ETHIO12.COM

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ደካማ መንግስት እንዲኖር አልያም የመንግስት ለውጥ ለማድረግ ስውር አጀንዳ መያዛቸው ተጋለጠ

ምዕራባውያን በትግራይ ክልል የተካሄደውን የሕግ የማስከበር እርምጃ ተከትሎ በኢትዮጵያ ደካማ መንግስት እንዲኖር አልያም የመንግስት ለውጥ ለማድረግ የያዙት ስውር አጀንዳ መኖሩን ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን የሚተነትነው ጂኦ ፖለቲክስ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው ትንታኔ ላይ አጋልጧል።

የህወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ የአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት እ.ኤ.አ ህዳር 10/2020 የኢትዮጵያ መንግስት ሊዳከም በሚችልበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውንና ባለ 7 ገጽ ሰነድ ማዘጋጀታቸውን ጂኦ ፖለቲክስ በጽሑፉ አብራርቷል።

ሰነዱ ከህብረቱ አባላት መካከል በጥንቃቄ ለተመረጡ የተወሰኑ ቡድኖች ስለመሰጠቱም ገልጿል።

ቡድኑ በሰነዱ ወደፊት ሊከሰቱ ይችላሉ የተባሉ ሁኔታዎችን መዳሰሱንና በተከሰተው ግጭት ሳቢያ ከአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ አውሮፓ ሀገራት ሊሰደዱ እንደሚችሉም አመላክቷል።

በምዕራባውያን ዘንድ የወደፊቱን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አስመልክቶ በተደረጉ ውይይቶች የኢትዮጵያ መንግስት ለድርድር ዝግጁ ከሆነ ክልሎች መገንጠል እንዲችሉ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርጉ ሊፈቀድ ስለሚቻልበት ሁኔታ መነሳቱም ጠቅሷል።

ይህ የምዕራባውያኑ የተሳሳተ አካሄድ ለአሜሪካና ለአውሮፓ ህብረት በአንድ በኩል ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ የተበታተነች ሀገር እንድትሆን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው፤ በሌላ በኩል የመጨረሻው የዩጎዝላቪያ ፕሬዝዳንት ስሎቦዳን ሚሎሶቪች ላይ እንዳደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን በሰብአዊ መብት ጥሰት ስም በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ለማቅረብ ያለመ መሆኑንም ጽሑፉ ያብራራል።

ምእራባውያን በትግራይ ክልል የተካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ የያዙት ስውር አጀንዳ በኢትዮጵያ ደካማ መንግስት እንዲኖር ማድረግ አሊያም የመንግስት ለውጥ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑንም አጋልጧል። via Ena

Exit mobile version