በትናንትናው ዕለት የዞብል ሰንሰለታማ ተራሮችን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳና ቦረን ከተሞችን ተቆጣጥሯል መቆጣጠር መቻሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሲያስታውቅ እነ ጸጋዬ አራርሳ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን የሕዝብ ግንኙነት ተክተው “የተረጋገጠ ዜና” ሲሉ ጋሸና ዳግም በትህነግ እጅ መውደቋን ያስታውቁ ነበር። ድል የማስፋት ስራው “ኢጉታ፣ አቱካ”ን እየተበቁ ያሉ ሃይሎች ዝግጅት ማተናቀቃቸው እየተሰማ ነው።

የትህነግ ኮሙኒኬሽ ክፍል ከነ ጸጋዬ አራርሳ ሰበር ዜና ቀጥሎ በጋሸና በኩል 80 ሺህ በላይ ሰራዊት፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና ልዩ ሃይል መግደሉን፣ አስራ አንድ ክፍለጦርና ሰባት ብርጌድ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን ” በድል ሰበር ዜና” አመልክቷል። ከጋሸና አውቆ እንደወጣ ያስታወቀው ትህነግ ለምን በድጋሚ በጋሸና ውጊያ ለመክፈት እንዳሰበ አላስታወቀም። በአንድ ቀን ውጊያ ሰማንያ ሺህ ተዋጊ ሃይል መደምሰሱን ትህነግ ባስታወቀበት የማህበራዊ ገጹ የአስተያየት መስጫ ስር ከትህነግ ደጋፊዎች ወገን ዜናውን የሚያወድስ ሃሳብ አይታይም። ይልቁኑም ከኢትዮጵያ ወገን የሆኑቱ በዜናው ተሳልቀዋል።

በጋሸና መስመር አዲስ ውጊያ መከፈቱን መንግስት ሳይክድ “ጠላት ዋናው የቆቦ ወልድያ መንገድ ስለተዘጋበት በድንብርብር በጋሸና ላሊበላ በኩል ለማምለጥ ከፍተኛ ትንቅንቅ ቢያደርግም በወገን ጥምር ጦር እንደ ቅጠል ከመርገፍ አልተረፈም” ሲል ነበር የጋሸና መስመር ላይ የተደረገውን ውጊያ ያስታወቀው።

” የአማራ ቴሌቪዥን በትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ የተመራ ልዑክ ቡድን በጋሸና ከተማ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ሲጎበኙና መልሶ ስለመገንባት ሲመክሩ በቪዲዮ አስደግፎ ፍርስራሹ መካከል፣ እወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያሳይ ሪፖርት ሲያቀርብ ነበር። ዜናው በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍም እንደነበር ታዝበናል” ሲሉ አስተያየት የሰጡእ አሉ።

Image

በአፋር ፈንቲ ረሱ በጎሊና ግንባር አቅጣጫ የተነሳው የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት ከራያ ቆቦና አካባቢው አርሶ አደሮችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ባካሄዱት ሰፊ ተጋድሎ የዞብል ሰንሰለታማ ተራሮችን ሙሉ በሙሉ መቆጣተራቸውን አስቀድመው ያስታወቁት የአፋር ሚዲያዎች ” መንገዶች ሁሉ ወደ መቀለ ያመራሉ” እያሉ በሚገኙበት ወቅት፣ ዛሬ ማለዳ የቦረንና አርጆ ተራራም ስፍራዎች ተገን ያደረገው ሰራዊት ዋጃን በጁ ማስገባቱ ከአፋር ክልል ይፋ ሆኗል።

