Site icon ETHIO12.COM

የተመድ የሚል ጽሁፍ ያለበት ኣወሮፕላነ ምስራቅ ሃረርጌ ወደቀ

ዛሬ አመሻሽ ላይ በምስራቅ ሀረርጌ ስለወደቀው አውሮፕላን የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ የሰጠው ምላሽ!

ዛሬ አመሻሽ 11 ሰዓት ተኩል አካባቢ አንድ አነስተኛ አዉሮፕላን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ መዉደቁን የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

የኮምቦልቻ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዲ ቡሽራ አራት ሰዎችን የጫነዉ አውሮፕላን ቄረንሳ ቀበሌ ተራራማ ቦታ ላይ መዉደቁን ተናግረዋል።

አውሮፕላኑ ከድሬደዋ ከተማ እንደተነሳና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ሰብአዊ አገልግሎት የሚል ጽሁፍ እንዳለበትም ተናግረዋል። “በአደጋዉ አንድ ሰዉ ብቻ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበታል” ብለዋል።

አውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ሶስቱ የኢትዮጵያ ዜጋ ሲሆኑ አንዱ የዉጭ ሀገር ዜጋ አንደሆነም አክለዋል። አደጋዉ የደረሰበት ቦታ አየር ሁኔታ በጣም ጭጋጋማ እንደነበር የተናገሩት አቶ አብዲ ቡሽራ የአደጋዉ መንስኤም ይኸዉ የአየር ሁኔታ ሊሆን እንደሚችል ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል።

በረራው ወዴት እንደነበር የተጠየቁት አቶ አብዲ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ለኢትዮጵያ ቼክ የተናገሩ ሲሆን ግለሰቦቹ ይዘዋቸው የነበሩ ሻንጣዎችም እንደተገኙ አስረድተዋል።

Exit mobile version