የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ አደረገ። ሁለት ሰዎች ያልተፈቀደ የመድሃኒት ስንቅ ይዘዋል በሚል በፍተሻ ተረጋግጦ ከጉዞ መቀነሳቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ፋና ዘግቦ ነበር።
በዚህ በ2ኛው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።
ይህ ዜና ከተላለፈ በሁዋላ በረራው ከመካሄዱ በፊት በተደረገ ፍተሻ ሁለት የእርዳታ ድጋፍ ሰጪ ናቸው የተባሉ ሰዎች ያልተፈቀደ መድሃኒት ጭነው በመያዛቸው ከበረራ መታገዳቸው ታውቋል።
ግዕዝ ሚዲያ ታማኝ የሚላቸውን የመረጃ ሰዎች ተቅሶ እንዳለው የተገኘው መድሃኒት ቢሆንም ተጨማሪ የተከለክሉና ከዕርዳታ ተግባሩ ጋር የማይገናኝ ቁሳቁስ መያዙ ተሰምቷል። ይህን አስመልክቶ መንግስት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በዕርዳታ ስም የማስታጠቅና የ1977ቱን ድርጊት የመድገም ሙከራዎች መያዙን ማስታወቁ አይዘነጋም።
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች ዜና የሚያቀብሉና እነሱኑ የሚከተሉ ስምምነቱ መክሸፉንና መንግስት ውሉን… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል ትዕዛዝ… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን በሃፍረት ስሜት ነው። ያፈርኩት ደግሞ በደርስንበት የሞራል… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ሲኖር መሳሪያ ሸጦ ትርፍ ማጋበስ… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!