Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ቡድን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እየደረሰበት እንደሚገኝ አብን ገለጸ

ይሄ ሁሉ የአሸባሪ ቡድኑ መፍጨርጨር ‹‹የሽሮ ድንፋታ ውሃ እስኪገባበት ነው›› እንደሚባለው

ወደ አማራ ክልል በወረራ የገባው የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እየደረሰበት ይገኛል ሲሉ በጦር ግንባር ተሰልፈው እየተሳተፉ የሚገኙት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን ) የአደረጃጀት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ ገለጹ፡፡

አቶ ጋሻው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ‹‹ትናንትና በነበረው ውጊያ ከፍተኛ የሆነ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሶባቸዋል፡፡ ከመከላከያ ዘርፈዋቸው የነበሩ የጦር መሳሪዎች አመድ ሆነዋል፡፡ በጣም ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ውድመት ደርሶባቸዋል››፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ የአማራ ሕዝብና አሁን ውጊያ እየተደረገ ያለባቸው አካባቢዎች ህወሃት እጅግ በጣም የተዳከመና የመከላከል ደረጃ ላይ መሆኑንና በአንጻሩም፤ የወገን ጦር በከፍተኛ መነቃቃት ላይ እንደሚገኝ ሊገነዘቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ህዝቡ አካባቢውን ባለመልቀቅ፣ የኢትዮጵያን ሰራዊት በመደገፍ፣ ለአማራ ሃይል ትብብር በማድረግና መውጫ መግቢያቸውን በመጠቆም እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም አመልክተዋል፡፡

“ይሄ ሁሉ የአሸባሪ ቡድኑ መፍጨርጨር ‹‹የሽሮ ድንፋታ ውሃ እስኪገባበት ነው›› እንደሚባለው ከእዛ ድንፋታ ያለፋ እንደማይሆን በርግጠኝነት መናገር እችላለሁ፣ ህዝባዊ ሃይሉ ያለው መናበብ በጣም የሚያስደስት ነው፡፡ ምናልባት በቃላት ለመናገር አስቸጋሪ ነው፣ በአካል የምታየውን ወኔና ጽናት በቃላት ለመግለጽ በጣም ይከብዳል” ብለዋል፡፡

በዘላለም ግዛው – (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version