ከትናንት በስቲያ ለሊት ላይ የወልደያ መቀለ መንገድ መቆረጡን ተከትሎ በጋሸና ግንባር አማራጭ ፈልጎ ለመውጣት ሲል የትህነግ ሃይል ውጊያ ቢከፍትም ተመክቶ እንድተደመሰሰና እንደተበተነ ታውቋል። ይሁን እንጂ በዚያ መስመር የተሰማራው ሃይል ቁጥሩ ከፍተኛ በመሆኑ በተበተነበት እየገቡ ለማጽዳት ቀላል እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። በርካታ ሬሳውን እንዳከማቸ ጥሎ መፈርጠጡን መንግስት ሲያስታውቅ ሃይሉ ቁስለኛ፣ ሙትና ምርኮኛ እንደሆነ አመልክቷል። ትሀንግ ይህን ጦርነት ነው ከሰማኒያ ሺህ በላይ ተዋጊዎችን እንደገደለበት ያስታወቀው። በአስተያየት መስጫው እንደተባለው ሰማንያ ሺህ ከገደለ ለምን ጋሸናንና ላሊበላን መልሶ አልያዘም?

Image

ኦሮሚያ በዕምነቷ “ጀግና ልጃችን” ስትል፣ በኦሮሞ የጀግና ስያሜ ሞጋሳ መሰረት የኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “አብቹ አባ ቢያ” የሚል የገዳ ስያሜ መስጠቱን፣ በዚህ ስነ ስርዓት ላይ “… ከአሸባሪው ትህነግ ጋር ጥምረት የፈጠረ ማንኛውም አካል የኦሮሞ ጠላት ነው፤ የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት የሞተለትን ዓላማ በመዘንጋት ከጠላት ጋር ማበር ውርደት ነው” በሚል እርግማን ተካሂዷል። አቢቹ አባ ቢያ የኢትዮጵያ ሁሉ ጀግና መሆናቸው ሲወደስና ክብር ሲሰጥ፣ በዛው ሰዓት አቶ ጸጋዬ አራርሳ ቀደም ሲል ” የተረጋገጠ ሚሌ ተያዘች” እንዳሉት ” ጋሸና ትህነግ እጅ ወደቀች” በሚል መረጃ ያሰራጩ ነበር።

ወራሪው በፍጻሜ ዋዜማ ላይ መሆኑን የሚያሳዩትን የዞብል ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የአርጆ፣ ፎኪሳ እና ቦረን ከተሞችን መቆጣጠሩ ይፋ በሆነበት ለሊት ዋጃን እጁ ያስገባው ሰራዊት ከላይ በምስል እንደሚታየው ጉባል ላፍቶን ተንተርሶ ወደ ወልደያ፣ ሓራን ተቆጣጥሮ ወደ ወልደያ፣ መርሳን የተቆጣጠረው ሃይል ወደ ወልደያ፣ የሚያደርጉትን የከበባ ጉዞ ከላይ ሆኖ በቆቦ በኩል እንደሚያጠናክር ባለሙያዎች አመልክተዋል።

በውጫሌ ግንባር የአምባሰል ከፍተኛ ሠንሠለታማ ተራሮችን ጨምሮ የሮቢትና የጎልቦን፣ በወረባቦ ወረዳ የሚሌ ኮትቻን፣ በሐብሩ ወረዳ የኮልቦን፣ የመርካታና የፋጂን አካባቢዎችን በመቆጣጣር ወደ መርሳ ከተማ እየተጠጋ ያደረው ሃይል ዛሬ መርሳ እንደሚገባ የገለጹ እንዳሉት፣ መንግስትም ትናንት እንዳስታወቀው የትህነግ ሃይል የትጥቅ አቅርቦትና ወታደራዊ ድጋፍ በማያገኝበት ደረጃ ስለተቆረጠ ውጊያው የነብስ ውጪ፣ የነብስ ግቢ እንደሚሆን ባለሙያዎች አመልክተዋል።

ዋጃ ከአላማጣ አስራ አምስት ኪሎሜትር ርቃ የምትገኝ ከተማ ስትሆን አላማጣ ስር ካሉ ሁለት ወረዳዎች አንዷ ስትሆነ የምዕራብ ትግራይ አካል ናት። መንግስት የወልደያ መቀለን መንገድ መቁረጡን ይፋ ባደረገ ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ዋጃን መያዙ ምን አልባትም ወደ መቀለ ለመግባት ጥርጊያ መንገድ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። በአፋር በኩል “ኢጉታ” ተነስ፣ “አቱካ” አጥቃ የሚል ወታደራዊ መመሪያ የሚጠብቁ ሃይሎች በተጠንቀቅ መሆናቸውና ከአፋር ሃይሎች ውስጥ አብዛኞቹ ከመከላከያ ጋር የዞብል ሰንሰለታማ ተራሮች ላይ እንዲያርፉ መደረጉ ምን አልባትም ዘመቻ ቁጥር ሁለት በደጅ እንደሆነ አመልካች አድርገው የተመለከቱም አሉ።

