Site icon ETHIO12.COM

የሁመራ ኮሪደር ድብቅ አጀንዳ ለምን? “አሸባሪና የሽብር ትጥቅ ይግባና ፈራርሱ እያሉን ነው”

ፎቶ አፕሪል 2016

አንዳንድ የምእራባዊያን ሀገራት በሰብዓዊ ዕርዳታ ሰበብ በሱዳን በኩል ኮሪደር እንዲከፈት የቀጠለው ጥያቄ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ደህንነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል እየተደረገ ያለው ሴራ አካል መሆኑን ገሀድ የወጣ እውነት ሆኗል።የኢትዮጵያ መንግሥት ለትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ በአፋር በኩል በየብስ ትራንስፖርት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ በቦሌ አለማቀፍ አየር መንገድ በኩል ድጋፎች እንዲጓጓዙ በማመቻቸት የተለያዩ አማራጭ መንገዶችን መከፈቱ ይታወሳል።

ማንኛውም እርዳታ የሚሰጥ ሃይል በአንድ ሀገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ የሀገሪቱን ህግ አክብሮ ነው እርዳታ ማድረስ ያለበት ያሉት የኢዜአ ምንጮች ፤ሉአላዊ በሆነና መንግስት ባለበት ሀገር ላይ እኛ ነን የምናዘው እያሉ እንደሚገኙም ጠቅሰዋል።ሆኖም የአሸባሪ ህወሃት ቡድን በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ ወረራ በመፈጸም በአፋር በኩል የሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ እንዲስተጓጎል አድርጎ ቢቆይም ዝምታን የመረጡት አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት ኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ሌላ መተላለፊያ ኮሪደር እንድትከፍት ግፊት እያደረጉ ነው።

አሜሪካን ጨምሮ የምዕራባውያኑ መንግሥታት የሰብዓዊ ዕርዳታን በማገድ ላይ ያለውን የሕወሃት አሸባሪ ቡድን ድርጊቱን በዝምታ በማለፍ አሁን ላይ መንግሥት ደህንነቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሌላ ኮሪደር እንዲከፍት ጫና እያደረጉ ነው።ምእራባዊያን የኢትዮጵያ ደህንነት ጉዳይ የራሱ ጉዳይ በማለት በእርዳታ ስም ለአሸባሪ ቡድኑ የጦር መሳሪያ እናስገባ ፤ አሸባሪ ይግባና ሀገሪቱን እናፈራርሳት እያሉ እንደሚገኙ ነው የገለፁት።

ድንበርን አልፎ ወረራ በፈጸመ ሀገር በኩል ኮሪደር ክፈቱ እርዳታ ይግባ በሚል መንግስትን እያስገደዱ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት።መንግስት ከሱዳን በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ከ 300 በላይ አሸባሪዎች መያዙን በቅርቡ ይፋ ማድረጉ የሚታወቅ ነው።በእርዳታ ስም የሚንቀሳቀሱ ምእራባዊያን ሀገራት ሁሉ ነገራቸው ሽብርተኛውን ህወሃት የማዳን ኢትዮጵያን የማድከም አላማን ይዘው ነው የሚንቀሳቀሱት።

እናም ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች በአሁኑ ወቅት የዩ.ኤስ.ኤይድ ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር በሱዳን እና ኢትዮጵያ እያደርጉት ያለው ጉብኝት በኢትዮጵያን ላይ ጫና በማድረግ እየሆነ ያለው ሴራ አካል ሊሆን ይችላል የሚል ግምት እንዳላቸው የኢዜአ ምንጮች ይጠቅሳሉ።በሱዳን በኩል የእርዳታ ማስተላለፊያ ኮሪደር እንዲከፈት የሚደረገው ጫና የሚመነጨው የጦር መሣሪያን በዚህ ኮሪደር በኩል ወደ ሕወሃት ለማሸጋገር ካለው ፍላጐትና ሴራ እንጂ የአስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ጉዳይ አደለም ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት የከፈተው አውዳሚ ትንኮሳ በአስቸኳይ ማስቆም እንዳለበት እንኳን ምዕራባውያን እስካሁን ድረስ ምንም ያሉት ነገር የለም።ይባስ ብሎ አሸባሪው ቡድን ጦርነት ቀስቃሽ ድርጊቱን በማራመድ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በኩል ዋና ዋና የሰብአዊ ድጋፍ መተላለፊያ መንገዶችን በመዝጋት ለትግራይ ህዝብ ያለውን ጭካኔ ያሳየበት እንደሆነ አንስተዋል፡፡

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ወ/ሮ ኤርጎጌ ተስፋዬ በቅርቡ በቲዊተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ሰብአዊ እርዳታው በአማራና በአፋር ክልሎች በኩል ወደ ትግራይ ክልል መግባት መፈቀዱን ገልፀው ፤በሱዳን በኩል ሌላ ኮሪደር ይከፈት በሚል አጀንዳ ማስገደድ ግን የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ማፈራረስ ስጋት ላይ ለመጣል እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የብሔራዊ የአደጋና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በቅርቡ ለኢዜአ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከአማራና አፋር ክልሎች ልዩ ኃይሎች ጋር በመፋለም ላይ የሚገኘው አሸባሪው ህወሃት ከ 170 በላይ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ማስቆሙን መግለጻቸው ይታወሳል።

የአሸባሪው ህወሓት የሰብዓዊ ዕርዳታ ለተቸገረው የትግራይ ሕዝብ እንዳይደርስ ያደረገው ክፉ ጥረት በሚዲያ መጋለጥ ያለበት ጉዳይ መሆኑ ተጠቅሰዋል።“ለኛ ታዛችሁ እርስ በርስ እየተባላችሁ የማትጠቅሙ ሆናችሁ ኑሩ ፤ አለበለዚያ መፍረስ አለባችሁ” የሚለው የምእራባዊያን ሴራ ፊትለፊት አፍጥጦ የመጣ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን አሁን እየሰጠነው ያለውን ምላሽ አጠናክረን መሄድ ይገባናል ብለዋል።

Exit mobile version