Site icon ETHIO12.COM

“አሜሪካ ትህነግ የሚባል አሻንጉሊትዋን ከስራለች”

“አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ይህንን አይነት አካሄድ የተከተለችበት ዋና ምክንያት አሻንጉሊቷ የነበረውን ትህነግን ስለከሰረች ነው” ሲሉ አን ጋሪሰን አስታወቁ። የብላክ አጀንዳ ሪፖርት ኤዲቶር፣ ተመራማሪ፣ በምርመራ ጋዜተኝነት ታዋቂ እነደ ሆኑ የሚነገርላቸው አን ይህን ያሉት ከአር ቲ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።

በፍጹም መገረም ጥያቄዎቹን ሲመልሱ የነበሩት አን ትህነግ አሁን ለተፈጠረው ችግርና ጦርነት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ እንደሆነ ያስረዱት በምክንያት ነው። እነ ሴኮና ጻድቃን እንዳሉት እሳቸውም ጦርነቱን ትህነግ እንደጀመረው አስመረው ተናግረዋል። “የትኛውም አገር የመከላከያ ሃይሉ ቢነካ ዝም ይላል?” ሲል የአሜሪካንን አካሄድ በምጸት የተችሁት አን ከራሺያው RT ቴሌቪዥን ጋር በነበራት ቆይታ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ምን ፈልጋ? ምንስ አስባ ነው? በሚለው ነጥብ ዙሪያ ሰፊ ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያን ጉዳይ ” መስሚያ የለኝም” ብላ እየሰራች ያለችው አሜሪካ አሁን አሁን ትችቶች ቀስ እያሉ እየተነሱባት ነው። አን ከተናገሩት ውስጥ አዲስ ዘመን ይህንን ቀንጭቦ አውጥቷል።

በውይይቱ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች.

. በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ግጭት መንስኤው ሀገሪቷን ለ27 ዓመታት የመራት ህወሓት በሰሜ ን ዕዝ ላይ የፈፀመው ጥቃት ነው፤

. ከዚህ ጥቃት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዚህ መልስ ሰጥተዋል፤ ነገር ግን ምዕራባዊያን እና ሚዲያዎቻቸው ጦርነቱን የጀመረው አብይ ነው ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው፤

. የትኛው ሀገር የትኛው መንግስት ነው የመከላከያ ሰራዊቱ በክልል ሀይል ጥቃት ተፈፅሞበት ዝም የሚለው?

. እውታው ይህ ቢሆንም ምዕራባውያን እና ሚዲያዎች ዛሬም ድረስ አብይና መንግስቱን ይወቅሳሉ ይህ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ክሥ ነው፤

. አሜሪካ አንድ ሀገር ማጥቃት ስትፈልግ ሁልጊዜም ዘር ማጥፋት ፣ የጦር ወንጀል የሰብዓዊ ቀውስና መሰል ክሶችን ታስቀድማለች፤

. በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት የተባለው ወንጀለል ስለመፈጸሙ በፀጥታው ም/ቤት መረጋገጥ አለበት፤

. ም/ቤቱ ችግሩን የሚፈታበት ሁሉን አቀፍ መፍትሄ አለው፤ አሜሪካ ግን አሁን እያረገች ያለችው ከዚህ ውጪ ነው

. አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ይህንን አይነት አካሄድ እየተከተለች ያለችው አሻንጉሊቷ የነበረችው ህውሓት ስለተወገደችባት ነው

. ህወሓት ወደ አስመራ ሮኬት ተኩሳለች ፤ የምትወቀሰው ግን ኤርትራ ናት

. አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ ጥላለች፤ በሌሎች ሀገራት ላይ እንዳደረገችው ሁሉ ሌሎች ማዕቀቦችንም ሆነ እርምጃዎችን መውሰዷ አይቀርም፤ በኢራቅ በሊቢያ የሆነውም ይሄው ነው፤

. አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ይህንን አይነት አካሄድ የተከተለችበት ዋና ምክንያት አሻንጉሊቷ የነበረችው ህወሓት ስለተወገደችባት ነው፤


Exit mobile version