ETHIO12.COM

“የአብይ ሰላይ መቀለ በአንድ ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለ”

ይህ ዜና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ደጋፊዎች በስፋትና በከፍተኛ ደረጃ የተቀባበሉት የ”ድል” ዜና ነው። TINSA ብለው የሰየሙት የትግራይ የስለላ መረብ ኤጀንሲ አነፍንፎና ልዩ ክትትል አድርጎ የኢትዮጵያ የስለላ መስሪያ ቤት ሃላፊ አቶ ተመስገን ወደ መቀለ የላኩት ሰላይ መያዙን “ሰበር ዜና” ሆኖ የቀረበበት ነው።

ኤርሚያስ ቶኩማ “የጁንታው አስቂኝ ውሸቶች ” ሲል “ሰበር ዜና” ተብሎና የትግራይ የስለላ ድርጅት ምጡቅ ተደርጎ የተሳለበትን ዜና በፊስ ቡክ ገጹ በማስረጃ አቅርቧል። ማብራሪያ ከምስል ጋር አካቷል። በሺ የሚቆተሩትን ተከታዮቹን አዝናንቶበታል። ነገሩ እንዲህ ነው።

ቅድሚያ ሜላት ተስፋዬ ካሰራጨችው አሉላ በላይ ለጌታቸው ረዳ ከላከው ከባድ ማስጠንቀቂያ ቅጂ እንጀምር። ” ይህ ሰው ለዩኤን ነው የሚሰራው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ ስትሆን ከማንናውም የፖለቲካ አስተሳሰብ ነጻ መሆን ወይም ገለልተኛ መሆን አለብህ። ስለዚህ ይህ ሰው በአሁኑ ሰዓት መቀለ ነው ያለው። ለምን ጉዳይ መቀለ እንደገባ የሚመለከተው አካል ማጣሪያ ቢያደርግ ጥሩ ነው” ይልና በነጮቹ ቋንቋ ጌታቸው ረዳ ብሎ ይዘጋዋል። ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያው ” ይድረስ የዝመኑ የትግራይ ኮከብ ተጨዋች ለሆንከው ጌታቸው ረዳ” እንደማለት ነው። በምኖች አገር አንድ እንትን ብርቁ እንደሚባለው!!

ከዛም አፍታ ቆይቶ ከላይ በምህጻረ ቃል የተገለጸው በሁለት አገር ህዝብ አጥንትና ፍርስራሽ ላይ ትገነባለች የተባለችው “የታላቋ ትግራይ” የስለላ ድርጅት ” የኢንሳው ተመስገን ወደ መቀለ የላከው የአብይ ሰላይ በአንድ ሆቴል ውስጥ ተገኘ” የሚል ዜና በ”ሰበር” ከትግራይ የመከላከያ ሃይል በሚል ማህበራዊ ገጽ ፎቶ ተደግፎ ተሰራጨ። ይህንኑ ዜናና ምስል በመቀባበልና ከስሩ አበባ በመበተን ለስለላ ድርጅታቸው ትጋትና አነፍናፊነት የላቀ መሆን ውዳሴ ዘነበ። ኤርሚያስ ቶኩማ ትዕይንቱን በእርጋታ ሰብስቦ ” ሰበሩን” ጉዳይ ” የጁንታው አስቂኝ ቀልዶች” ብሎ ተረከው።

እውነቱ እንዲህ ነው። ጓደኛው ነው “… ምኒሊክ ከጎኔ ቁጭ ብሎ በማግስቱ ሰኞ ለገብርኤል በዓል ወደ ድሬዳዋና ሐረር እንደሚሄድ ነገረኝና ተሰነባበትን። በማግስቱ ሰኞ ሐምሌ 19 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የድሬዳዋ ተጓዦችን በተከራየው የ UN አውሮፕላን ጭኖ እጅግ ዘግይቶ ወደ ድሬዳዋ ጉዞ ሊጀምር ሲል ጓደኛችን ምኒሊክ እኛን ለማሳቅ ብሎ ከአውሮፕላኑ ጋር ሰልፊ ፎቶ ተነስቶ ‘U N ለእርዳታ ሥራ ጠርቶኝ ወደ መቀሌ ልሄድ ነው’ ብሎ ፌስቡክ ገፁ ላይ እንደዋዛ ለጠፈው” ምን ለፋችሁ ጉዳዩ ከዛ በሁዋላ ምድር ቁና ሆነች … ሙሉውን ከኤርሚያ ፍተላ ተረዱት።

