Site icon ETHIO12.COM

«ህጻናት ልጆቹን ለጦርነት ያልላከ ቤተሰብ የእርዳታ እህል እንዳያገኝ ተደርጓል»

በትግራይ አሁን
👉 ህጻናት ልጆቹን ለጦርነት ያልላከ ቤተሰብ የእርዳታ እህል እንዳያገኝ ተደርጓል።
👉 በህዝቡና በጁንታው አመራሮች መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።
👉 በጁንታው በሚደርስባቸው ጫና ከርሃብ ጦርነት ይሻላል ያሉ ወላጆች ህጻናት ልጆቻቸውን ለጦርነት ለመላክ ተገደዋል።



መንግሥት የተናጠል ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ በማድረግ፡ አርሶአደሩ የእርሻ ጊዜው የጥሞና ጊዜ እንዲያገኘ ሠራዊቱን ከትግራይ ክልል ካስወጣ በኋላ በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ትንኮሳ የትግራይ ህዝብ ስቃይ ውስጥ መግባቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል።

ጁንታው ከተደበቀበት ዋሻ ከወጣ በኋላ ህዝቡን ደጋፊና ጠላት በሚል ፍረጃ ማሰቃየት፣ መግደል እና ማሳደድ ከመጀመሩም ባሻገር፤ ማንኛውም የትግራይ ቤተሰብ የእርዳታ እህል የሚሰፈርለት ከቤተሰቡ ውስጥ ለትግል ልጁን ያዋጣ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ነው። ልጆቻቸውን ለውጊያ ያልላኩ ቤተሰቦች ምንም አይነት የእርዳታ እህል እንዳያገኙ ይደረጋል፤ በዚህም በፍርሃት፡ ከርሃብ ጦርነት የመረጡ ወላጆች ሕጻናት ልጆቻቸውን ሳይቀር ወደ ጦርነት ለመላክ ተገደዋል ብለዋል።

ህዝቡ በጁንታው አመራሮች ችሮታ ብቻ እንዲኖር ተገዷል ያሉት ምንጫችን መንግሥት ላለፉት ስምንት ወራት ሲያደርግ የነበረውን ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያመሰግኑ፣ መከላከያ ተመልሶ እንዲመጣ የሚጠበቁና ልጆቻችን የት ገቡ? ብለው መጠየቅ የጀመሩ ወላጆች ተበራክተዋል ብለዋል።

ከርሃብ ጦርነት የመረጡ የትግራይ እናቶች ወደጦርነት የላኩዋቸውን ህጻናት ልጆችቻቸውን መጠየቅ መጀመራቸው በአሸባሪው ህወሃት አመራሮች ዘንድ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን ይህንን ለማረጋጋትም ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ፈትለወርቅ ገ/እግዜብሄር (ሞንጆሪኖ) ከሰሞኑ መቐለ ላይ ለማረጋጋት ሞክረዋል። በዚህም በጦርነቱ የደረሰባቸውን ኪሳራ ዘርዝረው አሁንም ትግሉን ለማስቀጠል የሚቻለንን እናድርግ ሲሉ ተማጽነዋል ሲሉ ምንጫችን ነግረውናል።

የሞንጆሪኖ ማሰትባበያ በኑሮ ውድነት እና ህጻናት ልጆቹን ወደጦርነት እንዲያስገባ የተገደደውን ህዝብ የሚያረጋጋ አልሆነም ያሉት ምንጫችን ቀደም ሲል የነበረው የመከላከያ እና የመንግስት ድጋፍ ይሻለን ነበር በሚል ምሬት ውስጥ ህዝቡ መግባቱን ጠቁመዋል።

በትግራይ ያለው የነዳጅ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ጁንታው ከዋሻ ከተመለሰ በኋላ ያገኛቸውን ተሽካርካሪዎች ለማንቀሳቀስ እንቅፋት ሆኖበታል። በዚህም ያለውን አቅም ሁሉ አስተባበሮ በአፋርና በአማራ በኩል ነዳጅና መሳሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ያሰማራው ሃይል ሙሉ በሙሉ በመድመስሱ ሊሳካለት እንዳለቻለ ምንጫችን አረጋገጠዋል።

ህዝቡ ውስጥ ያለው የምግብ፡ የነዳጅና ሌሎች መሰረታዊ ጥያቄዎች ጭንቀት የፈጠረበት የህወሓት አሸባሪ ቡድን በሁሉም አቅጣጫ የሞት ሽረት ትንኮሳ እያደረገ እና ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት ይገኛል።

የህወሓት አሸባሪ ቡድን መሪ ዶክተር ደብረጺዮን የትግራይ ህዝብ በሙሉ፣ ህጻናትና አዛውንቶች ሳይቀሩ ለውጊያ እንዲሰለፉ ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። በሌላ በኩል ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ በቅርቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የህወሓት አመራር ተረጋግቶ መቀሌ ሊቀመጥ አይችልም። ይህንን ካደረገ ህዝቡ ልጆቹን መጠየቅ ይጀምራል፡ ለኑሮው የሚያስፈልገውን ሁሉ መጠየቅ ይጀምራል። ለዚህ መልስ ስለሌለው ትንኮሳውን መቀጠል አማራጭ የለውም” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

አሸባሪው ቡድን በአፋርና አማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ከሰሞኑ ነዳጅና መሳሪያ ለማግኘት እንዲሁም ክህዝብ የሚነሳውን ጥያቄ በግጭት ውስጥ ለማድበስበስ ያደረገው ትንኮሳ አልተሳካለትም። ለትንኮሳ ባደረገው ጥረት ያሰማራው ኃይል ከፍተና ሰብአዊ ኪሳራ ደርሶበታል። የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ የተባለው ኃይል ዛሬ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ምንጮች ዛሬ ለኢፕድ ገልጸዋል። via ENA

Exit mobile version