Site icon ETHIO12.COM

ልጆቻቸው መቀለ ዩኒቨርስቲ የቀሩባቸው ወላጆች የተመድ ፊት እያነቡ ነው “ልጆቻችንን አስለቅቁልን”

ልጆቻቸው በመቀሌ ዩኒዘርስቲ የሚገኙ ወላጆች እያነቡ ነው። ባለፈው ሳምንት ወደ ቤተሰቦቻቸው ለማቅናት አፋር ድንበር ከደረሱ በሁዋላ የአሸባሪው ቡድን ቃለ አቀባይ ለሮይተርስ እንዳረጋገጡት፣ ቡድናቸው በከፈተው ጥቃት ተማሪዎቹ ወደ መቀለ ተመልሰዋል።

ይህንኑ ተከትሎ ቤተሰቦች ተሸብረዋል። እንቅልፍ የለም። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል። የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርም በጉዳዩ ዙሪያ አቋሙን ቁርጥ አድርጎ አላሳወቀም። አጥብቆ የጠየቀውም ዓለም ዓቀፍ አካል የለም።

ልጆቻቸውን ትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች እንዲሁም ቤተሰቦች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ አበባ ቢሮ ፊት ለፊት ቆመው እሪታቸውን እያሰሙ ነው።

ወላጅና ቤሰቦች ለትምህርት የላኳቸው ልጆቻቸው እንዲመለሱ እየጠየቁ ነው። በትንሹም በትልቁም የኢትዮጵያን መንግስት የሚወተውተው የተባበሩት መንግስታት ምን ምላሽ እንደሰጠ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ከዚህ ቀደም አንዳንድ ተማሪዎች ምንም እንዳልገጠማቸው መናገራቸው ይታወሳል። ሆኖም ግን ፈተና ከጨረሱ በሁዋላ ትግራይ እንዲቆዮ የተደረገበት ምክንያት ግልጽ አልሆነም።

Exit mobile version