Site icon ETHIO12.COM

ሁለተኛው የዕርዳታ በረራ ከመደረጉ በፊት በፍተሻ ያልተፈቀደ ጭነት ተያዘ፣ ሁለት ታገዱ

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ  ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ አደረገ። ሁለት ሰዎች ያልተፈቀደ የመድሃኒት ስንቅ ይዘዋል በሚል በፍተሻ ተረጋግጦ ከጉዞ መቀነሳቸው ተሰማ።

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ፋና ዘግቦ ነበር።

በዚህ በ2ኛው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

ይህ ዜና ከተላለፈ በሁዋላ በረራው ከመካሄዱ በፊት በተደረገ ፍተሻ ሁለት የእርዳታ ድጋፍ ሰጪ ናቸው የተባሉ ሰዎች ያልተፈቀደ መድሃኒት ጭነው በመያዛቸው ከበረራ መታገዳቸው ታውቋል።

ግዕዝ ሚዲያ ታማኝ የሚላቸውን የመረጃ ሰዎች ተቅሶ እንዳለው የተገኘው መድሃኒት ቢሆንም ተጨማሪ የተከለክሉና ከዕርዳታ ተግባሩ ጋር የማይገናኝ ቁሳቁስ መያዙ ተሰምቷል። ይህን አስመልክቶ መንግስት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ በዕርዳታ ስም የማስታጠቅና የ1977ቱን ድርጊት የመድገም ሙከራዎች መያዙን ማስታወቁ አይዘነጋም።


Exit mobile version