Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ” ፈሪና ጀግና” በሚል እየፈረጀ ነው፤ እነ ዳኔል ብርሃኔ መተንፈሻ አላገኙም

“አሸባሪ” የሚል መዕረግ ተሸልሞ ወደ መቀለ የተመለሰው የትህነግ ቡድን ” ፈሪና ጀግና” በሚል እተፈራረጁ መሆኑንን በአሜሪካ የድርጅቱ ዋና ደጋፊ መናገራቸው ተሰማ። በረሃ የወረዱት ” ጅግና” ሲባሉ፤ ከተማ ተደብቀው የነበሩ ” ፈሪ” እየተባሉ ነው።

ትህነግ ከበረሃ ወጥቶ ወደ መቀለ ሲገባ ከተደበቁበት ከወጡት መካከል ዳንዔል ብርሃኔ ይገኝበታል። የድርጅቱ ዋና ደጋፊ እንዳሉት እነ ዳንኤል የሳተላይት ስልክ እንዳይጠቀሙ ተከልክለዋል። ለዚህም ምክንያቱ ” ፈሪ” በመሆናቸው ነው።

ለወትሮው ከማህበራዊ ገጽ የማይጠፋውና ወደ መቀለ ከሄደ በሁዋላ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በመስደብ፣ በማሽሟጠጥና በማውገዝ ስራ ተሰማርቶ የነበረው ዳንዔል፣ መንግስት እንዴት እንደሚቀየር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዴት የዓለሙ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት እንዴት እንደሚቀርቡ፣ ጦርነቱ ከሁለት ሳምንት በላይ እንደማይፈጅ በተደጋጋሚ በማስረዳት ቀዳሚ ነበር።

ተደብቆ ሕይወቱን ያተረፈው ዳንዔል ስልክ ፈልጎ ማጣቱን ከላይ የተገለጹት የትህነግ ዋና አባል በስሞታ ደረጃ ከሌሎች መስማታቸውን አስታውቀዋል። ቀደ ባለው ጊዜ ዳኒ የጌታቸው አሰፋ ወገን እንደነበር በተደጋጋሚ ሲነገር ነበር። “የደህንነቱ ሹም አለመኖራቸው ዳኒ ስልክና ኢንተርኔት ብርቁ ሆነ” ሲል የሰማውን ወሬ ያጋራን የአሜሪካ ተባባሪያችን ነው።

እንደ ዳኒ ሁሉ በርካታ የተደበቁ የነበሩ ” ፈሪ” ተብለው ፊት እንደተነሱ ከመቀለ መረጃ ያላቸው አስታውቀዋል።


Exit mobile version