ትህነግ ለሶስተኛ ጊዜ የሽንፈት ምክንያት ሰጠ፤ እነ ጻድቃን መከበባቸውን አመነ፤ አፋር አሽነፈ

“አሸባሪው ሕወሃት በመከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በቅንጅት በተውሰደበት ርምጃ በብዙ ኪሳራ ደርሶበት አፋርን ሙሉ በሙል ለቆ ወጥቷል” ሲሉ የክልሉ ሃላፊዎች አስታውቀዋል። ትህነግ “በሰሜን ግንባር የተጠናከረ ጥቃት ለመክፈት ስምሪት ቀይሮ እንጂ ተሸንፎ እንዳልወጣ ለሶስተኛ ጊዜ ምክንያቱን “ያሻውን ይዘግብለታል” ለሚባለው ለሮይተርስ አመልክቷል። ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው ሽንፈትን ለመደበቅ የሚደረግ ሽምጠጣ እንደሆነ አመልክተዋል። በየእርከኑ ያሉ ሃላፊዎች ” ሽሽትና ወንጀሉ ” እያሉ የሚያቀርቡት በመረጃ የተመረኮዘ ወንጀል ሕዝቡን እያስቆጣና “እንዝመት” የሚሉትን ዜጎች ቁጥር በስፋት እየጨመረ ነው።

” ጀግንነት መለያቸው የሆነው የአፋር ነበልባሎች ከመከላከያ ጋር ሆነው ትህነግን ደምስሰውታል። ታንክና በርካታ መሳሪያዎች ማርከዋል። ከሞት የተረፈው ሃይል ፈርጥጧል” ሲሉ የአፋር ባለስልጣኖች ጀብድ መሰራቱን አመልክተዋል። “ከማይታወቅ ቦታ በሳተላይት ነገሩኝ” ሲል ሮይተርስ አቶ ጌታቸውን ጠቅሶ እንዳለው ትህነግ ሰራዊቱን ወደ ሰሜን አዛውሮ እንጂ ተሸንፎ አፋርን አልለቀቀም።

ሮይተርስ አቶ ጌታቸውን “ለምን ወደ ሰሜን ሃይል ማዛወር ፈለጋችሁ? ምን ተፈጥሮ ነው?” በሚል ያነሳው ነገር የለም። ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች በማይጸብሪ ግንባር በኩል ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽም የነበረው የጀነራል ምግቢ ሰራዊት ከተደመሰሰ በሁዋላ በሰሜን አቅጣጫ በመግባት መከላከያ የቀድሞው ሌተናል ጄነራል ጻድቃን የሚመሩት ሰራዊት መከበቡ ተሰምቷል። ኢትዮ 12 የመረጃ ባለቤቶቹን ጠቅሶ ይህን መዘገቡም ይታወሳል።

አቶ ጌታቸው ለአፋር ሽንፈት የሰጡት መልስ ቀደም ሲል የትህነግ ሃይል ስለመከበቡ የወጡትን መረጃዎች ያጠናክራል። ትህነግ ወደ መቀለ ከተመለሰ በሁዋላ አቶ ጌታቸውን በመጥቀስ ” ካልታወቀ ስፍራ” እየተባለው የሚዘገበው ዘገባ ቀርቶ ነበር። ዛሬ ሮይተርስ ” በሳተላይት ስልክ ካልታወቀ ቦታ” በሚል አቶ ጌታቸውን መጥቀሱ የትህነግ አመራሮች ራሳቸውን ይፋ ማድረግ የሚፈሩበት ደእረጃ መድረሳቸውን የሚያሳይ እንደሆነም አስተያየት የሰጡ አሉ።

ቀደም ሲል ” ለአፋር ወንድም ሕዝብ ስንል” በሚል ወደፊት የማጥቃት ሃሳባቸውን መሰረዛቸውን፣ በቅርቡ ደግሞ “ለደሴ ካለን ፍቅር የተነሳ” በሚል ደሴን ለመያዝ የጀመሩትን ኦፕሬሽን ማቋረጣቸውን፣ አሁን ደግሞ ሰራዊታቸውን ወደ ሰሜን ማዛወራቸውን ለሽንፈት እንደምክንያት መዘርዘራቸውን ያስታወሱ ” በሁለት ሳምንት አዲስ አበባ፣ በሳምንት ጎንደር፣ በቀናት ልዩነት ደብረ ብርሃን …” ሲሉና በየደቂቃው ” መንገድ ምረጡልን፣ ማንኛውም አይነት ሃይል አያቆመንም” በሚል መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩት አቶ ጌታቸው፣ ከጦርነቱ ጎን ለጉን በርካታ ሪኮርድ ተመዝግቦላቸዋል። አሁንም እያጉረመረመ ያለውን ደጋፊዎቻቸውን ለማስታገስ በሚዲያቸው ወጥተው የሚሰጡት ትንታኔ ይጠበቃል።

See also  Ethiopia Concludes Election Peacefully, Daily Life Continues

አሸባሪው ሕወሃት ከአፋር ክልል በራሱ ለቆ እንደወጣ የሚያናፈሰው ወሬ እውነታነት የሌለውና በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በክልሉ ልዩ ኃይል በተወሰደው እርምጃ ብዙ ኪሳራ ደርሶበት መልቀቁን ቢለኔ ስዩም ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ በሰጠበት ወቅት በአግባቡ አብራርተዋል። አሸባሪው ሕወሃት በአማራ ክልል በዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በጅምላ የተጨፈጨፉት ህፃናት፣ እናቶች፣ ዲያቆን እና ቀሳውስት ቁጥር ከ200 በላይ መላቁን አመልክተዋል። ይህ ሽንፈት ሲገጥመው ከከርሱና ከዘረፋ የተረፈውን ሁሉ እያውደመ፣ እየገደለ የሚሸሸው አሸባሪ ሕዝቡን ከቀድሞው በላይ እያስቆጣ እንደሚገኝ ከየስፍራው የሚወጡ ሪፖርቶች ያስረዳሉ። እናት ልጆቹእን ጥላ ወደ ግንባር ለመዝመት የወጣችበት ስፍራ ሁሉ መኖሩ ተመልክቷል።

” ትህነግ ቀጣፊ” እንደሆነ ያስረዱት ቢልለኔ ስዩም፣ አሸባሪው ሕወሃት ከአፋር ክልል በራሱ ለቆ እንደወጣ የሚያናፈሰው ወሬ ሽንፈቱን ለመደበቅ ያሰራጨው እውነታነት የሌለው መረጃ መሆኑንም አመልክተዋል። የሽብር ቡድኑ በሀገር መከላከያ ሰራዊትና በአፋር ክልል ልዩ ኃይል እንዲሁም በአፋር ሚሊሻ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ብዙ ኪሳራ ደርሶበት ሊለቅ መቻሉን ዳግም አስታውቀዋል። እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ከስፍራው በወጡ የቪዲዮ ማስረጃዎች የጉዳቱ መጠን ታይቷል።

የሕወሓት የጥፋት ቡድን እየደረሰበት ባለው መራር ሽንፈት በተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃንን በጅምላ ከጨፍጨፍ ባሻገር ፣ በሰቆጣ በታዋቂው አትሌት ኃ/ገብረስላሴ የተገነባውን ትምህርት ቤት ጨምሮ ሆስፒታሎች፣ የመንግስት ተቋማትና የግለሰብ ሃብቶችን፣ የምስኪኖችን መኖሪያ፣ የቤት እንሣትና ሌሎች ትምህርት ወዘተ እንዳወደመ መገለጹና እየተገለጸ ነው።

Leave a Reply