Site icon ETHIO12.COM

“ጦርነቱ ከትህነግ ሳይሆን ትህነግን ከቀጠሩት የውጭ ሃይሎች ጋር መሆኑን እናውጅ”

ጦርነቱ ከውጭ ባዕድ ኃይል ጋር መሆኑን ለመላው የዓለም ሕዝብ ማሳውቀ አንዱና ዋናው የደጀኑ ሃይል ስራ መሆን እንዳለበት የህግ ባለሞያው ጓንጉል ተሻገር ” ሁሉም ሊያውቀው የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ” ሲሉ አስታወቁ።

ምዕራባውያን፣ እነ CNN BBC, DW, Reuters, Washington Post, Newyork Times ወዘተ፣ የሚሰኙትን ሚዲያዎች በአብነት በመጥቀስ አቶ ጓንጉል እንዳሉት የዓለም ህዝብ ኢትዮጵያውያን ተገደው የገቡበትን ጦርነት አቅጣጫ እያሳቱ ነው።

“የዓለምን ሕዝብ ለማወናበድ ኢትዮጵያውያን የእርስ በርስ ጦርነት ላይ ያለን፣ ከትህነግ ጋር ብቻ የምንዋጋ አድርገው ያቀርባሉ” ያሉት አንጋፋው የሕግ ባለሙያ፣ “ጦርነቱ ወዲያና ወዲህ የሌለበት ትህነግ የሚባለውን አሸባሪ ሃይል ገዝተው ከለቀቁብን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች ጋር ነው” ብለዋል። ዓለም ዓይኑን ጨፍኖ ማየት፣ ጆሮውን ደፍኖ መስማት ባይፈልግም ይህን ደጋገሞ ማሳወቅ እጅግ አስፈላጊና ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንን አስታውቀዋል።

“ጦርነቱ ተንደባለን ስንርመጠመጥ እንድንኖር ከሚፈልጉ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ደመኞች ጋር ነው። ትህነግ ባንዳ ነች ” ሲሉ አበክረው ያስታወቁት አቶ ጓንንጉል፣ እገሌ ከገሌ ሳይባል የማህበራዊ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞችና መላው የሚዲያ ሠዎች፣ የማህበራዊ ድር ተጠቃሚዎች ሲዘገቡ ይህን ግልጽ እውነት ሊዘነጉ እንደሚገባ መክረዋል። ከዚህ ጦርነት ጀርባ ያሉ ሁሉ መታሰቢያቸው መቅመጥ ያለበት ከአሁኑ በመሆኑ ሚዲያዎች ይህንን ሃቅ ማስጨበጥና አቅጣጫ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

ጦርነቱ ከውስን ጎጠኛና የተገዙ ባንዳዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከታሪካዊ የአገራችን ጠላቶች ጋር መሆኑንን ዓለም ቢሰማም ባይሰማም ደጋግሞ መግለጽ፣ በሚገኘው አውድ ሁሉ ይህንኑ ማስተጋባት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ ያስታወቁት አቶ ጓንጉል፣ ጦርነቱን ከዚህ ውጭ ከላይ የተዘረዘሩት ሚዲያዎች ሆን ብለው እንደሚሉት ትህነግ ከሚባል ባንዳ ጋር የሚደረግ አድርጎ ማሳየት መስዋዕትነቱን ማሳነስ፣ ለጠላቶቻችንም ምሽግ መስራት ነው።

“ዛሬ መላው ዓለም ትክክለኛውን ገፅታ ተረድቶታል። እነ አሜሪካ ሶርያን፣ የመንን፣ ሊቢያን ወዘተ ሲያፈርሱ እንደ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ያሉ ቅጥረኞችን ይዘው ነው” ሲሉ በገሃድ የሚታውቁ ማስረጃዎችን አጣቅሰው አቶ ጓንጉል እንዳሉት፣ “ምዕራባውያን ራሳቸውን እንጂ ማንንም አያታልሉም፤ ካታለሉም የሚያታልሉት ራሳቸውን ብቻ ነው”

እንደ ትህነግ ላላ የዓላማቸው አስፈጻሚ ባንዳ ድርጅት ወይም ተቃዋሚዎች፣ መሳርያ፣ በሚልየኖች የሚቆጠር ዶላር አሽገው ፣ ስንቅ አቅርበው፣ እንደ ሲኤንኤን፣ ቢቢሲ ያሉ ሚዲያዎችን በማሰማራት አገራትን አፍረሰዋል። በሚያፈርሷቸው አገራት አጎራባቾች በኩል እየተንጠላጠሉና ኮሪዶር በማበጀት ወንበዴ አስርገው የፈጸሙትን አቶ ጓንጉል አስታውሰው፣ “ዛሬም” አሉ “ዛሬም በተመሳሳይ ከትህነግ ጀርባ ግብፅና ሱዳን እገዛ ተደርጎላቸው የኮሪዶር ያለህ የሚባለው ሌሎች ላይ የደረሰውን ለመፈጸም ነው” ሲሉ የጉዳዩን ተያያዥነት ያሳያሉ።

“ከግብፅና ሱዳን ጀርባ the “great” Satan¹ አለች።ከዛም አልፎ እነ አሜሪካ በቀጥታ ጣልቃ እየገቡ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ “ኢትዮጵያውያን” ቅጥረኞቻቸውንም ስለ ሰላም የመስበክ ስራ ላይ እንዲሰሩ አሰማርተዋቸዋል” የሚሉት የህግ ባለሙያው፣ ጦርነቱ ከተራ ሽፍታ ጋር እንዳልሆነ ዓለም እንዲረዳ መሰራት፣ ትህነግም የተሸጠ ባንዳ እንደሆነ ትውልድ እንዲረዳ መደረግ እንዳለበት አጥብቀው ያሳስባሉ።

“ጉዳዩ በእቅድ የሚመራ፣ ዋና ማዘዣ ማዕከል ያለው፣ የዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች፣ የታላላቅ አገራት መሪዎች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚባሉ ግለሰቦች፣ ህያ አራት ሰዓት በቅብብሎሽ የተሳተፉበት ኢትዮጵያን የማፍረስ ዘመቻ ካላስደነገጠን ምን ሊያስደነግጠን ይችላል” ሲሉ ዶክተር ሃይማኖት ከአቶ ጓንጉል ጋር የሚቀራረብ አሳብ ሰንዝረው ነበር።

“በአሁን ወቅት የምንዋጋው ኢትዮጵያን ሊያጠፋ ከመጣ ከውጭ ጠላት ጋር ነው የምለው ለዚህ ነው” ሲል ዳግመኛ አስረግተው የሚናገሩት አቶ ጓንጉል፣” አራት ነጥብ፣ ትህነግና የሲአይኤ ቅጥረኛ ምሁራን አምስተኛ ረድፈኞች ናቸው። ወያኔ በዋናነት ብረት አንስታ አምስተኛ ረድፈኛ Fifth columnist ² ሚናዋን አጠናክራ ይዛለች። የሲአይኤ ቅጥረኞች ደግሞ አትችሏትም ተደራደሩ በማለት የተዋጊውን ሞራል ለመስበር ይሞክራሉ” ሲሉ ባቋቋም የሚለያዩ፣ በግብር ግን ኢትዮጵያን በሁለት ቢላዋ የሚያደሙትን ኮንነዋል። ሲጨርሱም ” ሁሉም ቢያሱእሩ ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች!” በሚል ማተብ አትመዋል።

¹ Iranian authorities use it as a code-name for the United States. ² fifth column:- a group within a country at war who are sympathetic to or working for its enemies.

Exit mobile version