Site icon ETHIO12.COM

ከ100 በላይ የጥፋት ሃይሎች ተደመሰሱ

በክልሉ ከ100 በላይ የጥፋት ሃይሎች ተደመሰሱበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ርዝራዦችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሽምቅ ተዋጊዎች መደምሰሳቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሃመድ ማሻውን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ዛሬ የተደመሰሱት እነዚህ የጥፋት ሃይሎች በአሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ አወልቤጉ ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሽምቅ ተዋጊዎች ናቸው፡፡

ከተደመሰሱት አብዛኞቹ ክልሉን ሲያተራምሱ የነበሩ ራሱን የጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ብሎ የሚጠራው ቡድን አባላት እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ከመካከላቸው አምስቱ ደግሞ ከትግራይ ክልል የመጡ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ርዝራዦች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

የጥፋት ሃይሎቹ በሱዳን ጠረፍ መተከል ዞን አጎራባች በሆነው አሶሳ ዞን ሸርቆሌ ወረዳ በኩል ወደ ካማሽ ዞን ኦዳቡልድግሉ እና ሌሎችም ወረዳዎች ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

ታጥቀውት የነበሩ ክላሺንኮቭ ጠብመንጃዎች በጸጥታ ሃይሉ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል፡፡

የአገር መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ እና ሌሎችም የጸጥታ ሃይሎች በቅንጅት ባካሄዱት እንቅስቃሴ የጥፋት ቡድኑን መደምሰስ መቻሉን አስታውቀዋል።

ቡድኑ አሁንም ክልሉን ለማተራመስ እየጣረ መሆኑን ያመለከቱት ኮሚሽነር አብዱልአዚም፤የጥፋት ቡድኑን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ የሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Via ENA

Exit mobile version