ዛሬ በሣቅ ስሞት ነው የዋልኩት። ዲጂታል ወያኔዎች ያን ያህል desperate ይሆናሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ባለፈው እሁድ ጓደኛዬ ምኒልክ ቤት ተጋብዤ ሄድኩኝ። ምኒሊክ ከጎኔ ቁጭ ብሎ በማግስቱ ሰኞ ለገብርኤል በዓል ወደ ድሬዳዋና ሐረር እንደሚሄድ ነገረኝና ተሰነባበትን።

በማግስቱ ሰኞ ሐምሌ 19 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የድሬዳዋ ተጓዦችን በተከራየው የ UN አውሮፕላን ጭኖ እጅግ ዘግይቶ ወደ ድሬዳዋ ጉዞ ሊጀምር ሲል ጓደኛችን ምኒሊክ እኛን ለማሳቅ ብሎ ከአውሮፕላኑ ጋር ሰልፊ ፎቶ ተነስቶ “U N ለእርዳታ ሥራ ጠርቶኝ ወደ መቀሌ ልሄድ ነው” ብሎ ፌስቡክ ገፁ ላይ እንደዋዛ ለጠፈው።

ባሻዬ! ከዚያ በኋላ በዲጂታል ወያኔዎች ምድር ቁና ሆነቻ!መጀመሪያ ላይ አሉላ በላይ የተባለ ሰው ጌታቸው ረዳን ጠቅሶ “ይህ የ UN ሠራተኛ መቀሌ ስለገባ ለምን መቀሌ እንደገባ ይጣራ” ሲል ጻፈ፣ቀጥሎ ደግሞ TDF የተባለው ዲጂታል ወያኔ “ሰበር” በሚል ርዕስ “የኢንሳው ተመስገን ጥሩነህ የላከው ሰላይ መቀሌ መግባቱን የትግራይ የደህንነት መረጃ መረብ ደርሶበታል” ብሎ ጻፈ፣በመጨረሻም የጌታቸው ረዳ ምንጮች “ይህንን የአብይ አህመድ ሰላይ መቀሌ ባለ አንድ ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ሥር አውለነዋል” ብሎ በመጻፉ ከቁጥጥር በላይ የሆነ ሣቅ አመለጠኝ።

ይህንን ፖስት ከመለጠፌ ከ5 ደቂቃ በፊት ምኒልክ ጋር ደውዬለት ዜናውን ስነግረው ነገ ሁሌ ምሣ የምንበላበት ቤት ለመገናኘትና በደንብ ለመሣቅ ቀጠሮ ያዝን።ባሻዬ! ምኒልክ ለቀልድ ብሎ የተናገረው ነገር እንዲህ ይጦዛል ብሎ አላሰበም። ወያኔ ይህንን ያህል desperate ሆናለች የምልህ ለዚህ ነው። ወያኔ ከማረከቻቸው 30 ሺህ ወታደሮች መካከል ቀልደኛው ጓደኛችን ምኒልክ አለበት ማለት ነው።

በተመሳሳይ ብዙ መረጃዎች ለፕሮፓጋንዳ እየዋሉ ስለሆነ ለማሳያነት የኮተቤውን ንጉስ ኤርሚያስ ቶኩማን መረጃ አትመነዋል። ተመሳሳይ ካለ ካልኩልን ። ኤርሚያስን በዚህ አድራሻ ታገኙታላችሁ። Ermias Tokuma


Exit mobile version