Site icon ETHIO12.COM

እስራኤል በአፍሪካ ህብረት የታዛቢነት መሰጠቱ ደ.አፍሪካን አስቆጣ፤ ሙሳ ፋኪ በውሳኔያቸው ሳቢያ ስልጣን እንዲለቁ ትብሏል

የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጅብረት ሃምሳ አምስት አባል አገራት አባል ሳይመክሩበት ለእስራኤል በአፍሪካ ሕብረት የታዛቢ ወንበር መሰተቱን የአንድ ወገን ውሳኔ እንደሆነ አስታውቆ ነው ተቃውሞውን ያሰማው። ክስም ያቀረበው። (ኢ.ፌ.ኤፍ ) በበኩሉ የሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ መሃመት ውሳኔ አሳፋሪ እና “ በፍልስጥኤም ሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈጸመ ጥቃት” በማለት ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አስተላልፏል።

የአገሪቱ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር መምሪያ ውሳኔው በፍልስጥኤም ጭቁን ህዝቦች ላይ የቦምብ ናዳ በወረደባቸው ዓመት መሆኑና መሬታቸው በህገወጥ በተወረረበት ወቅት መሆኑ የበለጠ አስደንጋጭ እንደሚያደርገው ነው ደቡብ አፍርሪካ ያስታወቀችው።”እስራኤል የፈጸመቻቸው ኢፍትሃዊ እርምጃዎች የአፍሪካ ህብረት የተቋቋመበት አላማና መንፈስን የሚጻረር ነው” ስትልም አጥብቃ ተቃውማለች።

ደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመድ ለአባል አገራት ውሳኔውን አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ ፍላጎቷን ይፋ አድርጋለች። የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ ፓርቲ የኢኮኖሚ ነፃነት ታጋዮች (ኢ.ፌ.ኤፍ ) በበኩሉ የሊቀ መንበሩ ሙሳ ፋኪ መሃመት ውሳኔ አሳፋሪ እና “ በፍልስጥኤም ሰብአዊ መብቶች ላይ የተፈጸመ ጥቃት” በማለት ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጥሪ አስተላልፏል።

እስራኤል በአፍሪካ አንድነት ድርጅት የታዛቢነት ቦታ የነበራት ቢሆንም ድርጅቱ በ2003 በአፍሪካ ህብረት ሲተካ የታዛቢነት ስፍራዋ አብቅቶ ነበር እንደ ቢቢሲ አፍሪካ ዘገባ። ለአመታት ያህልም የታዛቢነት ስፍራ ለማግኘት የጣረችው እስራኤል በአንዳንድ የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ተቀባይነት በማጣቱ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ via ethioFM101


Exit mobile version