የትህነግ ሃይል በዚህ ሁሉ ጫና ውስጥ ቢሆንም በጋሸና በኩል መውጫ ለማግኘት እያደረገ ያለውን ትንቅንቅ በድል ዜና እንደሚያጅቡ የትህነግ መሪዎች እያስታወቁ ነው። ትህነግ ለምን ከክልሉ ወጥቶ በመዋጋት የትግራይ ልጆችን እንደሚያስጨርስ ግልጽ ያልሆነላቸው ወገኖች ዛሬም ሰላም እንደሚሻል እየመከሩ ነው። በሁሉም ወገን ሰላም አውርዶ ጥፋተኞችን ወደ ፍርድ ከማቀረብ የተሻለ ምንም አማራጭ እንደማይኖር የሚመክሩ ወገኖች “ቢበቃስ” እያሉ ነው። የትግራይ ሕዝብ ከኤርትራ፣ ከአፋር፣ ከአማራ ዙሪያውን እሳትና ጭድ ሆኖ ለምን ይኖራል በሚል የሚቆጩ ” ለምን ይህንን ጉዳይ የሚያመኩ የትግራይ ልጆች አይነሱም? ምን እስኪሆን ነው የሚጠበቀው?” ሲሉም ይጠይቃሉ።

ይህ በንዲህ እንዳለ ሮይተርስ ከምስክር ሰማሁ ሲል ላይሊበላ በድጋሚ በትህነግ እጅ ገብታለች ብሏል። የኢትዮያ ጦር ዋጃን እንደያዘ ያልተናገረው ሮይተርስ ዜናውን ማንም አላረጋገጠልኝም ብሏል።

ከስፍራው ፈታ ቲዩብ ከሰዓታት በፊት ያናገራቸው እሸቴ የሚባሉ ፋኖ እንዳሉት ከየግንባሩ እየሸሸ የመጣው ሃይል ወልደያ ሲዘጋበት በጋሸና መስመር ቀበሮ ሜዳና ዳቦ ከተማ ጥሶ ለመውጣት ውጊያ ከፍቶ በአየር መመታቱን ሲናገሩ ለመስማት ተችሏል።

ሮይተርስ እንዳለው የትህነግ ሃይል ወደ ላይሊበላ የተመስለሰው ያለ ጦርነት ነው። ፋኖው ሲናገሩ ግን በሰቆጣ አበርገሌ ብቻ የመሹለኪያ አማራጭ ስላለው መሞከሩን አመልክተው እኛ ላሊበላን አልፈን ገነት ብማሪያም ነን በት በኩል ላይሊበላን ይይዛል ብለዋል።

ፋኖው እንዳሉት ከደሴና ቆቦ ጨምሮ በህይወት የተረፈው ሃይል ቁጥሩ ቀላል ስላልሆነ ዋጋ ሊያስከፍል ይችል እንደሆነ እንጂ ምንም የመፍተር አቅም እንደሌለው ነው ያመለከቱት።

ኮማንዶ፣የሁለት ብርጌዶችን ስም ጠርተው እየደመሰሷቸው መሆኑንን ሳይሸሽጉ ተናግረዋል። ጠያቂው እንደጓደኛ እያዋዛ፣ እሳቸው ቃለ ምልልስ መሆኑን ሳያውቁ እንደተናገሩት መረዳት የተቻለው የወልደያ መንገድ መዘጋት የተቆረጠው ሃይል ወደ ውስጥ እንዲመለስ እንዳስገደደው ነው።


ተጨማሪ ያንብቡ


Leave a Reply