ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ ደብዳቤ በማስመሰልና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ በማዘጋጀት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። ባሕር ዳር:ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በተጠርጣሪዎቹ ለማስለቀቅ የተሞከረው በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በአንድ መጋዝን ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለና በምርመራ ሂደት ላይ ያለ የፌሮ ብረት ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ በማስመሰል “ሕጋዊነቱ ስለተረጋገጠ በቦታው የሚገኘው የፖሊስ ጥበቃ ተነስቶላቸው ወደ ፈለጉበት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅደናል” የሚል ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅተው በመያዝና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ አዘጋጅተው ብረቱን በአምስት ተሽከርካሪ ጭነው ሊወጡ ሲሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፋይናንስ ኢንተለጀንስ ጠንካራ ክትትል ሊያዙ ችለዋል።
ባለፈው ሳምንት የተያዘው ብረት ባለቤት ነኝ ከሚል ተክላይ ከሚባልና አሜሪካን ሀገር ነዋሪ ነው ተብሎ ከሚነገረው ግለሰብ ጋር ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኤግዚቢትነት ተይዞ በምርመራ ሂደት ላይ ያለውን የፌሮ ብረት በጥበቃ ላይ ላሉት የፖሊስ አባላትና አመራሮች 500 ሺህ ብር ጉቦ ለመስጠት በአቢሲኒያ ባንክ አዲስ አካውንት ከፈተው ያስገቡ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በተመሳሳይ ለሌሎች የጸጥታ አካላት 400 ሺህ ብር በባንክ እና የ25 ሚሊዮን ብር ቼክ አዘጋጅተው ብረቱ እንደሚለቀቅ ከተስማሙ በኋላ የፖሊስና የጸጥታ አካላቱ ጉዳዩን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ለበላይ ኀላፊ በማሳወቅ ሂደቱ እንዲቀጥል በመደረጉ፤ ብረቱን በአራት ሲኖትራክ እና በአንድ ክሬን ለመጫን ተስማምተው በሁለት ሲኖትራክ እንደተጫነ ባንክ የገባው ብር እና ቼኩ፣ እንዲሁም የተፃፈው ሐሰተኛ ደብዳቤ እና ሦስቱ ተጣርጣሪዎች ከተዘጋጁት ተሽከርካሪዎች ጋር ከነአሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተጠርጣሪዎቹ ለጸጥታ አካላት በርካታ ገንዘብ ሰጥተው በማማለል ለሕገ-ወጥ ድርጊት ፖሊስ ተባባሪ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት በማክሸፍና ለሕግና ለመንግሥት ፍፁም ታማኝ በመሆን ወንጀሉ ለሕግ እንዲቀርብ በማድረግ የአሸባሪው ጁንታን እኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻላቸውን ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ኅብረተሰቡ አሁንም በዚህ አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ለመሳተፍ የሚጥሩ የአሸባሪው ጁንታና ከጁንታው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሀገሪቱ ላይ የሚያሴሩ ባንዳ ግለሰቦችን እየጠቆመ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
ምንጭ አዲስ አበባ ዜና አገልግሎት
- “ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችው የባህር በር ስምምነት በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል”ዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተሰማ። ሶማሌላንድ ለኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባሕር ኃይል የጦር ሠፈር በኪራይ የሚሰጠው ሥምምነት በሁለት ወራት ገደማ ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያስታወቁት… Read more: “ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የጀመረችው የባህር በር ስምምነት በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል”
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና። ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥቷል። ተጠርጣሪዎቹ የቀድሞ የህዝብ ትራንስፖርት የተሽከርካሪ ዘርፍ ኃላፊና… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎቹን መልሶ ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ መሆኑን ካውንስሉ ባደረገው ግምገማ ስለተገነዘበ” ነው። “የኢትዮጵያ ባለሥልጣኖች ዜጎችን መልሶ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው ግን በሃፍረት ስሜት ነው። ያፈርኩት ደግሞ በደርስንበት የሞራል ውድቀት ነው። እንደ ማህበረሰብ ይሁን እንደ ቡድን በውል… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ሲኖር መሳሪያ ሸጦ ትርፍ ማጋበስ የሚፈልግ ይፈጠራል፡፡ የጦር መሳሪያ ፈላጊና አቅራቢ ሲገናኙ የጦር… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!