Site icon ETHIO12.COM

ኦብነግ ከመንግስት ጎን በመቆም አሸባሪውን ትህነግን እንደሚፋለም አስታውቀ

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ድርጅት የሶማሌን ህዝብ ከፋፍሎ ግፍ ሲፈጽም እንደኖረ ፣ ግፉም የማይረሳ መሆኑንን በማስታወቀ ” ይህን አሸናሪ ሃይል ከመንግስትና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመሆን እፋለመዋለሁ” ሲል አስታወቀ። ድርጅቱ ይህን ያለው የ37ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ዛሬ ባከበረበት ወቅት ነው። የሶማሌ ህዝብ በጠላት እንደቀድሞ እንደማይከፋፈልም አስታውቋል።

በሶማሌ ክልል ህዝቦች መካከል መከፋፈልና ግፍችን ሲፈፅም የነበረውን በሀገር ላይ ጦርነት ያወጀውን አሸባሪውን ትህነግ ከመንግስት ጎን በመቆም ሁሉም በጋራ እንዲታገል ጥሪ መቅረቡን ተከትሎ ነው ኦብነግ አቋሙን ያስታወቀው።

የኦብነግ የ37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በጅግጅጋ ከተማ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ተከብራል። በመድረኩ ላይ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዑመር፣ የሶማሊ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኢንጅነር መሀመድ ሻሌና የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ምክትል ሊቀመንበር አቶ አህመድ ያሲን እንደገለፁት ባለፉት 27 አመታት በኦብነግ ደጋፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች ላይ በአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ይደርስ የነበረው ግፍና በደል በቃል ለመግለጽ የሚክብድ ነው።

ኦብነግ ለዛሬ ቀን ለመድረስ ብዙ ውጣ ውረዶችን ማለፉን ገልጸዋል።“ይህ ድርጅት ዛሬ ላለው የሶማሌ ክልል ህዝቦች መብት ፣ ለነፃነት እና ዲሞክራሲ መታገሉንም ገልፀዋል። የሶማሌ ክልል ህዝቦችን ሲከፋፍልና ግፍ ሲፈፅም የነበረውን፣ በሀገር ላይ ጦርነት ያወጀውን አሸባሪውን የህወሓት ሀይል ከመንግስት ጎን በመቆም እንደሚዋጉትም ገልፀዋል።

በመድረኩ በክብር እንድነት የተገኙት የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የኦብነግ ባለስልጣናትና ደጋፊዎችን እንኳን ለ37ተኛው አመት የምስረታ አደረሳችሁ።ላለፉት 27 አመታት ወንድማማች የሶማሌ ክልል ህዝቦችን በመከፋፈል በጎሳ፣ በዘርና በቡድን በመነጣጠል አንድ መሆን እንዳንችል ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል። ከለውጡ ወዲህ ግን እነዛን መርዛማ ሀሳቦች በመስበር፣ ሲደርሱብን የነበሩ ግፍና በደሎችን በማስቀረት ሰላም የሰፈነበትና ዲሞክራሲ የተረጋገጠበት ክልል ሰርተናል ብለዋል።

ካሁን በፊት የኦብነግ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ብዙ ግፎችና በደሎች ይፈፀሙ እንደነበር አንስተው ከለውጡ ወዲህ ግን ያን ማስቀረት መቻሉንና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መስራት መጀመራቸውን ገልፀዋል። አሸባሪው ህወሓት ባለፋት 27 አመታት ያደረሰው ግፍና በደል አልበቃ ብሎት ሀገር ለማፍረስ ጦርነት መክፈቱን አስታውሰው ሀገር የማፍረስ ተግባር የሚደግፉ የቀድሞው ስረአት ርዝራዦች መኖራቸውን ጠቁመው ህዝቡ ከመንግስት ጎን ቆሞ በቃቹ ሊላቸው እንደሚገባም ተናግረዋል።

በመድረኩ የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችም አንድነትንና ሰላምን በማጠናከር ረገድ የክልሉ ማህበረሰብ የበኩልን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ነው።

Exit mobile version