራ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚችል የሚገልጹ አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባለፈው እሁድ ” ማንን፣ መቼ፣ በምንና እንዴት እንደምናጠቃ” ሲሉ ለከባድ ጉዳይ ዝግጅት መደረጉንና አሸባሪው ሃይል ባጭር ጊዜ ሲነቀል ዓለም እንደሚያይ ምናገራቸው ይታወሳል።

Exit mobile version