Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሐት ታዳጊዎች ዕጽ እንዲወስዱ እንደሚያደርጋቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጡ

አአሸባሪው የህወሐት ቡድን ለውጊያ እሚያሰልፋቸው ታዳጊዎች ዕጽ እንዲወስዱ እንደሚያደርጋቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች ከአፋር ግንባር ተገኙ፡፡

ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) በተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ መሰየሙ ይታወሳል፡፡

ከሰሞኑ በአፋር ከልል በኩል አሸባሪ ቡድኑ በከፈተው ውግያ የተማረኩ ታዳጊዎች ዕጽ እንደሚጠቀሙ የሚያሳይ መረጃ ተገኝቷል፡፡

ከታች በምስሉ ላይ የምትመለከቷቸው ታዳጊዎች እንዲጠቀሙበት ከተሰጣቸው ዕጽ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከታማኝ ምንጭ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ከዚህ ቀደም ህወሐት ለውጊያ እሚያሰልፋቸው ታዳጊዎች ዕጽ እንደሚወስዱ መረጃዎች በፎቶ ተደግፈው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

በዚያን ጊዜ ታዳጊዎቹ ዕጹን ከአንገት ማህተብባቸው ጋር አስረው እንደሚንቀሳቀሱ በፎቶ የተደገፈ መረጃ መውጣቱ አይዘነጋም፡፡(ዋልታ)

Exit mobile version