ደብረጽዮን አመኑ!!

«አዎ ! የእርዳታእህልለታጣቂዎችእናከፋፍላለን፤ሰውሳይበላአይዋጋም»

“ጦርነት አይቀሬ ነው”

የትግራይ ህዝብ መከራ ዛሬም መቋጫ አላገኘም፡፡ ወቅቱ ግድ ከሚለው የሃሳብ የበላይነት ከሚዘውረው ፖለቲካ ይልቅ በጉልበት ሁሉንም ፍላጎት እንሟላለን ብለው በድርቅና አንድ ቦታ ላይ ተቸንክረው በቀሩና በህዝብ ስም የራሳቸውን ቁሳዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚውተረተሩ ጥቂት በእብሪት የተሞሉ ግለሰቦች የተነሳ ትግራዋይ ወገኖቻችን በመገለል ስሜት እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡ መለመንን እንኳን እንደ ነውር የሚቆጥረው ኩሩው ትግራዋይ የእርዳታ መኪና እየቆጠረ በተስፋ የሚኖር ህዝብ ሆኗል፡፡

የትግራይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ህዝቡ በሰቆቃ ኑሮውን እየገፋ፤ በእነርሱ መካከልም ያለው ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ለመጠፋፋት እየተፈላለጉም ጦር ሰብቆ ጥፋት ለመፈጸም አንድ የሚያደርጋቸው ሰይጣናዊ ሃይል ያለ ይመስላል፡፡ ሰሞኑንም ይህን እኩይ ድርጊታቸውን ለመቀጠል ላይ ታች እያሉ ይገኛሉ፡፡ በውጭ ከሚኖረው የዳያስፖራ አባላትም ጦርነትን እንደ ተከታታይ ድራማ ለመቀጠል እየተነሳሳ ያለውን ህወሓት ግፋ በለው የሚሉ አልጠፉም፡፡

ይሁንና ህወሓት ወደ ጦርነት ከመግባቴ በፊት ከትግራይ ዳያስፖራ ጋር ምክክር ላድርግ በሚል በደብረጽዮን መሪነት በዙም የኮምኒኬሽን ስርዓት ያካሄደችው ምስጢራዊ ውይይት በምስጢር አነፍናፊዎች እጅ ገብቶ ብዙ ያልተሰሙ ገመናዎቿን ይዞ ወጥቷል . . .

ደብረጽዮን ሰሞኑን በምስጢር በተደረገው ምክክር ለዳያስፖራ አባላት ስለ ትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ በሰጠው ማብራሪያ የፌዴራል መንግሥት ቃል በገባው መሠረት ሰብአዊ እርዳተ በበቂ ሁኔታ እየገባ ነው፡፡ አሁን የምግብና የመድሃኒት አቅርቦት ችግር የለም ብሏል፡፡

ይህ ማብራሪያ ከዳያስፖራ አባላቱ ጥያቄ አስነስቷል፡፡ ‹‹በቂ የሰብአዊ አቅርቦት ካለ የትግራይ ህዝብ አሁንም ለምን በችግር ይማቅቃል፤ የእርዳታ እህል ለታጣቂዎች ታከፋፍላላችሁ የሚባለው እውነት ነው?›› የሚል ጥያቄ የዳያስፖራ አባላቱ ሰንዝረዋል፡፡

ደብረጽዮን ለዳያስፖራ አባላቱ በሰጠው ምለሽ ‹‹አዎ የእርዳታ እህል ለታጣቂዎች እናከፋፍላለን፡፡ ታዲያ ምን እንቀልባቸው፡፡ ሰው ሳይበላ አይዋጋም›› በማለት ቆፍጠን ብሎ ተናግሯል፡፡

የዳያስፖራ አባላቱ ህጻናት ያለ አቅማቸው ነፍጥ ማንገባቸው፤ ወላጆችም ተገደው የአብራካቸውን ክፋይ መገበራቸው እንቢ ቢሉም እንደሚታሰሩ በተለያየ መንገድ ከቤተሰቦቻቸው መረጃ እንደሚደርሳቸው በምስጢራዊው የዙም ውይይት ላይ አንስተው ነበር፡፡

ደብረጽዮን በሰጠው ምላሽ ጦርነት አይቀሬ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ‹‹ጦርነት አይቀሬ ነው፡፡ ጦርነቱ ደግሞ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ከጦርነት ውጪ አማራጭ የለንም፡፡ ህጻናትም አዛውንትም በግንባር ይሰለፋሉ፡፡ ሁሉንም አማራጭ እንጠቀማለን፡፡ ›› በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ደብረጽዮን በዙም ውይይቱ ከዳያስፖራው ጋር ምክክር ያስፈለገው ዓለም ቀፍ ማህበረሰቡ በትግራይ ላይ ፊቱን እያዞረ ስለሆን እውነታውን ተነጋግረን ሁሉም ትግራዋይ በአንድነት ተሰልፎ ግዴታውን እንዲወጣ ነው ብሏለ፡፡ ‹‹ዓለም አቀፍ ተቋማት በሰብዓዊ መብት ጥሰት እየከሰሱን ነው፡፡ የእርዳታ እህል እንዳይገባ መንገድ የምትዘጉት እናንተ ናችሁ፡፡ እርዳታ ከገባ በኋላም ለታጣቂዎች ታከፋፍላላችሁ በማለት ማስረጃ በመቁጠር ጭምር እየከሰሱን ነው›› በማለት በምስጢራዊው ስብሰባው ያወራው ደብረጽዮን ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ከዚህ ቀደም የነበረውን አቋም በመከለስ የትግራይን ሃይል እንደ አነስተኛ የጎሬላ ተዋጊ ቡድንና እንደ ህዳጣንም እያዩን ስለሆነ አሁንም በድጋሚ አቅማችንን ለማሳየት የእናንተ ትብብር ያስፈልጋል ብሏል፡፡

ደብረጽዮን የትግራይን ዳያስፖራ ከጎኑ ለማሰለፍ የእውር ድንብር መድረክ ቢመራም ተቃራኒ ውጤት እንዳስከተለ በገሃድ እየታየ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም የትግራይ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች እንዲሁም ልሂቃን በተሳሳተ ስሌት የለኮሱት ጦርነት የትግራይን እናቶች ለማያባራ ሀዘን፤ እስከ 300 ሺ የሚደርሱ የክልሉን ወጣቶች ለከንቱ መስዋዕትነት ዳርጓል፤ ወዳጅና አጋር አሳጥቶናል የሚል እምነት አለን የሚሉ በርካታ ዳያስፖራዎች ከፌዴራል መንግሥት ጋር ስምምነትና እርቅ እንዲፈጸም ፍላጎታቸው መሆኑን እየገለጹ ነው፡፡

Via – https://t.me/NatnaelMekonnen21/25437

Leave a Reply